መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በገንዘብ ግብይት ውስጥ ያሉ እስላማዊ ስነ-ምግባሮች

በዚህ ትምህርት ውስጥ ከገንዘብ ግብይቶች ውስጥ ስለሚያስፈልጉ አንዳንድ ስነ-ምግባሮችን ትማራላችሁ።

1 በእስለምና ውስጥ ስለ ገንዘብ ግብይት ፅንሰ ሃሳብ ትማራላችሁ።2 የገንዘብ ግብይትን በተመለከተ የእስምና ህግ የበላይነትን ትማራላችሁ።3 በገንዘብ ግብይት ውስጥ መታየት ያለበት እስላማዊ ስነምግባር ትማራላችሁ።

ስነ-ምግባር (አህላቅ) ከሁሉም የትምህርት ጉዳዮች ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው። የእስልምና የፋይናንስ ስርአት በጣም ወሳኝ ከሆኑ መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ከእሱ የተገኙ እና በእሱ የተጠበቁ የሞራል እሴቶች ናቸው። እስላማዊ የፋይናንስ ስርአትን ከሌሎቹ የፋይናንስ ስርአቶች ልዩ የሚያደርገውም ይህ ነው።

የገንዘብ ግብይት በእስምና ውስጥ

ገቢ ለማግኘት ሲባል በሸሪአ መስራት የተፈቀዱ ነገሮችን ሁሉ መስራት ይፈቅዳል። የገንዘብ ግብይት ገንዘብ ላይ ያተኮሩ ውሎችን ወይም የገንዘብ መብት የሚያስገኙ ለምሳሌ እንደ መግዛት እና መሸጥ ፣ ማከራየት ፣ በቡድን መነገድ እና ሌሎች ውሎችን ሁሉ ያጠቃልላል። ከእስላማዊ ግብይቶች ጋር የተያያዙ ውሳኔዎች የሰዎችን የገንዘብ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚቆጣጠሩ ህጋዊ ውሳኔዎች ናቸው።

የእስላማዊ የገንዘብ ግብይቶች ግቦች እና አላማዎች

١
ትዕዛዙን በመታዘዝ የሃያሉ አሏህ ውዴታ ማግኘት፡ በእርግጥ አሏህ እንዲህ አለ፡ "እሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው። በጋራዎች እና በመንገዶችም ሂዱ። ከሲሳዩም ብሉ። መመለሻም ወደ እሱ ብቻ ነው።" ሙልክ 15
٢
ገቢ እና መተዳደሪያ ሪዝቅ መፈለግ በህይወት ለመኖር ፣ ሃብት ለማካበት ፣ አገልግሎት ለማግኘት እና የተፈቀደውን የዱንያን ደስታ ለማጣጣም አስፈላጊ ነው።
٣
የተፈቀደውን በመፈለግ እና በግብይቶች ሁሉ የተከለከለውን በመራቅ በጀነት ውስጥ ከፍ ያለን ደረጃ ማግኘት ይቻላል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹እውነተኛ እና ታማኝ ነጋዴ ከነብያቶች ፣ ከእውነተኞች እና ከሰማዕታን ጋር ነው።›› (ትርሚዚ 1209)
٤
እድገት እና መሻሻል ማምጣት ፣ መልካም ማህበረሰብ መገንባት በሚያስችል መልኩ በሸሪአዊ ትዕዛዛት መሰረት ገንዘብን ፈሰስ ማድረግ፡፡
٥
ሃያሉ አሏህ ከእነሱ የሚፈልገው ነገር ለማሳካት እና በንግግራቸው እና በስራቸው አሏህን እንዲያመልኩ (እንዲገዙ) የማህበረሰቡን አባላት የሁሉንም ፍላጎት ማርካት ነው።
٦
በአሏህ የሸሪአ ህግ መሰረት በምድር ላይ የተተኪዎችን ሚና ማሳካት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እሱ ያ በምድር ምትኮች ያደረጋችሁ፤ በሰጠናችሁም ፀጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ነው። ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው። እሱ እጅግ በጣም መሃሪ ርህሩህ ነው።" (ሱረቱል አንአም165)

በእስላማዊ ግብይቶች ውስጥ ያለ ሚዛን

እስልምና እውነተኛ ሃይማኖት ነው። ለሰዎች ጥቅም እና ለእነሱ መሻሻል የሚሆን ነገር ይዞ የመጣ ነው። ምክኒያቱም ሰዎችን የፈጠረው ፣ ስለ እነሱ የበለጠ የሚያውቀው እና ለእነሱ የተሻለውን የሚያውቅ የሆነው የአሏህ ሃይማኖት ነውና። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሁሉን የፈጠረ አምላክ ፣ እሱ እውቀተ ረቂቁ ፣ ውስጥን አዋቂ ሲሆን (ሚስጥርን ሁሉ) አያውቅምን?" (ሱረቱል ሙልክ 14) ከሌሎች ህጎች እና ስርአት ጋር ሲነፃፀር እስልምና የሰው ልጅ አካላዊ ፍላጎቶች እና የአለም ጎዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የፋይናንስ ስርአት ይዞ የመጣ ነው። እንዲሁም የነፍስን ፍላጎት እና የመጭውን አለም ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው።

አንደኛ እስላማዊ ጉዳይ፡ የእስልምና ህግ የሰዎችን የገንዘብ ግብይት በተገበያዮች መካከል ፍትህን በሚያሰፍን መልኩ ግብይቶቻቸውን ይቆጣጠራል። እያንዳንዱም ሰው መብቱን በሚያገኝበት እና ሁሉም በሚደሰትበት ከዚህ በተጨማሪ ብዙ ግብይቶችን ህጋዊ እና የተፈቀዱ አድርጓል። የተከለከሉ ወይም ህገወጥ የሆኑ ግብይቶች ማህበረሰቡን የሚጎዱ እና አንድን ወገን ብቻ የሚጠቅሙ የሆኑ ብቻ ናቸው።

ሁለተኛ ሃይማኖታዊ ጉዳይ፡ ሁሉም የሸሪአ የህግ ድንጋጌዎች ዋና ግባቸው የአሏህን ውዴታ ማግኘት እና ጀነትን መውረስ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከእስልምና የገንዘብ ግብይት ስርአት ጋር በተያያዘ የተደነገጉ ህጎች በአማኞች መካከል ወንድማማችነትን ያረጋግጣሉ። ይህም ፍትሃዊነትን ጠቅለል አድርጎ በመያዝ ፣ በጎነትን ያበረታታል ለምሳሌ ባለእዳ ላይ መለሳለስ ያበረታታል። ገዳይ የሆኑትን ልክ እንደ አራጣ እና የእድል ጨዋታዎችን ህገወጥ ያደርጋል።

የገንዘብ ግብይቶች ምድቦች ከመብት አንፃር ሲታይ

አንደኛ ፍትህ፡ የሁለቱን ወገኖች መበት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በገንዘብ ግብይታቸው ሳይጨምሩ ወይም ሳይቀንሱ ግብይታቸውን ማከናወን ነው። ለምሳሌ መሸጥ ፣ ኪራይ ፣ ማጫረት እና መሰል ነገሮች ናቸው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህ ንግድን ፈቀደ።" (ሱረቱል በቀራ 275) ሁለተኛ አል-ፈድል፡ ይህም ቅንንት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "የድህነት ባለቤት የሆነም (ባለዕዳ) ሰው ቢኖር እስኪያገኝ ድረስ ማቆየት ነው። (በመማር) መመፅወታችሁ ለእናንተ በላጭ ነው። የምታውቁ ብትሆኑ (ትሰሩታላችሁ)።" (ሱረቱል በቀራ 280) ልክ እንደዚሁ ከአንድ ሰራተኛ ጋር በገንዘብ ተባብሎ ይስማማና ከዚያም ከተባባሉት አስበልጦ መስጠት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "በጎ ስራንም ስሩ፤ አሏህ በጎ ሰሪዎችን ይወዳልና።" (ሱረቱል በቀራ 195)

ሶስተኛ ኢፍትሃዊነት፡ ይህም አንድ ሰው ከሚገባው ከመብቱ በላይ የሚያገኝበት እና ያለፍትህ የሰዎችን ገንዘብ የሚበላበት ነው። ለምሳሌ አራጣ (ወለድ) ፣ ቁማር ፣ የሰራተኛውን መብት መንፈግ ወ.ዘ.ተ ናቸው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "(278) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ፍሩ። ከአራጣም የቀረውን ተው። አማኞች እንደሆናችሁ ተጠንቀቁ። (279) የታዘዛችሁትን ባትሰሩም ከአሏህ እና ከመልዕክተኛው በሆነች ጦር (መወጋታችሁን) እወቁ። በትፀፀቱም ለእናንተ የገንዘባችሁ ዋናው አላችሁ። አትበደሉም፤ አትበደሉምም።" (ሱረቱል በቀራ 278-279) የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አሏህ ‹በትንሳኤዋ ቀን በሶስት ሰዎች ላይ እቃወማለሁ› አለ። 1 በስሜ ቃልኪዳን የገባ ነገርግን ቃሉን ያጠፈ (የከዳ) 2 አንድን ነፃ ሰው (እንደ ባሪ አድርጎ) የሸጠና የዋጋውን ተመን የበላ 3 የጉልበት ሰራተኛ የቀጠረ እና ሙሉ ስራውን ሰርቶ ካጠኛቀቀለት በኋላ የቀን ክፍያውን አልከፍልም ያሉ ናቸው።›› (ቡኻሪ 2227)

1 ከእስምና የግብይት ስነ-ምግባሮች መካከል

١
የተፈቀዱ ውሎችን ማክበር እና በታማኝነት መፈፀም። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እናንተ ያመኛችሁ ሆይ! ቃልኪዳናችሁን (ውላችሁን) ሙሉ።" (ሱረቱል ማኢዳ 1)
٢
አደራን መመለስ፡ አሏህ እንዲህ አለ፡ "አደራ የተሰጠው ሰው አደራውን ይመልስ። ጌታውን አሏህንም ይፍራ።" (ሱረቱል በቀራ 283)
٣
ምስክርነትን አይደብቅ፡ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ምስክርነትንም አትደብቁ። የሚደብቀውም ሰው በልቡ ውስጥ እሱ ሃጢያተኛ ነው። አሏህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ አዋቂ ነው።" (ሱረቱል በቀራ 283)
٤
እውነተኛነት እና ቅንነት፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ሁለቱ ሻጮች ሲናገሩ፡ ‹‹እውነተኞችና ግልፅ ከሆኑ በመሸጫቸው ይባረካሉ። ቢደብቁና ቢዋሹም የሽያጫቸው በረካ ይጠፋል።›› (ቡኻሪ 2079 ፣ ሙስሊም 1532)
٥
ታማኝ መሆን፤ አታላይ ወይም ከዳተኛ ኣለመሆን። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ያታለለን ሰው እሱ ከእኛ አይደለም።›› (ሙስሊም 101)

2 ከእስላማዊ የግብይት ስነምግባሮች መካከል

١
1 አጠራጣሪነገሮች መራቅ፡ ጥርጣሬ ወይም አሻሚ ነገር ማለት ለሰው ልጅ ስለመፈቀዳቸው እና ስላለመፈቀዳቸው እርግጠኛ አለመሆን መቻል ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ህጋዊ እና ህጋዊ ያልሆኑ ነገሮች ግልፅ ናቸው። ነገርግን በመካከላቸው አጠራጣሪ ነገሮች አሉ። አብዛሃኛዎቹ ሰዎች ስለ እነሱ እውቀት የላቸውም። ከአጠራጣሪ ነገሮች እራሱን የጠበቀ ሰው ሃይማኖቱን እና ክብሩን ጠበቀ።›› (ቡኻሪ 52 ፣ ሙስሊም 1599)
٢
የሰዎችን ገንዘብ በውሸት (አላግባብ) አለመብላት፡ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ገንዘባችሁንም አላግባብ አትብሉ። ከሰዎች ንብረቶች ከፊሉን ያለ አግባብ በመበደል እና እያወቃችሁ ትበሉ ዘንድ ዳኞችን ለመደለል አትጠቀሙበት።" (ሱረቱል በቀራ 188)
٣
አንድ ሙስሊም ሰው ለእራሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ መውደድ አለበት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹ከእናንተ መካከል አንዳችሁም ለእራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።›› (ቡኻሪ 13 ፣ ሙስሊም 45)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር