የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሶላት ቅድመሁኔታዎች እና ድንጋጌዎች
ለሠላት ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች
ከሐደስና ከነጃሳ መጥራት አብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- “ሶላት ያለ ጦሃራ አይቀበልም” (ሙስሊም 224)።
ሀፍረተ ገላን በአጭርነትና ወይም በስስነት የሰውነት ክፍሎችን የማያጋልጥና የማያሳይ በሆነ ልብስ መሸፈን የግድ ነው፡፡
ከእምብርቱ እስከ ጉልበቱ ድረስ ነው፡፡
ለሴት፡ ሰላት ለመስገድ የደረሰች ሴት ሀፍረተ ገላ ከፊቷና ከመዳፎቿ በስተቀር ሰውነቷ በሙሉ ነው፡፡ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈችው፡- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “አላህ ለወር አበባ የደረሰች ሴት ሶላትን (ማለትም የአዋቂን) በህጃብ እንጂ አይቀበልም። ” (አቡ ዳዉድ 641፣ ቲርሚዚይ 377)
አላህ (ሱ.ወ)፡- «ከየትም (ለጉዞ) ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ አቅጣጫ አዙር፡፡» ብሏል፡፡ (አል በቀራ 149)
የሙስሊሞች የስግደት አቅጣጫ የተከበረው ካዕባ ነው፡፡ እሷን የገነባት የነብያት አባት የሆነው ኢብራሂም(ዐ.ሰ) ነው ፡፡ ነብያት ወደርሷ የአምልኮ ጉዞ (ሐጅ) አድርገዋል፡፡ እርሷ የማትጠቅም የማትጎዳም ድንጋይ እንደሆነች እናውቃለን፡፡ ግን አላህ (ሱ.ወ) ሙስሊሞች በሙሉ ወደ አንድ አቅጣጫ በመዞር አንድ እንዲሆኑ፣ ስንሰግድ ወደርሷ እንድንዞር ወይም እንድንቅጣጭ አዞናል፡፡ ስለሆነም፣ ወደ ካዕባ በመዞራችን የአላህ ባርነታችንን እንገልፅበታለን፡፡
ወደ መካ አቅጣጫ መዞር
ልክ የተቀሩት ግዴታዎች በመቸገር ምክንያት ግዴታነታቸው እንደሚነሳ ሁሉ፣ በበሽታ ወይም በሌላ ምክንያት ወደ ካዕባ መዞር ላልቻለም ግዴታነቱ ይነሳለታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት፡፡» ይላል፡፡ (አል ተጋቡን 16)
ይህ ለሠላት ትክክለኛነት መስፈርት ነው፡፡ ወቅቷ ከመግባቱ በፊት የተሰገደች ሠላት ትክክለኛ አትሆንም፡፡ ከወቅቷ ማዘግየትም የተከለከለ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- «ሶላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡» ይላል፡፡ (አል ኒሳእ 103)
ሠላትን በመጀመሪያው ወቅት ላይ መስገዱ በላጭ ነው፡፡በኡሙ ፋርዋ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈችው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተጠየቁ፡- የትኞቹ ሥራዎች በላጭ ናቸው? እንዲህ ብለዋል፡- “ሶላት በመጀመሪያ ግዜ ላይ መስገድ ነው” (አቡ ዳዉድ 426)።
ሠላትን በወቅቷ መስገድ ግዴታ ነው፡፡ በማንኛውም ምክንያት ቢሆንም ሠላትን ማዘግየት ክልክል ነው፡፡ መሰብሰብ የተፈቀደበት ሁኔታ ስቀር
በእንቅልፍ ወይም በመርሳት ምክንያት ሠላት ያለፈው ሰው ባስታወሰ ጊዜ ፈጥኖ መስገድ አለበት። አነስ ቢን ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ ነቢይ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ሶላትን የረሳ ወይም ከርሷ የተኛ ሰው መካካሸው ስያስተውስ መስገድ ነው።” (ሙስሊም 684)።
የሠላት ግዴታነት
ለአቅመ አዳምና ሄዋን መድረስ የሚወሰነው ከሚከተሉት ምልክቶች አንዱ ሲሟላ ነው፡፡
አምስቱ የግዴታ ሠላቶችና ወቅቶቻቸው
የፈጅር ሠላት፡ ሁለት ረካዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ጎሕ ከሚወጣበት ጊዜ ሲሆን፣ በአድማስ ላይ ብርሃን ሲፈነጥቅ ወይም ጨለማ መገፈፍ ሲጀምር ይከሰታል፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ፀሐይ ስትወጣ ነው፡፡
የዙህር ሰላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ፀሐይ ከመሐል አናት በምታዘነብልበት ጊዜ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ የእያንዳንዱ ነገር ጥላ ከራሱ ቁመት ጋር ሲስተካከል ነው፡፡
የዐሥር ሠላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው የዙህር ወቅት ካበቃበት ጊዜ ጀምረ ሲሆን ይኸውም የእያንዳንዱ ነገር ጥላ ከራሱ ቁመት ጋር ሲስተካከል ነው፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ፀሐይ ስትጠልቅ ነው፡፡ አንድ ሙሰሊም ይህችን ሠላት፣ የፀሐይ ብርሃን ጮራ መድከምና መገርጣት ሳይጀምር ፈጠን ብሎ ሊሰግድ ይገባዋል፡፡
የመግሪብ ሠላት፡ ሦስት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ፀሐይ ከጠለቀችበትና ፍንጣቂዋ ከአድማስ ላይ ሲወገድ ወይም ሲደበቅ ነው፡፡ የሚያበቃው ደግሞ ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ የሚታየው ቀዩ ወጋገን ሲጠፋ ነው፡፡
የዒሻእ ሠላት፡ አራት ረከዓ ነው፡፡ ወቅቱ የሚጀምረው ቀዩ ብርሃን ከጠፋበት ቅጽበት ነው፡፡ የሚያበቃው እኩለ ሌሊት ላይ ነው፡፡ አስቸጋሪ ሁኔታ በሚገጥምበት ጊዜ ጎህ እስኪ ቀድ ባሉት ሰዓቶችም ውስጥ ሊሰገድ ይችላል፡፡