የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ኢድ በዓል
የተባረከው የጾም ፍቺ በዓል
በኢስላም ውስጥ፣ በዓል አንድ የአምልኮ ዘርፍን ስላጠናቀቁ ደስታን የሚገልጹበትና አላህ(ሱ.ወ) ለዚህ አምልኮ ስለመራቸውና ስለገጠማቸው እሱን የሚያመሰግኑበት አጋጣሚ ነው፡፡ በዒድ ቀን፣ የሚያማምሩ ልብሶችን በመልበስ፣ ለከጃዮች መልካም በመዋል በሰዎች ልቦና ውስጥ ደስታን መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ ኢስላም ያስተምራል፡፡ በማንኛውም የተፈቀዱ መንገዶች፣ የሁሉም ልቦና የደስታ ስሜት እንዲሰማውና የአላህን ጸጋ የሚያስታውስ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
የሙስሊሞች በዓል በዓመት ውስጥ ሙስሊሞች የሚያከብሯቸው ሁለት በዓላት አሉ፡፡ ከሁለቱ ቀናት ውጪ ሰዎች እንደ በዓል አድርገው የሚያከብሯቸውን ቀናቶች ማክበር አይፈቀድም፡፡ እነኚህ በዓላት፡
የበዓል ሠላት (የዒድ ሠላት)፡ ኢስላም፣ ሙስሊሞች ከሴቶችና ሕፃናት ጋር በመሆን በአንድነት ወጥተው ይህን ሠላት እንዲሰግዱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ አስተምሯል፡፡ የመስገጃ ጊዜው፣ ፀሐይ ወጥታ የጦር ዘንግ ያክል ከፍ ካለችበት ቅጽበት ጀምሮ ከሰማይ መሐከል እስከምታዘነብልበት ጊዜ ይረዝማል፡፡
አፈፃፀሙ፡ የዒድ ሠላት ሁለት ረከዓ ነው፡፡ ኢማሙ ሲያሰግድ ቁርኣን የሚያነበው ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲሆን ከሠላቱ በኋላም ሁለት ኹጥባዎችን ያደርጋል፡፡ በዒድ ሠላት ‹‹አላሁ አክበር›› የሚለውን ቃል በእያንዳንዱ ረከዓ መጀመሪያ ላይ ደጋግሞ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ላይ ፋቲሓን ማንበብ ሳይጀምር በፊት፣ ከመጀመሪያው የሠላት መግቢያ ተክቢራ ሌላ ስድስት ጊዜ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፡፡ በሁለተኛው ረከዓ ላይ ደግሞ ከመጨረሻው ሱጁድ ሲነሳና ሲቆም ከሚለው ተክቢራ ሌላ አምስት ጊዜ ‹‹አላሁ አክበር›› ይላል፡፡
በተፈቀዱ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም፣ በተቻለ መጠን፣ በቤተሰብ ውስጥ፣ ትልቁንም፣ ትንሹንም፣ ወንዱንም፣ ሴቱንም፣ እንዲደሰትና እንዲዝናና ማድረግ በኢስላም የተደነገገ ተወዳጅ ተግባር ነው፡፡ የሚያምር ልብስ መልበስም እንዲሁ የተወደደ ነው፡፡ በዒድ ቀን መጾም ክልክል ነው፡፡ በዒድ ቀን የሚወደደው፣ በመብላትና በማፍጠር አላህን መገዛት ነው፡፡
በኢድ ዋዜማ ሌሊቱን፣ እንዲሁም ወደ ዒድ ሠላት ሲወጣ፣ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት አላህን ማላቅ ኢስላም የደነገገው ተግባር ነው፡፡ የዒድ አልፊጥር ሠላት ተሰግዶ ሲያበቃ የተክቢራው ጊዜ ይጠናቀቃል፡፡ ይህ የሚደረገው፣ አላህ(ሱ.ወ) ወደ ጾም በመምራት፣ የተባረከውን የረመዳንን ወር ጾም ለማጠናቀቅ ስላበቃን፣ ለዋለልን ጸጋ እርሱን ለማመስገንና ደስታችንን ለመግለጽ ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ቁጥሮችንም ልትሞሉ፣ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህንን ደነገግንላችሁ)›› (አል በቀራ 185)
የተክቢራ አባባል፡
ወንዶች፣ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ ሰዎችን በማይረብሽ ወይም በማያስቸግር መልኩ ተክቢራን መመላለሳቸው የተደነገገ ተግባር ነው፡፡ ሴቶች ግን ድምፃቸውን ዝቅ ማድረግ አለባቸው፡፡