መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ትምህርት፡ ኢማን ከጉዞ ጋር

በሃያሉ አሏህ የተፈጠረን ውብ ተፈጥሮ መመልከት ፣ ማድነቅ እና የእግር ጉዞ ሽርሽር መሄድን እስልምና አይከለክልም። ነገርግን አንድ ሙስሊም ሰው ጉዞ ላይ በሚሆን ጊዜ ስንቆችን መሰነቅ እና የእስልምና ግብረገቦችን መላበስ አለበት። በዚህ ትምህርት የምናየው ይህንኑ ነው።

1 ሙስሊም ሰው በሃይማኖቱ እና በህይወቱ መካከል ያለን ነገር ያስተሳስራል።2 ፍጡራኖቹን እየተመለከተ የአሏህን ሃያልነት ያሰላስላል።

ጉዞዎች የሰው ለጆች ተፈጥሮን ለማየት እና ለማድነቅ የሚያደርጓቸው ልክ እንደ ሽርሽር እና የእግር ጉዞ ያሉ ናቸው።

በቁርአን ውስጥ ‹‹ጎዞ›› የሚለው ቃል በሃያሉ አሏህ ንግግር ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል። "ቁረይሾችን ለማላመድ (ባለዝሆኖቹን አጠፋ)። የብርድ እና የበጋን ወራት ጉዞ ሊያላምዳቸው ይህንን ሰራ።" (ሱረቱል ቁረይሽ 1-2) የክረምቱ ጉዞ የተባለው ቁረይሾች ለንግድ በክረምት ውስጥ ያደርጉት የነበረው ጉዞ ሲሆን ወደ የመን ጉዞ ያደርጉ ነበር። በበጋ ደግሞ ወደ ሻም (ሶሪያ ፣ ፈለስጢን ፣ ጆርዳን ፣ ሌባኖስ) ጉዞ ያደርጉ ነበር።

ጉዞዎች ኢማናችነን እንዴት ይጨምራሉ?

የሙስሊም ሰው ህይወት ከሃያሉ አሏህ እና በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ከህግጋቱ ጋር የተሳሰረ ነው። ጉዞና ጉብኝቶች አሏህ ለእኛ የደነገጋቸው ህጎች የሞሉበት ነው። ምክኒያቱም በዚህ አለም ሆነ በመጭው አለም ህይወት ውስጥ ታላቅ ጥቅሞችን ይዟል። ያ ደግሞ የሚገኘው አንድ ሰው በደንብ ሲሰራበት ነው።

አማኝ ሰው የአምልኮ ተግባራት ወደሚፈፀሙበት ቦታ ለምሳሌ ሐጅ እና ኡምራ ወይም እውቅት በመፈለግ ጉዞውን አንድ የአምልኮ ተግባር ማድረግ ይችላል። ከቤተሰቦቹ ከዘመዶቹ ጋር በማያያዝ ኒያውን ማሳመር ይችላል። ወይም ደግሞ ለቤተሰቦቹ በቂ ነገር ትቶ በመሄድ አሏህን በመታዘዝ እና ወደ አሏህ በመሸሽ እርዳታውን ይሻል።

"በል! በእርግጥ ሶላቴ ፣ እርዴ ፣ ህይወቴ ፣ ሞቴ ለአለማቱ ጌታ አሏህ ነው።" (ሱረቱ አንዐም 162)

ጉዞና ጉብኝቶች ለማስተንተን እና ለማሰላሰል ጥሩ እድሎች ናቸው

ፍጥረተ አለሙ የአሏህን ሃያልነነት ፣ እዝነት እና ጥበብ በሚያመላክቱ ነገሮች የተሞላ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በእርግጥ በሰማያት እና በምድር ፍጥረት ውስጥ ፣ በሌሊት እና በቀን መፈራረቅ ውስጥ ለሚረዱ ሰዎች ምልክቶች አላቸው።" (ሱረቱል ኢምራን 190) ለዚህም ነው በደስታ እይታ ብቻ ሳይሆን በማሰብ ፣ በማሰላሰል እና በማስተንተን እይታ እንድንመለከተው ያዘዘው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በሰማያት እና በምድር ግዛት ውስጥ፤ አሏህ የፈጠራቸውን ማንኛውንም ነገሮች አይመለከቱምን።" (ሱረቱ አል አእራፍ 185)

ልክ እንደዚሁ በመገለል (ኸልዋ) ውስጥ አንድ ሰው ነፍሱ ጋር የሚተሳሰብበት እና ለነገ ያስቀመጠውን ነገር የሚያስብበት ጥሩ እድል አለ። ከእራሱ ጋር ብቻውን ሆኖ እና ከአሏህ በቀር በእሱ ላይ ተመልካች (ተቆጣጣሪ) ከሌለ ማለት ነው።

የጉዞ መዳረሻህ ስትደርስ ምንድን ነው የምታደርገው?

በረባዳ ቦታ ወይም ሌላ የጉዞ መዳረሻው ላይ የደረሰ ሰው ቀጣዩን ዱአ (ፀሎት) ማለቱ ይመከራል።

ኸልዋ ቢንት ሐኪም እንዳስተላለፈችው (ረ.ዐ) እንዲህ አለች፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡ በጉዞ ቦታ ላይ (ቤት) አርፎ ‹‹ፍፁም በሆኑት የአሏህ ቃላት ከፍጡራኑ ክፋት እጠበቃለሁ። ያለ ሰው (ያን ቦታ ወይም ቤት ትቶ እስኪሄድ ድረስ ምንም ነገር አይጎዳውም። (ሙስሊም 25708)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር