የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በአላህ ጌትነት ማመን
በኃያሉ አላህ ጌትነት የማመን ትርጉም፡-
በፍጥረተ-ዓለሙ ውስጥ ያሉትን ነገሮች የፈጠረው አላህ ብቻውን ነው ከርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡” (አል- ዙመር፡62) የሰው ተግባር ግን አንድን ነገር ወደ ሌላ ቅርፅ መቀየር ወይም እርስ በእርሱ ማቆራኘትና የመሳሰሉት እንጂ ከባድና ከምንም ተነስቶ የሚፈጥረው ነገር የለም፡፡ ሙት የሆነውን ነገር ወደ ህይወት ማምጣትም አይችልም፡፡
ለፍጥረታት ሁሉ ሲሳይን የሚሰጠው አላህ ነው፡፡ ከርሱ ውጪ ሲሳይን ሰጪ የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “በምድር ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ቢሆን እንጂ…” (ሁድ፡6)
አላህ የሁሉም ነገር ባለቤት ነው፡፡ ከርሱ ሌላ የነገሮች እውነተኛ ባለቤት የለም፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “የሰማያትና የምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡» (አል-ማኢዳህ፡12ዐ)
የሁሉም ነገር አስተናባሪ እርሱ ነው፡፡ ከርሱ ሌላ ነገሮችን የሚየሰተናብር የለም፡፡ እንዲህ ይላል… «ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያዘጋጃል፡፡» (አል-ሰጅዳህ፡5)
የ አላህ ማስተናበርና የሰው ማስተናበር
በአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘመን የነበሩ አረብ አጋሪዎች በአላህ ጌትነት ያምኑ ነበር፡-
አንድ ሰው የፍጥረተ-ዓለሙ ፈጣሪ፣ አስተናባሪ፣ ህይወት ሰጪና ነሺ አላህ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ የአምልኮ ዓይነቶችን ከርሱ ውጪ ላሉ ነገሮች ማዋል በጣም የማያስገርም ነገር ነው፡፡ ይህ አስጠያፊ በደልና ታላቅ ወንጀል ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ያሉት “… ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና ያለውን (አስታውስ)፡፡” (ሉቅማን፡13)
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) አላህ ዘንድ ታላቅ ወንጀል ምን እንደሆነ ሲጠየቁ “አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ተጋሪን ማድረግህ ነው፡፡” በማለት መልሰዋል፡፡ (አል-ቡኻሪ፡4207 ሙስሊም፡86)
አንድ የአላህ ባሪያ በእርግጠኝነት የሚያውቅ ከሆነ፥ ከኃያሉ አላህ ውሳኔ ውጭ ሊሆን የሚችል ፍጡር እንደሌለ ይገነዘባል፡፡ ምክንያቱም የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት አላህ ሲሆን ከጥበቡ ጋር በሚስማማ መልኩ እንዳሻው የሚያደርጋቸው እርሱ ነው፡፡የሁሉም ፈጣሪ እርሱ ነው፡፡ ከአላህ ውጭ ያለው ፍጥረት ሁሉ የተፈጠረና ፈጣሪው ወደ ሆነው አላህ ፈላጊ ነው፡፡ ነገሮች ሁሉ በአላሀ እጅ ናቸው፡፡ ከርሱ ውጭ ፈጣሪ የለም፡፡ ከርሱ ውጭ ሲሳይን ሰጭ የለም፡፡ ከርሱ ሌላ ፍጥረተ-ዓለሙን የሚያስተናብር የለም፡፡ ያለርሱ ፈቃድ የምትንቀሳቀስ ቅንጣት ነገር የለችም፡፡ ያለርሱ ትዕዛዝ የምትቆምም የለችም፡፡ይህ እምነት ያለው ሰው ቀልቡ በአላህ ላይ ብቻ ይንጠለጠላል፡፡ እርሱን ብቻ ይጠይቃል፣ ከርሱ ብቻ ይፈልጋል፡፡ በሁሉም የህይወት ጉዳዩ የሚመካው በርሱ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡