መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት በአላህ አምላክነት ማመን

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እውነተኛ አምላክ ነው፤ ከእርሱም በቀር ሌሎች አማልክት ሁሉ ውሸት ናቸው። በዚህ ትምህርት ስለ አምላክነት አንድነት ትርጉም እና አስፈላጊነት ትማራለህ።

  • የአምላክነት አንድነት ትርጉም ማወቅ።
  • የአምላክነት አንድነት አስፈላጊነት ማወቅ።

በኃያሉ አላህ የማመን ትርጉም፡-

ግልፅም ሆነ ድብቅ የአምልኮ ዓይነቶች ሁሉ የሚገቡት ለኃያሉ አላህ ብቻ ነው ብሎ በቁርጠኝነት አምኖ መቀበል ማለት ነው፡ ሁሉንም የአምልኮ ዓይነቶች ለአላህ ብቻ እናውላለን፡፡ ዱዓእን፣ ፍራቻን፣ መመካትን፣ እርዳታ መፈለግን፣ ሶላትን፣ ዘካንና ፆምን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከአላደህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡፡ “አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እርሱ እጅግ በጣም ርኀሩኀ አዛኝ ነው፡፡” (አል-በቀራህ፡163)

አምላክ አንድ ብቻ መሆኑን አላህ ነግሮናል፡፡ ይህ ማለት የሚመለከው አንድ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ከአላህ ሌላ አምላክ ተደርጎ ሊይያዝ የሚገባው ነገር የለም፡፡ ከርሱ ውጭ ማንም አይመለክም፡፡

“አምላካችሁም አላህ ብቻ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለለ፤ሁሉንም ነገር በእውቀት ያከበባ ነው፡፡” (ጦሃ፡163)

በአላህ አምላክነት የማመን አስፈላጊነት፡-

በአላህ አምላክነት የማመን አስፈላጊነትን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ግልፅ ይሆናል፡-

1 ሰውም ሆነ ጋኔን የተፈጠረበት ዓላማ ነው፡፡

እነዚህ የተፈጠሩት አላህን በብቸኝነትና ያለምንም ተጋሪ ለመግገዛት ነው፡፡ አላህም እንዲህ ብሏል…«ጋኔንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡» (አል-ዛሪያት፡56)

2 የአላህ መልእክተኞች የተላኩት ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡

መለኮታዊ መፅሐፍት የወረዱት ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡ዓላማቸው በእውነት መመለክ የሚገባው አላህ መሆኑን ለማፅናት ሲሆን ከርሱ ውጭ በሚመለኩ ነገሮች ደግሞ ለመካድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል…“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል፤” (አል-ነሕል፡36)

3 እሱ በሰው ልጅ ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ነው፡፡

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሙዓዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን ለደዕዋህ በላኩት ጊዜ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነገር ነግረውት ነበር፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት… “የመፅሐፍቱ ባለቤት የሆኑ ህዝቦች ክርስቲያኖች /አይሁዶች/ ያጋጥሙሃል በመጀመሪያ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለከ አምላክ የለም ወደ ሚለው ቃል ጥራቸው፡፡” (አል-ቡኻሪ፡1389 ሙስሊም፡19) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ለማለት የፈለጉት “በሁሉም የአምልኮ ዓይነቶች አላህን ብቻ አምልኩ በላቸው፡፡” ለማለት ነው፡፡

4 “ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል ትክክለኛ ትርጉም፥ በአላሀ አምላክነት ማመን ነው፡፡

አምላክ ማለት የሚመለክ ማለት ነው፡፡ ከአላህ በቀር በዕውነት የሚመለክ የለም፡፡ ማንኛውም የአምልኮ ዓይነት ከርሱ ውጭ ለማንም አናውልም፡፡

5 በአላህ አምላክነት ማመን፣ አዕምሮ የሚመራው አሳማኝ የሆነ፣ አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ፣ ባለቤትና አዘጋጅ ነው ብሎ የማመን ውጤት ነው፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር