መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የኡምራ አደራረግ

ዑምራ ታላቅ ኢባዳ ነው፡ ለሱም ሙእሚን ወደ ተከበረው ቤት የሚሄድ ሲሆን በመስራትም ታላቅ ምንዳን ያገኛል። በዚህ ትምህርት ስለ ትርጉሙ, ስለ ትሩፋቱ እና አደራረጉ ትማራለህ።

  • ስለ ዑምራ ትርጉም፣ ፍርዶቹና ትሩፋቶቹን ማወቅ።
  • ስለ ዑምራ አደራረግ ማወቅ።

የዑምራ ትርጉም

ዑምራ፣ የኢሕራም ልብስ በመልበስ በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ በመዞር፣ በሠፋና መርዋ መሐከል ሰባት ጊዜ በመመላለስ እና ከዚያም ጸጉርን በመላጨት ወይም በማሳጠር የሚጠናቀቅ የአምልኮ ተግባር ነው፡፡

የዑምራ ብያኔ

ኡምራ ማድረግ በሚችል ሰው ላይ በዕድሜ አንድ ጊዜ መስራቱ ግዴታ ነው፡፡ ደጋግሞ መስራቱ ይወደዳል፡፡

ኃያሉ አላህ እንዲህ አለ፡- "ሐጅና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ" (አል በቀራህ 196)።

ከዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዳስተላለፈችው፡- “የአላህ መልእክተኛ ሆይ በሴቶች ላይ ጂሃድ አለ ወይ?" ብዬ ጠየኳቸው እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- “አዎ ውጊያ የሌለበት ጂሃድ አለባቸው እሱም፣ ሐጅንና ዑምራ ነው።” (አህመድ 25322 እና ኢብኑ ማጃህ 2901)።

የኡምራ ትሩፋት

١
በአቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ከዑምራ እስከ ዑምራ በመካከላቸው ላለው ማበሻ ነው፣ ተቀባይነት ያለው ሐጅ ደግሞ ከጀነት በስተቀር ምንዳ የለውም። ” በማለት ተናግሯል። (አል-ቡኻሪ 1773 እና ሙስሊም 1349)።
٢
ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ሀጅና ዑምራን ቀጥሉ፤ ምክንያቱም ድህነትንና ኃጢአትን ያስወግዳሉ። ልክ እቶን ከብረት ብክለትን እንደምያስወግድ።” (አል-ነሳኢይ 2630)

የዑምራ ጊዜ

ጊዜው፡ ዓመቱን ሙሉ ዑምራ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በረመዳን ወር ውስጥ የሚደረግ ዑምራ እጥፍ ድርብ የሆነ ምንዳ አለው፣ ከሀጅ ጋር እኩል ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በረመዳን ውስጥ የሚደረግ ዑምራ (በምንዳ) ከሐጅ ጋር ይስተካከላል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1863/ሙስሊም 1256)

የዑምራ አፈፃፀም

١
ኢህራም(ኒያ)
٢
ጦዋፍ ከእባን ሰባት ጊዜ መዞር
٣
ሰዒይ በሶፈና በመርዋ መካከል ሰባት ጊዜ ምልልስ ማድረግ
٤
የራስ ፀጉር መለጨት ወይም ማሳጠር

1 ኛ (እህራም)

ዑምራን ኒያ ማድረግ የፈለጋ ሰው መደበኛ ልብሱን አውልቆ እህራም መልበስ፣ ገላዉን መታጠብ፣ ራሱን ና ፂሙን ሽቶ መቀባት ያስፈልገዋል።

ከዚያም ግዜው ፈርድ ሶላት ከሆነ ሚቃት ላይ ይሰግዳል፤ አለበለዚያ ሁለት ረከዓ ይሰግዳል፡ ሶላትንም እንደጨረሰ ይሀርማል፤ በበልቡ ወደ ኡምራ ማግባትን ያስባል፤ ከዚያም እንዲህ ይላል፡- "ለቤይከ አላሁመ ኡምረተን"(አላህ ሆይ በኡምራ አቤት ብያለሁ)።

-

ሁለተኛ ጠዋፍ

ወደ ተከበረው መስጂድ ሲገባ ቀኝ እግሩን እያስቀደማ መስጂድ የመግባትን ዝክር ይናገራል። ካዕባ ላይ ሲደርስ መዞር ከመጀመሩ በፊት ተልቢያ ማለቱን ያቆማል። እድጥባእ እንድያደርግ ይመከራል። ይህም የልብሱን መሃከል በቀኝ እጁ ብብት ስር እና ሁለቱን ጫፎች በግራ ትከሻው ላይ ማድረግ ነው።

ጦዋፍ የሚጀምረው ከጥቁር ድንጋይ ነው።

ከዚያም ጦዋፉን ሊጀምር ወደ ጥቁር ድንጋይ ሄዶ ድንጋዩን በቀኝ እጁ ይሰላመትና ይስማል፤ ካልቻለም ድንጋዩን ፊት ለፊት በመጋፈጥ በእጁ ይጥቁማል። ቤቱን በግራው ያደርጋል። በሰባት ዙር ይዞራል።, እና ወንዶች በመጀመሪያዎቹ ሶስት ዙሮች ውስጥ መለስተኛ ሩጫ ይሮጣሉ።

የየመን መእዘን ላይ ስደረሰ ሳይስም ይንካው፤ ካልቻለም አያመለክተው፤ በየመን መእዘንና በጥቁር ድንጋይ መካከል፡- “ጌታችን ሆይ በዱንያ ላይ መልካምን ነገር ስጠን። በመጨረሻይቱም ዓለም መልካም ነገር ስጠን፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን።"

-

ጥቁሩን ድንጋይ ባለፈ ቁጥር "አላሁ አክበር" እያለ በቀሪው የዙሪያው ወቅት ዚክር፣ ዱዓ እና ቁርኣን ማንበብ ይችላል።

የጦዋፍ ሶላት

የሰባት ዙሮችን ዙርያ ከጨረሰ በኋላ አንሶላውን በትክክል በሁላቱም ትከሻዎች ላይ ይለብሳል። ከዚያም ወደ መቃም ኢብራሂም ይጠጋል እና ከተቻለ ሁለት ረከዓን ከኋላው ይሰግዳል። ካልተመቸው በመስጂድ ውስጥ የትኛውም ቦታ ይሰግዳል፡ በመጀመርያው ከአል-ፋቲሃ በኋላቁል ያአዩሀልካፊሩን እና በሁለተኛውቁል ሁመላሁ አሀድ ያነባል።

ሶስተኛ ሰእይ

ከዚያም ወደ አል-መሳእ ይወጣል፤ ወደ አል-ሰፋ ሲቃረብ ይህንን አያ ይቀራል፡- “በእርግጥም አል-ሳፋ እና አል-መርዋህ ከአላህ ማምለክያ ምልክቶች መካከል ናቸው”። እንዲህም ይላል፡- አላህ በጀመረው እጀምራለሁ።

ከዚያም ወደ ሳፋ ይወጣል ወደ ካዕባ ፊቱን ያዞራል፣ እጆቹን ዘርግቶ አላህን ያመሰኛል፣ ዱዓ ያደርጋል። ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ዱዓዎች መካከል፡- لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير، لا إله إلا الله وحده، أنجز وعده، ونصر عبده، وهزم الأحزاب وحده" ከዚያም የፈለገውን ዱኣ ያደርጋል ይንን ሶስት ጊዜ ይደግማል።

-

ከዚያም ከአል-ሳፋ ወርዶ ወደ አል-መርዋ በማቅናት ከሁለቱ አርንጓዴ ማብራቶች ጋ ስደርሱ ወዶች በሀይለኛ ይሮጣሉ። ለሴት ግን በሁለቱ መብራቶች መካከል መፋጠን አይፈቀድላትም እንደ ጠቅላላው ሰኢይ በዝግታ ትሄዳለች።

-

ከዚያም አል-መርዋህ እስኪደርስ ድረስ መራመዱን ይቀጥላል፣ በሷ ላይ ይወጣል፤ ፊቱን ወደ ቅብላ ያዞራል፣ እጆቹን ወደ ላይ በማንሳት በአል-ሷፋ ላይ የተናገረውን ይደግማል፣ አንቀጹን አያነብም፣ አላህ በጀመረው እጀምራለሁም አይልም።

-

ከዚያም ከአል-መርዋህ ወርዶ ወደ አል-ሰፋ በማቅናት አርንጓዴ መብራት ጋር ትይዩ እስኪሆን ድረስ ይራመዳል እዚያ ስደርስ ይሮጣል። አል-ሶፋ ላይ በአል-መርዋ ላይ ያደረገውን ያደርጋል። እና ሰባት ዙር እስኪያጠናቅቅ ድረስ ይቀጥላል። ጉዞው አንድ መንገድ ነው፣ መመለሻውም አንድ መንገድ ነው፣ በሰእይ ጊዜ ብዙ ዝክርና ዱአእ ያድርግ፣ ከትንሹና ከትልቁ ሀደስ የጠራ ይሁን።

-

አራተኛ: ፀጉር መላጨት ወይም መቁረጥ

የዑምራ ተሳላሚው ሰኢዩን ከጨረሰ ከመስአው ወጥቶ ጻጉሩን ለመላጨት ወይም ለማሳጠር ይሄዳል እና መላጨት ይበልጣል።

አብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አላህ ሆይ ፀጉራቸውን ለሚላጩ እዘንላቸው። ጸጉራቸውን የሚቆርጡትስ የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉዋቸው፤“አላህ ሆይ ፀጉራቸውን ለሚላጩ እዘንላቸው።" "ጸጉራቸውን የሚቆርጡትስ የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉዋቸው፤ "የምያሳጥሩንም" አለ። (አል-ቡኻሪ 1727 እና ሙስሊም 1301)

ሴቲቱም ፀጉሯን ሰብስባ አንድ ሳንትሜትር ታሳጥራለች ኢህራም ላይ ያለ ሀጃጅ የተጠቀሰውን ቢያደርግ ዑምራው ተጠናቀቀ፤ እና በኢህራም ወቅት የተከለከለው ነገር ሁሉ ለሱ ተፈቅዶለታል።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር