የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ቅዱስ ቁርአን የማንበብ ህጎች እና አደቦች (ስነ-ስርአት)
ቁርአንን የመሐፈዝ (የመሸምደድ) ብያኔ
አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ቁርአንን የሚያነብ እና የሚሸመድድ ሰው ከተከበሩ እና ፃድቅ መላእክት ጋር ነው።›› (ቡኻሪ 4937)
ቁርአን የመቅራት (የማንበብ) ብያኔ
ቁርአንን ማንበብ እና እስከቻለው ድረስ ማድረግ ለሙስሊም ሰው የተወደደ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ! በእነዚያ የአሏህን መጽሐፍ የሚያነቡ ፣ ሶላትንም አስተካክለው የሚሰግዱ ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጥርም ሆነ በግልፅ የሚለግሱ በፍፁም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ።" (ሱረቱል ፋጢር 29)
የቁርአን ንባብን ማድመጥ እና ትኩረት መስጠት
ቁርአን ሲነበብ ሲሰሙ ማድመጥ እና ለእሱ ትኩረት መስጠት በሙስሊም ሰው ላይ ግዴታ ነው። በተለይ ደግሞ ሶላት እና በጁምአ ሁጥባ (ትምህርት) ውስጥ ሲሆን ማለት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ቁርአን በተነበበ ጊዜ እሱን አድምጡ። ፀጥም በሉ ይታዘንላችኋልና።" (ሱረቱል አዕራፍ 204)
ቁርአን በሌሎች ቦታዎች ላይ (ከሶላት እና ከጁምአ ሁጥባ ውጭ) በሚነበብ ጊዜ እሱን ማድመጥ እና ለእነሱ ትኩረት መስጠት የተወደደ ነው። ምክኒያቱም ለሃያሉ አሏህ ቃል ያለንን አክብሮት እና ትህትና መሳያ ስለሆነ ነው።
ሁሉም ሰው በቁርአን ማመን እና ህግጋቱን ማጥናት ፣ የተከለከሉትን መከልከል ፣ የታዘዙትን መታዘዝ እና በህግጋቱ መሰረት መስራት አለበት።
ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ተገቢ ንባብን ያነባሉ።›› (ሱረቱል በቀራ 121) ኢብን አባስ እና ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የተፈቀደውን ይፈቅዳል፤ የተከለከለውንም ይከለክላሉ። ከተከለከለውም ነገር አንድንም ነገር አይቀይሩም።›› (ተፍሲር ቢን ከሲር 1/403)
አቡዱሏህ ቢን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስር አንቀፆችን የምንማር ከሆነ በውስጡ ያለውን ነገር እስከምናውቅ ድረስ ከዚያ በኋላ የተገለጡትን (ራዕይ) እንማርም ነበር።›› (አል-ሐኪም 2047) ‹‹በውስጡ ያለውን ነገር›› የሚለው ንግግር ከሐዲስ ዘጋቢዎች አንዱ እንዳብራራው በውስጡ ሊተግባር ወይም ሊሰራበት የሚችል ስራን ማለቱ ነው።
አንድ ሙስሊም ሰው ቁርአንን በማንበብ ላይ መፅናትና መጠባበቅ አለበት። አንዲትም ቀን ከቁርአን የሆነ ነገር ሳያነብ ማሳለፍ የለበትም። እንዳይረሳው ወይም ደግሞ እንዳይተወው መጠንቀቅ አለበት። አሏህ እንዲህ አለ፡ "መልዕክተኛውም ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ ይህን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት አለ።" (ሱረቱል ፉርቃን 30)
አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዞ እንዳወራው እንዲህ አሉ፡ ‹‹ቁርአንን በማንበብ ላይ ፅኑ። ነፍሴ በእጁ በሆነው ይሁንብኝ፡ ከማሰሪያ ገመዷ ከተለቀቀች ግመል የበለጠ ቁርአን ይሸሻል (ይረሳልና) አሉ።›› (ቡኻሪ 5033)
ቅዱስ ቁርአንን የማንበብ ስነ-ስርአት
ቁርአንን ማንበብ ተቀባይነት እና ሽልማት ያለው እንዲሆን ልንከተላቸው የሚገቡ ስነ-ስርአተቶች አሉ። እነዚህ ስነ-ስርአቶች (አደቦች) ቁርአንን ከማንበባችን በፊት እና በምናነብበት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ናቸው።