የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ 2
በእስልምና መልዕክት መላካቸው
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ነብይነት መጀመሪያ የጀመረው በእውነተኛ ህልም ነው። በእንቅልፋቸው ህልም አያዩም እንደ ንጋት ጮራ (ብርሃን) ሆኖ የመጣ ቢሆን እንጅ። ይህ ከሆነ በኋላ ስድስት ወራት አለፉ፤ ከዚያም ወህዩ (ራዕ) መገለጥ ጀመረ።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እድሚያቸው ወደ አርባ በተቃረበ ጊዜ ከሰው መገለልው (ለብቻቸው) መሆን ይወዱ ነበር። የረነዷንን ወር በሂራ ዋሻ ውስጥ ብቻቸውን ሆነው አሏህን እየተገዙ ያሳልፉም ነበር። ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ከሰው አግልለው በቆዩበት አመት የመጀመሪያው የራዕይ መገለጥ እስተቀበሉበት ጊዜ ድረስ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቆዩ።
አርባ አመት በሞላቸው ጊዜ የነብይነት ብርሃን አካበባቸው። ሃያሉ አሏህ ለፍጡራኖቹ በላከው መልዕክት አከበራቸው። ይህ ክብር ለእሳቸው ነጥሎ ሰጣቸው፤ በእሱ እና በባሪያው መካከል ባላደራ አደረጋቸው። በጅብሪል (ዐ.ሰ) አማካኝነት ትዕዛዙን (መልዕክቱን) ለአለማት እዝነት ፣ ለሰዎች አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ ላካቸው።
ይህን ‹‹አንተ (ልብስ) ደራራቢው ሆይ! ተነስ አስጠንቅቅ።›› (ሙደሲር 1-2) የሚለውን የአሏህን ትዕዛዝ ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ ሰዎች አሏህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ እና አሏህ የላከውን ሃይማኖት እንዲቀበሉ ጠራቸው (አስተማራቸው)።
ሚስጥራዊ ዳዕዋ (ጥሪ)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ሰዎች የጥላቻ ተቃውሞ እንዳይገጥማቸው በማሰብ ወደ እስልምና በሚስጥር መጥራት ጀመሩ። እናም ለእሳቸው ቅርብ ለሆኑ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለጓደኞቻቸው ፣ መልካም ነገር ላዩባቸው እና እውነትንና መልካም ነገርን ይወዳሉ ላሏቸው ሰዎች እስልምናን አስተዋውቀዋል።
እስልምናን የተቀበለው የመጀመሪያው ሰው
እስልምናን በመጀመሪያ ደረጃ የተቀበሉት ሚስታቸው ኸድጃ ቢንት ኽወይሊድ (ረ.ዐ) ፣ ጓደኛቸው አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ) እና የአጎታቸው ልጅ አሊ ቢን አቢጧሊብ እና ነፃ ያወጡት ዘይድ ቢን ሐሪስ (ረ.ዐ) ናቸው።
በአደባባይ እንዲያስተምሩ ከሃያሉ አሏህ ትዕዛዝ መጣ ‹‹የታዘዝክበትን ነገር በይፋ ግለፅ።›› (ሱረቱል ሂጅር 94) የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ኢስላም ያደረጉት ጥሪ ተገለጠ፤ ሃያሉ አሏህ እንዳዘዛቸውም እውነቱን በግልጽ አወጁ።
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጥሪያቸውን ይፋ ባወጡ ጊዜ የቁረይሽ መሪዎች በጥላቻ ፊታቸውን ዘኦሩባቸው። ተቃውሟቸውንም በፌዝ ፣ በስላቅ ፣ በንቀት እና በክህደት የሞራላቸውን ጥንካሬ ሊያዳክሙ ሞከሩ ፣ የእስልምና ሃይማኖት አስተምህሮት ሊያንቋሽሹ ፣ ጥርጣሬን ሊያጭሩ ፣ የውሸት ወሬ በመንዛት ጥሪውን አስተባበሉ። እናም ጥሪያቸውን ከተው ጥቅማጥቅሞችን እንደሚሰጧቸው በመንገር ሊደራደሯቸው ፈለጉ።
ሙሽሪኮች እነዚህ የጥላቻ ሴራዎች እንዳልሰሩ ሲያውቁ እና ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) በጥሪያቸው መፅናታቸውን ባዩ ጊዜ እስልምናን ለመዋጋት ወሰኑ፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸውን ማሰቃየት እና ማሳደድ ጀመሩ። ሙሽሪኮች ያደርሱባቸው የነበርው ግፍ በበረታ ጊዜ ሶሃቦቻቸው ወደ ሀበሻ እንዲሰደዱ አዘዙ። የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ወንዶች እና ሴቶች ነብዩ ከተላኩ ከአምስት አመት በኋላ ተሰደዱ።
በዚህ ጊዜ የነበር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጥሪያቸው በስኬት እና በስደት መካከል ሆኖ እያለ ነው የኢስራዕ እና ሚዕራጅ ክስተት የተፈፀመው። ይህ ክስተት ከብዙ አመት ጥሪ ፣ ከሙሽሪኮች ጥቃት ፣ ክህደት እና መገፋት በመታገሳቸው ሊያፀናቸው እና ሊያከብራቸው የመጣ ነው።
ከመካ ውጭ ያደረጉት ዳዕዋ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ውጭ እስልምናን ለሰዎች ማስተዋወቅ ጀመሩ። እናም ለዚሁ አላማ ወደ ጧኢፍ ሄዱ። ከጧኢፍ ነዋሪዎች ተቃውሞ በገጠማቸው ጊዜ ወደ መካ ተመልሰው ለተለያዩጎሳዎች እና ለሐጅ ለሄዱ ሰዎች እስልምናን ማስተዋወቅ ቀጠሉ።
ሁላቱ የአቀባ የአብሮነት ቃልኪዳን
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተላኩ በአስራ አንደኛው አመት ላይ መዲና ብለው የሰየሟት የያነዋ ያስሪብ ከተማ ውስጥ ስድስት ሰዎችን አገኙ። እስልምናን አስተዋወቋቸው ፣ እውነቱን ገለፁላቸው ወደ አምልኮተ አሏህም ጠሯቸው። እናም ቁርአንን ካነበቡላቸው በኋላ እስልምናን ተቀበሉ። እነሱም ወደ መዲና ተመልሰው እስልምና በመካከላቸው እስኪስፋፋ ድረስ ህዝባቸውን ማስተማር ቀጠሉ። ከዚያ በአስራ ሁለተኛው አመት 1ኛ የአቀባ ቃልኪዳን ተፈፀመ። ሁለተኛው የአቀባ የአብሮነት ቃልኪዳን በ13ኛ አመት በሚስጥር ተፈፀመ።የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አብረዋቸው የነበሩትን ሙስሊሞች ሁሉ ወደ መዲና እንዲሰደዱ ባዘዙ ጊዜ በቡድን ሆነው ተጓዙ።
አብዘሃኛዎቹ ሙስሊሞች ከመካ ከተሰደዱ በኋላ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና አቡበክር (ረ.ዐ) ወደ መዲና ተሰደዱ። ነገርግን የሄዱት ቁረይሾችን አቅጣጫ ለማሳት በተቃራኒ አቅጣጫ ነበር። ከዚያም በሰውር ዋሻ ውስጥ ለሶስት ቀን ያህል ከቆዩ በኋላ የቀይባህር ዳርቻን ተረተራማ ቦታ ተከትለው በመሄድ ወደ መዲና አቀኑ። ከአጋራቸው ጋር በመዲና ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ሙስሊሞች በሚያስደንቅ ሃሴት እና ፈንጠዝያ በተሞላበት ሰልፍ በእልልታ ተቀበሏቸው።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ያደረጉት የመጀመሪያው ነገር የነብዩን መስጊድ መገንባት እና ሙሐጅሮችን (ስደተኞቹን) እና አንሷሮችን (የመዲና ደጋፊዎችን) በወዳጅነት ማስተሳሰር ነበር። ይህም ለአዲሱ እስላማዊ ማህበረሰብ ፅኑ መሰረት ጣለ።
ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ የእስልምና ህግጋት ልክ እንደ ዘካ ፣ ፆም ፣ ሐጅ ፣ ጅሃድ ፣ የሶላት ጥሪ ፣ በመልካም ማዘዝ እና ከክፉ ነገር መከልከል እና ሌሎች እስላማዊ ህግጋቶች መገለጣቸውን ቀጠሉ።
ሙስሊሞች ሃይማኖተራቸውን እንዲከላከሉ (እንዲከላከሉ) እና ዘላለማዊውን መልዕክት እንዲያስፋፉ ፈቃዱን አወረደላቸው (ገለጠላቸው)። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹እነዚያ በበደል የሚገደሉ ምዕመናን የተበደሉ በመሆናቸው መዋደቅ (መጋደል) ተፈቀደላቸው።›› (ሱረቱል ሐጅ 39) ለመፋለም (ለመዋደቅ) የተፈቀደበት የመጀመሪያው አንቀፅ ይህ ነው። ከዚያም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) 27 ወታደራዊ ዘመቻዎችን መርተዋል፤ ሃምሳ ስድስት ቡድኖችን አሰማርቷል።
ከሒጅራ (ከስደቱ) በኋላ የተከሰቱ ወሳኝ ክስተቶች
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ የተከሰቱ በጣም ወሳኝ ከስተቶች እንደሚከተለው እጥር ምጥን ባለመልኩ ቀርበዋል።
የሂጅራ የመጀመሪያው አመት
የሒጅራ ሁለተኛው አመት
የዘካ (ምፅዋት) ፣ ፆም እና አሏህ ለምዕመናን በቁረይሽ ከሃዲያን ላይ ድልን የተጎናፀፉበት ታላቁ የበድር ጦርነት የተደነገገበት ነው።
የሒጅራ ሶስተኛው አመት
የኡሁድ ጦርነት የተካሄደበት ጊዜ ሲሆን ቀስተኞች ምርኮ ለመሰብሰብ ብለው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ በመጣስ ከተራራው ወርደው ሽንፈትን ተከናንበዋል።
የሒጅራ አራተኛ አመት
የበኑ ነዲር አይሁዶች ከሙስሊሞች ጋር የነበራቸውን ስምምነት በመጣሳቸው ምክኒያት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያስወጧቸው መሆኑን ተከትሎ የበኑ ነዲር ጦርነት የተካሄደበት ነው።
የሒጅራ አምስተኛ አመት
የበኒ ሙስጦሊቅ ጦርነት ፣ የዐህዛብ ጦርነት እና የበኒ ቁረይዛ ጦርነት የተካሄደበት ጊዜ ነው።
የሁደይቢያ የሰላም ስምምነት በሙስሊሞች እና በቁረይሾች መካከል የጠካሄደበት ነው።
የሁደይቢያ የሰላም ስምምነት በሙስሊሞች እና በቁረይሾች መካከል የጠካሄደበት ነው።
የሒጅራ ሰባተኛው አመት
የኸይበር ጦርነት የተካሄደበት እና የዐሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እና ሙስሊሞች መካ ገብተው ኡምራ ቀዳ ያደረጉበት አመት ነው።
የሒጅራ ስምንተኛ አመት
በሙስሊሞች እና በሮሞች መካከል ሙዕጣህ ጦርነት የተካሄደበት ፣ መካን ድል ያደረጉበት እና በሐውዚን እና ሰቂፍ ጎሳዎች ላይ የሁነይን ጦርነት የተካሄደበት አመት ነው።
የሒጅራ ዘጠንኛው አመት
የተቡክ ጦርነት የመጨረሻው ጦርነት የተካሄደበት ነው። ይህዝብ እንደራሴዎች (ተወካዮች) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመጡበት እና ብዙ ሰዎች በገፍ (በብዛት) ወደ አሏህ ሃይማኖት የገቡበት አመት ነው። ይህ አመት የእንደራሴዎች አመት ተብሎ ይጠራል።
የሂጅራ አስረኛው አመት
ሐጀተል ወዳዕ (የስንብት በሐጅ)አንድ መቶ ሽህ የሚበልጡ ሙስሊሞች ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሐጅ ያደረጉበት አመት ነው።
ጥሪው (ዳዕዋው) ሙሉ በሙሉ በተፈፀመበት ጊዜ ፣ በአረብ ባህረሰላጤ በሙሉ እስልምና ተስፋፋ ፣ ሰዎች ወደ እስልምና በገፍ (በጣም በብዛት) ገቡ፤ በአለም ዙሪያ እንደራሴዎች (መልዕክተኞች) ተላኩ። እስልመና ከሌሎች ሃይማኖቶች የበለጠ ተቀባይነት አገኘ። ይህኔ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ፍፃሚያቸው (ሞታቸው) መቃረቡ ተሰማቸው።ከዚያም ጌታቸውን ለመገናኘት ዝግጅት ጀመሩ። ንግግራቸው እና ስራቸው ከዚች ጠፊ አለም መለየታቸው የማይቀር መሆኑን ያመላክት ነበር።
በአስራ አንደኛው የስደት አመት በ12ኛው ረቢኡል አወል ወር ሰኞ ቀን የአሏህ መልዕክተኛ ይችን አለም ተለዩ።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በስልሳ ሶስት አመታቸው ነው። አርባ አመት ነብይ ከመሆናቸው በፊት እና ሃያ ሶስት አመት አስራ ሶስቱን መካ ውስጥ እና አስሩን መዲና ውስጥ ነብይ እና መልዕክተኛ ሆነው ኖረዋል።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞተዋል ነገርግን ሃይማኖቱ ዘላቂ (ዘላለማዊ) ነው። እሳቸው ሞተዋል፤ ይሁን እንጅ መልካም ነገርን አልተውም (አላስቀሩም) ህዝባቸውን ወደ እሱ ያመላከቱ ኒሆን እጅ። እንዲሁም ክፍን (መጥፎ) ነገር አልተውም ከእሱ ያስጠነቀቁ ቢሆን እንጅ። ወደ መልካም ነገር ያመላከቱት አሃዳዊነትን ፣ አሏህ የሚወደውን እና የሚደሰትበት ነገር ሁሉ ነው። ከክፉ ነገር ያስጠነቀቁት ደግሞ ሽርክ (በአሏህ ላይ ማጋራት) እና አሏህ የሚጠላው እና የማይቀበለው ነገርን በሙሉ ነው።