የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ሰው እንዴት ወደ እስልምና ይገባል?
እነኚህ ሁለት የእምነት የምስክርነት ቃሎች የሚከተሉት ናቸው፡
የሰው ልጅ፣ ወደ ኢስላም የገባበት ቅጽበት በሕይወቱ ውስጥ ከባድ ቦታ ያለው አጋጣሚ ነው፡፡ እውነተኛው ልደቱ ያ ነው፡፡ በሕይወት የመገኘቱን ሚስጥር የሚረዳው ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ሃይማኖት ውስጥ ከመግባቱ ጋር ተያይዞ ሰውነቱን በጠቅላላ በውሃ መታጠብ ይኖርበታል፡፡ ውስጡን ከማጋራትና ከወንጀሎች እንዳጠራና እንዳጸዳ ሁሉ ላዩንም በውሃ በመታጠብ ቢያጸዳ ይወደድለታል፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ከዐረብ መኳንንት መካከል የነበረን ሠሐብይ ወደ ኢስላም ለመግባት በፈለገ ጊዜ ሰውነቱን እንዲታጠብ አዘውት ነበር፡፡ (አል በይሃቂ 837)
በዚህ መልክ የተገለፀ ሰው፣ ይህችን ንሠሐውን በመጠበቅ ላይ ከፍተኛ ጉጉት ሊያድርበት ይገባል፡፡ በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ እንዳይገባና ወደ ኋላ እንዳያፈገፍግም የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ንሠሐውን መጠበቅ አለበት፡፡
አንድ ሰው ሁለቱን የእምነት የምስክርነት ቃል ትርጉማቸውን አውቆ፣ በልቦናውም እርግጠኛ ሆኖ፣ በምላሱ በመናዘዝ ወደ ኢስላም ይገባል፡፡
ንሠሐ
የንስሐ ትክክለኛነት ቅድምያ ሁኔታዎች፡-
ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚረዱ እርምጃዎች፡
ከንሠሐ በኋላስ?
አንድ ሙስሊም ትክክለኛ ንሠሐ ከገባ በኋላ ወንጀል የሌለበት ንጹሕ ይሆናል፡፡ ከዚህም አልፎ፣ አላህ (ሱ.ወ) እውነተኛ ተጸጻች የሆነን፣ በትክክል መቆጨትን የተቆጨን ንሠሐ አድራጊ ለየት ባለ ታላቅ ካሳ ይክሰዋል፡፡ መጥፎ ሥራዎቹን በበጎ ይቀይርለታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፤ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፤ አላህም እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው፡፡›› (አል ፉርቃን 70)
ውዴታው ከማንም በላይ ለአላህና ለመልክተኛው የሆነለት ሰው፣ ሌሎችን የሚወደው ለአላህና ለሃይማኖታቸው ለኢስላም ባላቸው ቀረቤታ ልክ የሆነ፤ወደነበረበት የክህደትና የማጋራት እንዲሁም የጥመት መንገድ መመለስን ልክ በእሳት መቃጠልን እንደሚጠላ ያክል የጠላ፤ በዚህን ጊዜ በልቡ ውስጥ የኢማንን ጣዕምና ጥፍጥና ያገኛል፡፡ ይህም ከአላህ በሚያገኘው ማበረታቻና እርጋታ፣ በአላህ ድንጋጌዎች በመርካትና በመደሰት፣ እንዲሁም ለቀጥተኛው ጎዳና መመራት ጸጋ ይረጋገጣል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሦስት ነገሮችን በውስጡ ያገኘ ሰው፣ በነርሱ ሰበብ የኢማንን ጣዕም ያገኛል፤ አላህና መልክተኛው ከነርሱ ሌላ ካለ አካል ሁሉ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መሆናቸውን፤ አንድን ሰው ለአላህ ብሎ እንጂ ለሌላ ነገር አለመውደድን፤ አላህ ከርሱ ከገላገለው በኋላ ወደ ክህደት መመለስን ልክ እሳት ውስጥ መወርወርን እንደሚጠላ መጥላትን (በልቡ ውስጥ ያገኘ ሰው፡፡) ›› (አል ቡኻሪ 21 / ሙስሊም 43)
ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝና ለሚያጋጥሙ ችግሮች ታጋሽ መሆን
አንድ ሙስሊም ኢስላምን ከተቀበለ በኋላ በሚያጋጥመው ችግርና መከራ ማዘን የለበትም፡፡ ለችግርና ለመከራ መጋለጥ የአላህ ተፈጥሯዊ ሕግ ነው፡፡ ከኛ በላጭና ታላቅ የነበሩት መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ብርቱ ችግርና መከራ ደርሶባቸው ታግሰዋል፤ ታግለዋል፡፡ የአላህን ነብያት ብንመለከት፣ አላህ ታሪካቸውን ተርኮልናል፤ በምን መልኩ እንደተንገላቱና እንደተሰቃዩ ነግሮናል፤ ከጠላት በፊት የዘመድና የጓደኛ ጥቃት እንደደረሰባቸው ገልጾልናል፤ ሆኖም በአላህ መንገድ ላይ በገጠማቸው ነገር ምንም አልተዳከሙም፤ የነበራቸውን አቋምና እምነት አልቀየሩም አልለወጡም፡፡ ስለዚህ ይህ በአንተም ላይ የደረሰብህ ችግር፣ እምነትህ እውነተኛ፣ እርግጠኛነትህም ጠንካራ በመሆኑ ከአላህ የሆነ ፈተና ነው፡፡ እናም በፈተናው ልክ አንተም በርታ! ይህን ሃይማኖትህን አጥብቀህ ያዝ፤ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዱዓቸው ላይ በብዛት ይደጋግሙ እንደነበረው አንተም አላህን ለምነው፡ ‹‹አንተ ልብን ገለባባጭ የሆንክ ጌታ ሆይ! ልቤን በእምነትህ ላይ አጽናልኝ፡፡›› በል፡፡ (አል ቲርሚዚ 2140)