መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ሽርክና

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ሽርክና ሃሳብ እና በሸሪአ ህግ ውስጥ ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ አህካሞችን ትማራላችሁ።

1 በእስልምና ህግ ውስጥ ሽርክና ምን ማለት እንደሆነ ትማራላችሁ።2 የሽርክና አይነቶችን ትማራላችሁ።3 የውል ክፍሎችን ትማራላችሁ።4 ሽርክናን በተመለከተ የተወሰኑትን የሸሪአ ብያኔዎች ትማራላችሁ።

የሽርክና ትርጉም

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች መካከል ንብረትን የመሸጥ ወይም የማስተዳደር ውል ነው። ለምሳሌ የመጀመሪያው ሁለት ሰዎች በውርስ ወይም በስጦታ የሚጓደኑበት ሲሆን ለሁለተኛው ምሳሌ ደግሞ ሁለት ሰዎች በሽያጭ እና በግዥ የሚጓደኑበት ነው።

ከሽርክና ጋር የተያያዙ ብያኔዎች

ሽርክና የተፈቀደ ነው። በእርግጥ የአሏህ አገልጋዮች መተዳደሪያ ገቢያቸው ይከስቡ ዘንድ ለማመቻቸት አሏህ ማንኛውንም ግብይት ፈቅዷል። ሽርከኛው ሙስሊም ሆነም ካፊር ሽርክና የተፈቀደ ነው። ሙስሊም ያልሆነ ሰው ከሙስሊም ውጭ እሰራለሁ ብሎ እስካላለ ድረስ በሽርክና መሳተፍ ይፈቀድለታል።

የሽርክና መፈቀድ ጥበብ

የሰው ልጅ በተፈጥሮው ገንዘቡ እንዲጨምርለት ይፈልጋል። አንዳንዴ በችሎታ ወይም ልምድ እጥረት እና በመነሻ ገንዘብ ማነስ ምክኒያት ብቻቸውን መስራት ላይችሉ ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ ማህበረሰቡ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ያስፈልጓቸዋል። ይሁን እንጅ አንድ ግለሰብ ብቻውን ላይወጣው ይችላል። ሽርክና ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ነው።

የሽርክና አይነቶች

١
1 የንብረት ሽርክና
٢
2 የውል ሽርክና

የንብረት ሽርክና ሁለት አይነት ነው

١
1 የፍላጎት ሽርክና
٢
2 አስገዳጅ ሽርክና

የፈቃደኝነት ሽርክና

ይህ ሽርክና በሁለት አጋሮች ድርጊት ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሪልስቴት ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ሲገዙ ባለቤት የሚሆኑት በንብረት ሽርክና አግባብ ነው።

አስገዳጅ ሽርክና

ይህ ሽርክና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ አጋሮች ያለነሱ ጥረት እና ስራ ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሁለት ግለሰቦች ንብረት ወርሰው በጋራ በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ባለቤት የሚሆኑት በንብረት ሽርክና አግባብ ነው።

በንብረት ሽርክና ውስጥ አጋሮቹ ንብረቱን የሚያስተዳድሩበት አግባብ

ሁለቱ አጋሮች እያንዳንዳቸው በባከለቤትነት ድርሻቸው ልክ እንግዳ የሆኑ ያህል ነው። ሆኖም አንዱ ያለ አንዱ ፈቃድ እንደ ፈለገ ሊሸጥ ወይም እንደ ፈለገ ሊያደርግ አይፈቀድለትም።

የውል ሽርክና

ልክ እንደ መሸጥ ፣ መግዛት ፣ ማከራየት እና በመሰል ሽያጮች ላይ የሚፈጠር ስብስብ ነው።

የውል ሽርክና ክፍሎች

١
የሙዳረባ ሽርክና
٢
የሞራል ዋስትና ሽርክና
٣
ሃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና
٤
የግል ሽርክና
٥
የወኪል ሽርክና

የሙዳረባ ሽርክና

ከሁለቱ አጋሮች አንደኛው ለሌላኛው አጋር የሚነግድበትን ገንዘብ የሚሰጥበት እና ከትርፉ በፐርሰንት እንደ ውላቸው ሩብ ወይም 1/3ኛውን ትርፍ የሚወስድበት ፣ ሌላኛው አጋር ደግሞ ቀሪውን ትርፍ ደግሞ የመነሻ ገንዘቡ ባለቤት የሚወስድበት የሽርክና አይነት ነው። ነጋዴው አጋር ቢጠፋበት ወይም ቢከስር ያገኝ ከነበረው የትርፍ ክፍፍል ተቀናንሶ ይሰጠዋል። ያለ አጋሩ ጥፋት መነሻ ካፒታሉ ቢጠፋ ነጋዴው ሽርከኛ (አጋር) ሊከፍለው የሚገባ ካሳ የለም። ነጋዴው አጋር ገንዘቡ በመሰብሰብ ሂደት አጠራቃሚ ፣ የሽርከኛው ወኪል ፣ የትርፍ ተካፋይ ነው።

የሞራል ዋስትና ሽርክና

ሁለት ሰዎች መነሻ ገንዘብ ሳይኖራቸው ሰዎች ዘንድ ያላቸውን ስም (ዝና) ተጠቅመው በብድር ገዝተው የሚሸጡበት የሽርክና አይነት ነው። ትርፉንም ኪሳራውንም የሚጋሩት እኩል ነው። ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱ አጋሮች እያንዳንዳቸው ለሚገዙት እና ለሚሸጡት ነገር ወኪሎች እና የሽርክና ባለድርሻ አካል ናቸው። ሽርክናው የሞራል ዋስትና አለበት። ምክኒያቱም ከሰዎች ዘንድ ጥሩ ስም (ዝና) ስላላቸው ብቻ በእዳ የሚገዙበት ነውና። ለሚታወቁና ለሚታመኑ ሰዎች ካልሆነ በቀር በዱቤ አይሸጡም።

ሃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና

ሁለት ሰዎች ምንም እንኳ ሚናቸው የተለያየ ቢሆንም ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን ተጠቅመው ሽርክናቸውን የሚያስቀጥሉበት ነው። መነሻ ካፒታሉም በግልፅ መታወቅ አለበት። ትርፍና ክሳራን በውልና ስምምነት መሰረት ይጋራሉ

የስራ ሽርክና

ሁለት አጋሮች ጉልበታቸውን ተጠቅመው ስራን በጋራ የሚሰሩበት ነው። ይህም ንግድ ወይም ሙያ ነክ ነገር ለምሳሌ ብረት አንጥረኛ (ብረት ቀጥቃጭ) ፣ አናፂ ፣ ግንበኛ እና ሌላ የተፈቀደ ስራ ልክ እንደ እንጨት ቆራጭ እና ጠራቢ ፣ መኖ ሰብሳቢ ስራ ላይ ሊሰማሩ ይችላሉ። ትርፍንም በተስማሙበት መሰረት ይከፋፍላሉ።

የወኪል ሽርክና

እያንዳንዱ አጋር የሽርክናውን የገንዘብ እና የአካል ስራ እንዲያስፈፅም ሃላፊነት ይሰጣጣሉ። ሆኖም እያንዳንዱ አጋር በነፃነት ስራውን ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ፣ ለሽያጭ ፣ ለግዥ ደረሰኝ ለመቀበል ፣ ዋስ ለመሆን ፣ ለመበደር እና ሎሎች በንግድ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለማስፈፀም መብት ያገኛል።

አንደኛው አጋር ሌላኛው አጋር የሚሰራውን ስራ መስራት አለበት። የሽርክናው ካፒታል አጋሮቹ በተስማሙበት ውል ላይ የተመሰረተ ነው። እንዲሁም ትርፉን የሚከፋፈሉት በተስማሙበት መሰረት ሲሆን ኪሳራውም በሽርክናው ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው እንደየ ድርሻቸው ይጋራሉ። ይህ አይነቱ ሽርክና የተፈቀደ ነው። ከላይ የተገለፁትን አራት የሽርክና አይነቶች አጣምሮ ይይዛል። ሁሉም የተፈቀዱ ናቸው። ምክኒያቱም መተዳደሪያ ገቢ በማግኘት ፣ የሰዎችን ፍላጎት በማሟላት እና ፍትህን በማስፈን መተባበር ነውና።

የሽርክና ጥቅሞች

1 ሃብት የሚያፈሩበት ፣ ስራ አጦች የሚቀጠሩበት ፣ ማህበረሰቡ የሚጠቀሙበት ፣ ገቢያቸውን የሚያሰፉበት እና ፍትህ የሚያሰፍንበት ጥሩ መንገድ ነው።

2 ካልተፈቀዱ የገቢ ምንጮች ለምሳሌ አራጣ ፣ ቁማር ወ.ዘ.ተ ገቢ ሳያገኙ ለሌላ ዘርፍ ተሰማርተው ገቢ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

3 የተፈቀዱ የገቢ ማግኛ እድሎችን ያሰፋል። እስልምና አንድ ሰው ብቻውን ሰርቶ ወይም ሌሎች ሰዎች ጋር ሽርክና ፈጥሮ ገቢ እንዲያገኝ ይፈቅዳል።

የሽርክና ውል እንዲቋረጥ የሚያደርጉ ነገሮች

١
1 ሽርክናው በአንድ ወይም በሁለት አጋሮች መቋረጥ (መፍረስ)
٢
2 ከሁለቱ አጋሮች ውስጥ አንዱ ካበደ
٣
2 ከሁለቱ አጋሮች ውስጥ አንዱ ካበደ
٤
3 ከሁለቱ አጋሮች ውስጥ አንዱ ከጠፋ እና ለረዥም ጊዜ ጠፍቶ ከቆየ። ምክኒያቱም ያ ልክ እደ ሞት ነውና።

የሽርክና ምሰሶዎች

١
1 ቢያንስ ሁለት አጋሮች መሆን
٢
2 ከገንዘብ ፣ ከስራ ወይም ከሁለቱም ጋር በተያያዘ የውል ስምምነት መኖር
٣
3 በሽርክናው ደንብ መሰረት አባል ለመሆን እና የአባልነት ጥያቄን ለመቀበል ፎርም ያለው መሆን

የሽርክና ቅድመ ሁኔታዎች

١
1 የሚያስፈልገው ካፒታል (የመነሻ ገንዘብ) እና የሰው ሃይል በእያንዳንዱ አባል መታወቅ አለበት፡፡
٢
2 እያዳንዱ አጋር በፐርሰነት ወይም ግማሽ ፣ ሩብ ፣ 1/3ኛ የሚል ክፍልፋይን በመጠቀም ከትርፉ የሚገኘውን ማወቅ አለበት። በእርግጥ የትርፍ ክፍፍል አሰራሩ ግልፅ ካልሆነ ተቀባይነት የለውም። ምክኒያቱም አንዳንዱ የሚጠቀምበት አንዳንዱ ደግሞ የሚጎዳበት መሆን የለበትምና።
٣
3 የሽርክና ስራው በሸሪአ ውስጥ በተፈቀዱ የስራ ዘርፎች ላይ መሆን አለበት። አንድ ሙስሊም ሰው በተከለከሉ ነገሮች ላይ መሳተፍ እና ሽርክና መፍጠር የለበትም። ለምሳሌ የትንባሆ (የሲጋራ) የእፅ ፣ የአስካሪ መጠጥ ምርት ወይም ደግሞ ቁማር ቤት ፣ የሙዚቃ እና የፊልም ስራዎች ፣ የወለድ ባንኮች እንዲሁም አሏህና መልዕክተኛው የከለከሉት ሌሎች መሰል ነገሮች ናቸው።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር