መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ሴቶች እና ወቅታዊ ጥሪዎች

በዚህ ትምህርት ውስጥ የሴቶችን ጉዳይ የተመለከቱ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ ወቅታዊ እምነቶች ፣ መርሆዎች እና ጥሪዎች ትማራላችሁ።

የትምህርቱ አላማ1 ከሴቶች ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሸሪአን ፍትህ እና ጥበብ ማሳየት2 የሴቶች ጉዳይ ላይ ተፅዕኖ እያሳደሩ ያሉ ወሳኝ ወቅታዊ መርሆዎች እና ሃሳቦች ማሳወቅ3 ከሴቶች ጉዳይ ጋር በተያዘ ያፈነገጡ ጥሪዎችን ህፀፅ (እንከኖች) ማብራራት

.በድሮ ጊዜ እና በጥንት የሰው ልጅ ስልጣኔዎች ውስጥ ሴቶች ምንም አይነት የሰውነት ክብር እነኳ አይሰጣቸውም ነበር። ይልቁንም ችላ የተባሉ እና ለምንም ነገር ግምት የማይሰጣቸው ነበሩ። ምንም አይነት መብት እና ለምንም ነገር ብቁነት የላቸውም ናቸው ተብሎ ይታመን ነበር። የሰው ልጅ መሆናቸው ተረስቶ እንደማንኛውም ነገር ይሸጡ ይለወጡ ነበር። በደረጃ ከወንዶችም ያነሱ ፍጡሮች እንደሆኑ ይታመን ነበር።

.ይህ አይነቱ አካሄድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተለያዩ ስልጣኔዎች እና ባህሎች ውስጥ የሴትልጅ ሚና ዝቅ አድርጎ የሚመለከት እና የሚንቅ እና የሚያንቋሽሽ መሆኑን ቀጠለ። ምንም እንኳ የምዕራቡ አለም በኋላ ላይ ለውጥ ቢያመጣም፤ ከኢንፓየር ግዛቶች እና ከቤተክርስቲያናት የጭቆና ቀንበር የተላቀቀ የሚመስል የነፃነት ጭላንጭል ታየ። ይህ ለውጥ ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለሴቶች እና ለጉዳዮቻቸው አልደረሰም ነበር።

.ይህ የተዛባ አመለካከት በሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመሰረተ ነው።

.የመጀመሪያው፡ የፍልስፍና ገፅታ

.በድሮ ጊዜ ፈላስፎች ሴቶችን ይንቃሉ፤ ያንቋሽሻሉ። በእነሱ ውስጥ ክብር ወይም መብት ብሎ ነገር አይታያቸውም። ከነዚህ ፈላስፎች ውስጥ ሶቅራጥስ ፣ ፕላቶ እና አርስቶትል ይገኙበታል።

ሁለተኛው፡ ሃይማኖታዊ ገፅታ

በሒንዱይዝም አንዲት ሴት ከወላጆቿ የመውረስ መብት የላትም። ባሏ ቀድሟት ቢሞት ከእሱ ጋር አብራ ተቃጥላ እንድትሞት ትገደዳለች። ምክኒያቱም ከእሱ በኋላ አለመኖር ለእሷ የተሻለ ነው ተብሎ ይታሰባልና። በአይሁዶችን እና በክርስቲያኖች እምነት ደግሞ ሴቶች ያላቸው ክብር ዝቅ ያለ ነው። የክፋት ፣ የሃጢያት እና የብልግና ሁሉ መሰረት ተደርገውም ይከሰሳሉ። እንደ እርኩስ እና እንደ ቆሻሻ ተደርገውም ይቆጠራሉ። እነዚህ ሃሳቦች የመጡት ከተዛቡ እና ከተንሻፈፉ መጽሐፍቶቻቸው ፣ ከሃይማኖታቸው እና ከጉባኤዎቻቸው ማደማደሚ ሃሳቦች የመጡ ሲሆን በቀሳቅስቶች እና በቤተክርስቲያኗ የተደገፉ ናቸው።

ከሴቶች ጋር በተያያዘ በዚህ ሰለጠነ በሚባለው ዘመን የብዙሃኑን ማህበረሰቦች ሃሳብ ፣ አመለካከቶች እና ባህሪያት ላይ ተፅእኖ ያደረሰ እና ተፅእኖ ማድረሳቸውን የቀጠሉ እምነቶች ፣ ሃሳቦች እና ፅንሰ ሃሳቦች (ቲዎሪዎች) ብቅ ብለዋል።

1 ዘመናዊነት እና ድህረ ዘመናዊነት

ዘመናዊነት የሰውን ልጅ የፍጥረተ አለሙ ሁሉ ማዕከል ያደርጋል። ከመለኮታዊ ራዕይ እራሱን ነፃ እንደሚያደርገው ፣ እሱ እራሱ ሃይል እንዳለው እና አዕምሮው ስለ አካባቢው እና ስለ ፍጥረተአለሙ ማብራሪያ እንደሚሰጠው ያስረዳሉ። አብዛሃኛው ሃሳቦች እና ተረድኦዎች ከዘመናዊነት ፅንሰ ሃሳብ የመነጩ ናቸው።

2 ምክኒያታዊነት

ይህ አዕምሮን እና ደረጃዎቹን ከፍ አድርጎ የመምረጥ እና የሚያሞግስ ነው። እንደነሱ ገለፃ የሰውን ልጅ የፍጥረተ አለሙ ማዕከል እንደሆነ ያስባሉ።

3 ነፃነት እና ግለኝነት

የሰው ልጅ ጉዳዮችን እና ለእሱ ተስማሚ በሆነ መንገድ እጣፈንታውን ይወስናል ብሎ በማሰብ ለሰብአዊ መብት አፅንኦት መስጠት ማለት ነው።

4 ዳርዊኒዝም

የሰው ልጅ አፈጣጠር መነሻን በተመለከተ ከብዙ ሚልዮን አመት በፊት አንስቶ አሁን ያለበትን ቅርፅ እስኪያገኝ ድረስ ያለው የሰው ልጅ እድገት የዝግመተ ለውጥ ሂደት እንደሆነ የሚናገር ፅንሰ ሃሳብ (ንድፈ ሃሳብ) ነው።

5 የሴቶች ነፃነት

የሴቶች ነፃነት ሃሳብ በከፋ ጭቆና እና በደል ይሰቃዩ ከነበረበት አውሮፓ ብቅ አለ። የነፃነት እና የፍትህ መፈክሮች ከፍ ብለው ተውለበለቡ። ይህን ተከትሎ ሴቶች ሰብአዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ፓለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ መብቶች ተሰጣቸው። ነገርግን ፍላጎቶቻቸው ሃይማኖታዊ ድጋፍ እና መዋቅር አልነበረውም እና በድጋሚ ከሃይማኖት እና ከቀኖናዎቹ ነፃ እንዲወጡ ጥሪያቸውን ወደዚያ አዞሩ። ይህ ሁሉ ከወንዶች የበላይነት ነፃ እንሆናለን በሚል ሰበብ እና ሽፋን ነበር።

ሴኩላሪዝም እና የሴቶች ነፃነት

ከሴቶች ነፃነት ሃሳብ እና ጥሪ ጋር የተያያዘው ሃይማኖትን ከሁሉም የህይወት ጉዳዮች መነጠል እና ሴኩላሪዝምን እንደ አንድ የሕይወት መንገድ መተግበር ነው። በተለይ ደግሞ ሃይማኖታዊ ቁጥጥሮችን እና አስተምህሮቶችን ማለት ነው።

6 ሴኩላሪዝም

የህይወት አስተዳደር ጉዳዮች ጋር የተያያዙትን ሁሉ ከሃይማኖት መነጠል (መለየት) ማለት ነው። የሰው ልጅ በተለያዩ ዘርፎች የሚተገብራቸውን ሃሳቦች እንደ መነሻ በመውሰድ ሃይማኖት በየትኛውም የሰው ልጅ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ ማድረግ ነው። ለምሳሌ ፓለቲካ ፣ ምጣኔሃብት እና ማህበራዊ እና ሌሎች ጉዳዮችም።

7 የፆታ እኩልነት

ይህ ጥሪ መጀመሪያ ላይ መሰረት ያደረገው በወንዶች እና በሴቶች እኩል የመማር ፣ የመስራት ፣ የመደራጀት ፣ በፖለቲካ የመሳተፍ እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎች ላይ የተመሰረተ ነበር። በሴቶች ላይ የሚደርስ አድልኦ እና መድሎ ሁሉ እንዲጠፋ የሚጠይቅ ነው። ነገርግን የእኩልነት ጥያቄው (ጥሪው) ከመሰረታዊ አውዱ ወጥቶ ወንዶች እና ሴቶች ያሏችን ልዩነቶች ላይ የማይስማማ እና ሁለቱ ፆታዎች አንድ ናቸው የሚል አዝማሚያ ያለው ሆነ።

8 ፌሚኒዝም (የሴቶች እኩልነት ጠበቃ)

የሴቶች ነፃነት እና የፆታ እኩልነት ሃሳብ ‹‹የሴቶች እኩልነት ጠበቃ›› ወይም ፌሚኒዝም ተብሎ ይጠራል። ከዚህ መሰረታዊ ሃሳብ ብዙ ፓለቲካዊ ፣ ማህበራዊ እና ሌሎች ተግባራትን የሚፈፅሙ ንቅናቄዎች ተፈጥረዋል። የሴቶች እኩልነት ሃሳብን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እና ሃሳቦችን በማህበረሰቡ ውስጥ ለማስረፅ ሞክረዋል።

የሴቶች እኩልነት ሃሳብ መርሆዎች

١
ፍፁም ነፃነት ያለው ቤተሰብ ሳይሆን ግላዊነት ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ ሃሳብ ውስጥ ነው፡፡
٢
በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለፅ ማህበራዊ ፆታ የሚለውን ሃሳብ መቀበል እና የሴት እና የወንድ የሚል ሃሳብን ማግለል
٣
የሴትን ልጅ አካል ባለቤትነቱን ለእሷ መስጠት እና ያለማንም ተቆጣጣሪነት እና ያለ ገደብ የፈለገችውን እንድታደርግበት ሙሉ መብት መስጠት
٤
የአባውራ የበላይነትን ውድቅ በማድረግ አባት በቤተሰብ ውስጥ ያለውን ሚና ማጥፋት
٥
ተሟጋችነት፡ ከሴቶች መብት ጠበቃ ንቅናቄ ውስጥ ግብረሶዶማዊነት ፣ ፅንስ የማስወረድ ህጋዊነት ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚጻረሩ ሃሳቦች እና አለማቀፋዊ እና እምነታዊ እሴቶች የምንዱ ይገኙበታል።

የተባበሩት መንግስታት ስምምነት (CEDAW)

በ1979 ዓ.ል በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሴቶች ላይ የሚደርስ አድልኦ እና መድሎን ሁሉ ለማጥፋት በአለም አቀፍ ስምምነቱ ሐገራት እንዲያፀድቁላቸው እና ፖለቲካዊ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል። የሲዶ ስምምነት ይባላል

የስምምነቱ ይዘት

ስምምነቱ በሁሉም ዘርፍ ወንዶች እና ሴቶች ፍፁም እኩልነት እና አቻነት አላቸው የሚል ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ነው። ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊ እና የህግ ዘርፎች እና ሌሎች ዘርፎች ላይ አቻ እና ፍፁም እኩልነት አላቸው ብሎ ያምናል። ይህ መርህ ከነባራዊ እውነታው የተቃረነ ፣ ከሰማያዊ ህግ ጋር የተፃረረ ፣ ከቁርአን እና ከሱና ጋር ተቃራኒ የሆነ እና ጤናማ አዕምሮ የሚፈልገወ ያልሆነ ነው። ከቁርአን ጋር የሚቃረን የመሆኑ ማሳያ ተከታዩ የአሏህ ንግግር ነው። "ወንድ እንደ ሴት አይደለም።" (ሱረቱል ኢምራን 36) አሏህ እንዲህ አለ፡ "ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው።" (ሱረቱ ኒሳዕ 34) እንዲህ ከሚለውም የአሏህ ቃል ጋር ይቃረናል። "ወንዶች (ጣጣቸውን ስለሚሸከሙ) በእነሱ ላይ ብልጫ አላቸው።" (ሱረቱል በቀራ 228) ከሱና ጋር የሚቃረን መሆኑን የሚያመለክተን ደግሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው ነው ‹‹እያንዳንዳችሁ ለምትጠብቁት ነገር ሃላፊነት አለባችሁ። ወንድ በቤተሰቡ ውስጥ እረኛ ነው። በእነሱ ላይ (በቤተሰቦቹ) ሃላፊነት አለበት። ሴት በባሏ ቤት ውስጥ እረኛ ናት። በምትጠብቀው ነገር (በቤተሰቦቿ) ላይ ሃላፊነት አለባት።›› (ቡኻሪ 893 ፣ ሙስሊም 1829) ይህ ብዙ ማብራሪያ አይፈልግም፤ ምክኒያቱም ይህ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ልዩነቱ በችሎታ እና የህይወት ኡደት እንዲቀጥል በማድረግ ሂደት ውስጥ ልዩነት ይፈጥራልና ነው። የተሟላ እኩልነት እና አቻነትን ለማሳካት መሞከር ከወንዶች እና ከሴቶች አፈጣጠር ጋር የሚቃረን ነው።

የተባበሩት መንግስታት የCEDAW ስምምነት እና በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለ ጥላቻ

የተባበሩት መንግስታት ስምምነት እና የሴቶች መብት ተሟጋች ንቅናቄ የሚያሳየው በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው ግኑኝነት እንዲያበቃ የሚፈልጉት የፉክክር እና የታሪካዊ ግጭት መስተጋብር አካል እንደሆነ ነው። በወንዶች እና በሴቶች መካከል ፍፁም እኩልነት እንዲመጣ በማድረግ ይህ ባላንጣነት እንዲያበቃ ይፈልጋሉ። ለወንድ ልጅ ጥቅም የሆነ ሁሉ ለሴት ልጅ ጉዳት እንደሆነም ያስባሉ። በእርግጥ ይህ ጠባብ እይታ ነው። በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለው ግኑኝነት አንዱ አንዱን የሚተካበት ሳይሆን አንዱ ያንዱን ክፍተት የሚሞላበት ፣ ጥላቻ እና ፍክክር ሳይሆን ትብብር እና መደጋገፍ የሚሰፍንበት ነው። እያንዳንዳቸውም የየራሳቸው ሚና እና ተግባር አላቸው። ህይወትን ለማስቀጠል በስምምነት እና በመሸፋፈን መርህ በጋራ እውቀት ፣ ፍቅር እና መተዛዘን የሰውን ልጅ ዘር ያስቀጥላሉ። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ። ትተዋወቁም ዘንድ ጎሳዎች እና ነገዶች አደረግናችሁ። በእርግጥ ከእናንተ መካከል አሏህ ዘንድ በላጩ አሏህን ፈሪው ነው።" (ሱረቱል ኹጅራት 13) አሏህ እንዲህ አለ፡ "ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ ሚስቶችን ወደ እነሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ ፣ በመካከላችሁም ፍቅርን እና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶች ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ህዝቦች ተአምራቶች አሉ።" (ሱረቱ ሩም 21) ከዚህ በተጨማሪ በህይወት ውስጥ ሁለቱ ፆታዎች የሚጫወቱት ሚና መለያየት የሚያመለክተው ምንም አይነት በደል ፣ ኢፍትሃዊነት ሳይኖር መብቶቻቸው እና ሃላፊነቶቻቸው የተለያየ መሆኑን ነው፡፡ ሆኖም እያንዳንዱ ተጨማሪ ሃላፊነት በተጨማሪ መብቶች ይካካሳሉ።

በወንዶች እና በሴቶች መካከል እኩልነት እንዲኖር ሸሪአ ያስተምራልን?

ሸሪአ ወንዶች እና ሴቶች በሰውነታቸው እና በሞራል ልዕልናቸው ፣ በሃላፊነታቸው ፣ አደራን በመሸከም ፣ በዚህ አለም እና በመጭው አለም ህይወት ምንዳቸው ፣ ለእያንዳንዳቸው መብታቸው እንዲከበር ፣ የአምልኮ ስርአቶችን በመፈፀም ዙሪያ እኩል እንደሆኑ ይደነግጋል። እንደዚሁ ህጉ በመካከላቸው ያለውን አወንታዊ ልዩነትም ያረጋግጣል። ምክኒያቱም በአካላዊ እና በስነልቦናዊ ውቅራቸው ይለያያሉና። ለምሳሌ ሴቶች በአቋም ድክመት ምክኒያት ጅሐድ (ተጋድሎ) እንዲያደርጉ አይጠበቅባቸውም። እንዲሁም የወር አበባ ላይ እና የወሊድ ደም ላይ በሆኑ ጊዜ አይሰግዱም፤ አይፆሙም። ሃብታም እንኳ ብትሆን የቤት ወጭን መሸፈን አትገደድም። በተጨማሪ ሃላፊነቶች ተጨማሪ መብቶች ናቸው። የፍትህ ዋናው መሰረት ይህ ነው።

የሸሪአ የውርስ ፍትህ

በእስልምና ህግ መሰረት ሴቶች በውርስ የሚደርስባቸው ግፍ የለም። አንዳንዴ ከወንዱ ድርሻ አነስ ያለውን ትወስዳለች። አንዳንዴ እኩል እና ተመሳሳይ ድርሻ ትወስዳለች። አንዳንዴ ደግሞ ከእሱ ድርሻ በላይ የምትወርስበት እና እሱ ሳይወርስ እሷ የምትወርስበት ሁኔታ አለ። ይህ የአሏህ ድንጋጌ እና የዕውቀት ሰዎች ማብራሪያ መጽሐፍት ውስጥ በዝርዝር የተቀመጠ ነው።

ሸሪአ ለሴቶች የሰጠው ክብር መሳያዎች

ሴት ልጅ በሸሪአ የተጠበቀች እና የተከበረች ናት። በእርግጥ አሏህ እንዲህ አለ፡ "መጥፎ የሰራ ሰው ቢጤዋን (አምሳያዋን) እንጅ አይመነዳም። አማኝ ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎ (መልካም) ነገር የሰራ ሰው ጀነት ይገባል። በእሷ ውስጥም ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ።" (ሱረቱ ጋፊር 40) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በእርግጥ ሴቶች የወንዶች እህቶች ናቸው።›› (ትርሚዚ 11) ከዚህ በተጨማሪ ሴት ልጅ የፈለገ ሃብታም ብትሆን ወዳ እና ፈቅዳ ካልሆነ በቀር አንድ ብር ማውጣት አይጠበቅባትም። ይልቁንም የሴቷ ጠባቂ (አባቷ ወይም ባሏ) የመጠለያዋን ፣ የመጠቃቀሚያዋን እና ሌሎች ወጭዎቿን መሸፈን ይገደዳል። አባቷም ሆነ ባሏ እንኳ ቢሆኑ በእሷ ገንዘብ ላይ ተቆጣጣሪ የለባትም። ሴት ልጅ የመሸጥ ፣ የማጫረት ፣ የንግድ ሽርክና መፍጠር ፣ ዋስትና መስጠት እና መቀበል መብት አላት።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር