የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የልጆች መብት
አሏህ በወላጆች ልብ ውስጥ ዘርን የመተካት ፍላጎትን አድርጓል። ይህ ምኞት የአባታችን አደም እና የእናታችን ሐዋ ምኞትም ነበር። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከእሷም መቀናጆዋን (ሐዋን) ወደ እሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው። በተገናኛትም ጊዜ ቀላል እርግዝና አረገዘች። ፅንሱን ይዛ ተሸከመች። በከበደችም ጊዜ "ደግ ልጅ ብትሰጠን በእርግጥ ከአመስጋኞች እንሆናለን ሲሉ ጌታቸው አሏህን ለመኑ።" (ሱረቱል አዕራፍ 189) ይህ ምኞታቸው በተሳካ ጊዜ ውለታው እና ፀጋው የመጣው ከአሏህ ነውና ልያመሰኙት ግድ ይላል።
ዘርን ከመተካት እና ከእሱ ጋር ተያያዥ ስለሆኑ ጉዳዮች እስልምና ልዩ ትኩረት ያደርጋል። ይህን ከሚያመላክቱ ነገሮች መካከል አሏህ በቁርአኑ ውስጥ የሰማያት እና የምድር ንግስና የእሱ እንደሆነ ከተናገረ በኋላ ስለ ልጆች እና አሏህ በእነሱ ላይ ስላደረገው ፀጋ የተናገረው ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "የሰማያት እና የምድር ንግስና የአሏህ ነው። የሚሻውን ይፈጥራል። ለሚሻው ሰው ሴት ልጆችን ይሰጣል። ለሚሻውም ሰው ወንድ ልጆችን ይሰጣል። ወይም ወንዶች እና ሴቶች አድርጎ ያናዳቸዋል። የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል። እሱ ሁሉን አዋቂ ቻይ ነውና።" (ሱረቱ አሹራ 49-50) በሌላ በኩል ደግሞ አሏህ ልጆች የዚህ አለም ጌጦች ናቸው ይላል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ገንዘብ እና ልጆች የዚህ አለም ህይወት ጌጦች ናቸው።" (ሱረቱል ካህፍ 46)
ሸሪአ ለልጆች አስተዳደግ እና ለትምህርታቸው ትልቅ ትኩረት ይሰጣል። ምክኒያቱም የወደፊቱ ኡማ ምሰሶዎች ናቸውና። በደግነታቸው ምድር ላይ አሏህን በሚያስደስት መንገድ አሏህን ማገልገል እና መገዛት እንዲቀጥል ያደርጋሉ። አሏህ እንዲህ አለ፡ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ።" (ሱረቱ ተህሪም 6) አሊ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ የዚህ ትርጉም ስርአት አስይዟቸው አስተምሯቸው ማለት ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሁለት ሴት ልጆችን እስኪያድጉ (እስኪጎረምሱ) ድረስ በደንብ ያሳደገ ሰው፤ ጣቶቻቸውን አጠላልፈው እያሳዩ እሱ እና እኔ በትንሳኤዋ ቀን በጣም እንቀራረባለን አሉ።›› (ሙስሊም 2631)
ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸው መብት
እነዚህ መብቶች መጠለያ ቤት ፣ ምግብ ፣ መጠጥ ፣ ልብስ ፣ የጤና ወጭዎች እና ሌሎች ለልጆች ጥቅም የሚሰጡ ወጭዎችን ሁሉ መሸፈንን ይይዛል። አባት ይህን ማድረግ በቻለ ጊዜ እነዚህን መብቶች የሚወጣው እሱ መሆን አለበት።
ወላጆች መፈፀም ካለባቸው የልጆች የሞራል መብቶች መካከል በእስለምና ሃይማኖት አስተምህሮ መሰረት ጥሩ አድርጎ ተንከባክቦ ማሳደግ ነው። ሆኖም ቅዱስ ቁርአን ፣ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱናን እና የህይወት ታሪካቸውን እንዲማሩ ማድረግ ያስፈልጋል። በእስልምና አስተምህሮ መሰረት እንዲያድጉ ፣ የታዘዙትን እንዲፈፅሙ ፣ የተከለከሉትን እንዲከለከሉ እና መልካም ባህሪ እንዲላበሱ ማድረግ አለባችሁ። ይህ ሁሉ አሏህ እና መልዕክተኛውን በመውደድ ፣ ሃይማኖቱን እና ህጉንም በመውደድ መሆን አለበት።
እዝነት እና ርህራሄ በልጆች አስተዳደግ ላይ ጥልቅ የሆነ ተፅዕኖ አለው። ሆኖም በህይወት ውስጥ ባህሪያቸው ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሮ የሚያበላሻቸው መሆን የለበትም። በሌላ በኩል ደግሞ ለልጆች አለማዘን እና ርህራሄ የሌለው መሆን ፣ እነሱን መበደል ፣ ያለ አግባብ መግረፍ ወ.ዘ.ተ አዕምሯቸው ላይ ከፋት እንዲጫር እና አመፀኞች ፣ ውለታቢሶች ፣ መጥፎ ባህሪ የተላበሱ እና ግራ የተጋቡ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
ከሞራል መብቶች መካከል አክብሮት ፣ መረጋጋት ፣ ሰላም እና መዋደድ ፣ መተዛዘን እና መደጋገፍ በቤተሰብ ውስጥ መስፈን አለበት። ወላጆች ወይም የቅርብ ዘመዶች ዘወትር መጨቃጨቅ እና መነታረክ የለባቸውም። ምክኒያቱም ልጆቹ ላይ የራሱ የሆነ ተፅእኖ ያሳድራል። የተጨናነቀ እና ሸህም የሆነ ህይወት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።
ከሞራል መብቶች መካከል፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ጥሩ ጓደኛ እንዲኖራቸው ማድረግ ይኖርባቸዋል። መጥፎ እና የሚኮነን ባህሪ እና ልማድ ያለቸው ሰዎች ጋር እንዲደባለቁ መፍቀድ የለባቸውም። ምክኒያቱም ይህ የእነሱ ባህሪ ላይ ተፅዕኖ ያሳድርባቸዋል። መጥፎ ባህሪያቸው ወደ እነሱ ይጋባባቸዋልና ነው።
አባቶች እና እናቶች የወንድ ልጃቸውን እና የሴት ልጃቸውን ሁኔታ ፣ ባህሪያቸውን እና ድርጊታቸውን መከታተል እና መቆጣጠር አለባቸው።አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ደግሞ ምክር በመለገስ እና መመሪያ በመስጠት ጣልቃ መግባት ይኖርባቸዋል። ነገርግን በሚያደርጉት ነገር መካከለኛ መሆን አለባቸው። ሆኖም የሚሰጡት ምክር ወይም መመሪያ እድሚያቸውን ያገናዘበ እንጅ የተንዛዛ የማያቋርጥ ፣ በጣም ትንሽ ወይም በጣም ትልቅ መሆን የለበትም። ይህም ልጁ ምክሩን በማድመጥ እንዲዝል ፣ እንዲሰለች ሚያደርገው ሲሆን ወደ ስራ ለቀየርም ቸልተኛ እንዲሆን ያደርገዋል። ስለዚህ አባቱ እና እናቱ መቼ እና እንዴት ምክር መለገስ እና መመሪያ መስጠት እንዳለባቸው ጊዜ እና ቦታ መምረጥ አለባቸው።