የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሙስሊም ሴት ንፅህና
ሙስሊም ሴት የሚያስፈልጋትን የንፅህና ህጎች እንድትማር ሸሪአ ያስገድዳታል። ለምሳሌ የወር አበባ ፣ ኢስቲሃዷ እና የወሊድ ደም
አንዲት ሙስሊም ሴት ማወቅ እና መስራት ካለባት ነገሮች መካከል
ከግብረ ስጋ ግኑኝነት በኋላ ገላዋን መታጠብ
በቋንቋ ደረጃ ጀናባ ማለት የራቀ ማለት ሲሆን በሸሪአ ጁኑብ ማለት ደግሞ የግብረስጋግኑኝነት ወይም ነባዘርን ማፍሰስ ነው። ይህ የንፅህና መጓደል ጁኑብ ተብሎ ይጠራል። ምክኒያቱም ከንፅህና ጉድለት እስኪጠራ ድረስ ወደ ሶላት መስገጃ ቦታ መቅረብ የተከለከለ ነውና። ከግብረስጋግኑኝነት በኋላ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክኒያት ‹‹ጀናባ›› ብትሆኑ ታጠቡ።" (ሱረቱል ማኢዳ 6)
የወር አበባው ካበቃ በኋላ መታጠብ
አንዲት ሙስሊም ሴት የወር አበባዋ ባቆመ ጊዜ ገላዋን መታጠብ አለባት። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ስለ ወር አበባ ይጠይቁሃል። እሱ አፀያፊ ነው። ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው። ንፁህ እስከሚሆኑም ድረስ አትቅረቧቸው። ንፁህ በሆኑ ጊዜ አሏህ ካዘዛችሁ ቦታ ተገናኟቸው። አሏህ ከሃጢያት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው።" (ሱረቱል በቀራ 222) ‹‹ፈኢዛ ተጦሃሩነ›› በተጥራሩ (ንፁህ በሆኑ) ጊዜ›› የሚለው የአሏህ ንግግር የሚያመላክተው ገላን መታጠብን ነው።
የወር አበባ እና ኢስቲሃዷ
የወር አበባ አንዲት ሴት ልጅ ባልፀነሰች ጊዜ ወይም ሳትታመም እንዲሁ በተፈጥሮ ከማህፀኗ የሚፈስ ደም ነው። ኢስቲሃዷ ደግሞ በህመም ወይም በሌላ ምክኒያት ከተለመደው ጊዜ ውጭ ከሴት ልጅ ማህፀን የሚፈስ ደም ነው።
የወር አበባ የቆይታ ጊዜ ከሴቶች ሴቶች ይለያያል። በትንሹ ይሄ የሚባል ገደብ የለውም። እንደ ሊቃውንቶች ንግግር እና እንደአብዛሃኛዎቹ ከሆነ 15 ቀን ነው። ከዚያ ከበለጠ የወር አበባ ሳይሆን የኢስቲሃዷ (የበሽታ) ደም ነው። ብዙ ጊዜ የሴቶች የወር አበባ የቆይታ ጊዜ ስድስት ወይም ሰባት ቀን ነው።
የወሊድ ደም ካበቃ በኋላ መታጠብ
አንዲት የወሊድ ደም ያየች ሴት ከወሊድ ደም በኋላ ገላዋን መታጠብ እንዳለባት ሊቃውንት (ኡለሞች) በማያሻማ መልኩ ተስማምተዋል።
የወሊድ ደም (ኒፋሷ) ምንነት
በወሊድ ጊዜ እና እንደ ምልክት ከዚያም ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በፊት ማህፀኗን ላላ እና ዘና የሚያደርግ ደም ነው። ከዚያም በኋላ አርባ ቀን እስኪሞላት ድረስ ሊዘልቅ ይችላል። የወሊድ ደም (ኒፋሷ) የቆይታ ጊዜ ከፍተኛው 40 ቀን ሲሆን ዝቅተኛው ግን ገደብ የለውም።
ከወር አበባ እና ከወሊድ ደም ጋር የተያያዙ ጉዳዮች
የግብረስጋ ግኑኝነት ክልከላ
ባል ከሚስቱ ጋር በወር አበባ ጊዜዋ ግብረስጋ ግኑኝነት ከመፈፀም ተከልክሏል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ስለ ወር አበባ ይጠይቁሃል። እሱ አፀያፊ ነው። ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ ራቋቸው። ንፁህ እስከሚሆኑ ድረስ አትቅረቧቸው። ንፁህ በሆኑ ጊዜ አሏህ ካዘዛችሁ ቦታ ተገናኟቸው። አሏህ (ከሃጢያት) ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው።" (ሱረቱል በቀራ 222) በኡለሞች ስምምነትነ መሰረት በወሊድ ደም ወቅት የግብረስጋ ግኑኝነት ማድረግ የተከለከለ ነው።
የፍች ክልከላ
አሏህ እንዲህ አለ፡ "ነብዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ በኢዳቸው (የወር አባባ በመጠበቂያ ጊዜያቸው) ፍቷቸው።" (ሱረቱ ጦላቅ 1) ይህ የወር አበባ መጠበቂያ ጊዜያቸው ወይም (ኢዳቸው) የሚለው የአሏህ ንግግር ትርጉም የወር አበባ ላይ ፣ ወሊድ ላይ ወይም በንፅህና ጊዜያቸው ግብረስጋ ግኑኝነት አድርገው እያለ እርግዝናቸው ባለየበት ሁኔታ እንዳይፈቷቸው ነው።
የሶላት እና የፆም ክልከላ
ምክኒያቱም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋልና ነው ‹‹አንዲት ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የማትሰግድ እና የማትፆም መሆኗ እውነት አይደለምን? ያ የሀይማኖቷ ጉድለት ነው።›› (ቡኻ 1951)
የጠዋፍ (ካዕባን የመዞር) ክልከላ
ምክኒያቱም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሐጅ ወቅት አኢሻ (ረ.ዐ) የወር አበባ ባየች ጊዜ እንዲህ ብለዋልና ነው ‹‹ይህ አሏህ በአደም ሴት ልጆች ላይ ሁሉ የደነገገው ነው። ንፁህ እስክትሆኝ ድረስ በካዕባ ዙሪያ ካለመዞር በቀር ሐጃጆች የሚያደርጉትን አድርጊ አሉ።›› (ቡኻሪ 305 ፣ ሙስሊም 1211)
ቁርአንን የመንካት ክልከላ
ይህ ክልከላ አሏህ በቃሉ እንዳለው ነው፡ "ሙጦሃሩን (የተጥራሩ) እንጅ ማንም አይነካውም።" (ሱረቱል ዋቂአ 79) ይህ በዚህ እንዳለ በትክክለኛ እይታ መሰረት ጁኑብ እንደሆነ ሰው ሳይሆን ከቁርአን ከሸመደደችው በቃሏ ከያዘቸው ማንበብ ለእሷ የተፈቀደ ነው። ምክኒያቱም ጁኑብ የሆነ ሰው እስኪታጠብ ድረስ አያነብምና ነው። የወር አበባ ላይ ወይም የወሊድ ደም ላይ የሆነች ሴት አንድን የቁርአን አንቀፅ መከለስ ብትፈልግ ወይም ሌሎችን የምታስተምር ብትሆን እና መሰል ነገሮችን የምታደርግ ከሆነ ልክ እንደ እጅ ጓንት መሰል ግርዶሽ ወይም መከለያ ነገር በመጠቀም ቁርአንን መንካት ለእሷ የተፈቀደ ነው።
መስጅድ ውስጥ የመቆየት ክልከላ
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግራቸው፡ ‹‹መስጅድ በወር አበባ ላይ ለሆነች ሴት እና ጅኑብ ለሆነ ሰው የተፈቀደ እንዲሆን አላደርግም በለዋል።›› (አቡዳውድ 232) በእሱ በኩል ማለፍ መግባት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መግባት የተፈቀደ ነው። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ትላለች፡ ‹‹የወር አበባ ላይ ነኝ አልኳቸው። እሳቸውም፡ ‹‹የወር አበባሽ በአንች እጅ አይደለም አሉኝ።›› (ሙስሊም 298)
የወር አበባ አንድምታ
ጉርምስና
ለአቅመ ሐዋ የመድረስ ግዴታ ይከሰታል። ለሴት ልጅ ጉርምስና በጣም አስተማማኝ ከሆኑ ምልክቶች አንዱ የወር አበባ ነው።
የተፈታች ሴት የወር አበባዋን የምትቆጥርበት መነሻ ወይም የመጠበቂያ ጊዜ ነው
የተፈታች ሴት በወር አበባ ላይ ለነበረው የመጠበቂ ጊዜ በሶስት ወር የወር አበባ ኡደት ይጠናቀቃል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "የተፈቱ ሴቶች በነፍሶቻቸው (ከማግባት) ሶስት የወር አበባን ኡደትን ይጠብቁ።" (ሱረቱል በቀራ 228)
ሴቶች ከወር አበባ የነፁ መሆኑን የሚያመላክቱ ነገሮች
ከሴት ብልት የሚወጣ ነጭ ፈሳሽ
በወር አበባዋ የመጨረሻ ቀን ላይ ከሴት ብልት የሚወጣ ነጭ ክር መሰል ነገር የንፅህና ምልክት ነው።
የደም ፍሰቱ ማቆም እና መድረቅ
ከወር አበባ ለመንፃት ምልክት ይሆን ዘንድ አንዲት ሴት ወደ ብልቷ ቁራጭ ጨርቅ ባስገባች ጊዜ በደም ፣ በቡናማ ወይም ቢጫማ ቀለም ሳይቀልም ይወጣል።
ጉሱል (የገላ ትጥበት) ሁለት ግዴታዎች አሉት። እነሱም ኒያ ማድረግ (ማሰብ) እና ፀጉርን እና መላ አካን በውሃ ማዳረስ ናቸው። ፀጉሯ ጥቀቅጥቅ ያለም ሆነ የሳሳ በውሃ በደንብ መዳረስ አለበት።
ሴቶች ከወር አበባ እና ከጁኑብ በኋላ የሚታጠቡበት መንገድ
አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው አስማ (ረ.ዐ) ከወር አበባ በኋላ መታጠብን አስመልክቶ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀቻቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ፡ ‹‹ውሃ ይዛ እራሷ ላይ በማፍሰስ እና የፀጉሯ ስር ድረስ እስኪደርስ በማሸት እራሷን በደንብ ታንፃ። ከዚያም ሰውነቷ ላይ ውሃ ታፍስ። ከዚያም ደረቅ ጨርቅ በመያዝ እራሷን ታንፃ አሉ። አስማ በእሱ እንዴት እራሴን ላንፃ? አለች። ሱብሃነሏህ! በእሱ እራስሽ አጥሪ አሏት። ወደ እኔ ጎተትኳትና ‹‹በደም የጎደፈውን ቦታ ፈግፍጊው›› አልኳት ትላለች አኢሻ(ረ.ዐ)›› (ቡኻሪ 314 ፣ ሙስሊም 332)
ውሃ ወደየትኛውም የሰውነት ክፍል እንዳይዳረስ የሚያደርግ ማንኛወም ነገር ትጥበትን ያበላሻል፤ ውድቅ ያደርገዋልም። ለምሳሌ፡ ሴቶች የሚጠቀሙት የጥፍር ቀለም ወይም ደግሞ ሌሎች ተመሳሳይ ቁሳዊ ነገሮች ናቸው።
ቢጫማ እና ቡናማ ምልክት
ከወር አበባ በፊት እና በኋላ ከሴት ልጅ ብልት አንዳንድ ፈሳሽ ነገር ይወጣል። ከወር አበባ ጋር አብረው የሚታዩ ከሆነ የእሱ አንድ አካል ናቸው። ሴቷም ከሶላት እና ከሌሎች መቆጠብ ካለባት ነገር መቆጠብ አለባት። እንደ ኡሙ አቲያ ሐዲስ ደግሞ ከወር አበባ ውጭ ከታዩ ምንም አይነት ተፅዕኖ አይኖረውም። ‹‹ቢጫማ ወይም ቡናማ ምልክት እንደ አስፈላጊ ነገር (እንደ ወር አበባ) አንቆጥረውም ነበር።›› (ቡኻሪ 325 ፣ አቡዳውድ 307)