መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሙስሊም ሴቶች አልባሳት

በዚህ ትምህርት ውስጥ ከሙስሊም ሴቶች አልባሳት ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ስለሆኑ ጉዳዮች ትማራላችሁ።

1 ከአልባሳት እና ከጌጣጌጥ ጋር በተያያዘ አሏህ በሰዎች ላይ ያደረገውን ፀጋ ትረዳላችሁ።2 ከሴቶች አልባሳት ጋር በተያያዘ የእስልምና ሸሪአዊ ውሳኔዎችን ትማራላችሁ።3 ከሂጃብ ህጋዊነት ጋር በተያያዘ ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን ታውቃላችሁ።4 ሙስሊም ሴት ከአካሏ ለሰዎች የሚታሳየውን ገደቦች ታውቃላችሁ።

የልብስ ፀጋዎች (ጥቅሞች)

ልብስ አሏህ ለሰዎች የሰጠው አንድ ትልቅ ፀጋ ነው። በዚህም የሰው ልጅ አካሉን ይሸፍናል ፣ ከሙቀት እና ከቅዝቃዜ እራሱን ይከላከላል ፣ መዋቢያው እና ማጌጫውም ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን። አሏህንም የመፍራት ልብስ የተሻለ ነው። ይህ ከአሏህ ተአምራቶች ነው። ይገሰፁ ዘንድ (አወረደላቸው)።" (አዕራፍ 26) ልብስ ለሁሉም ወንድ እና ሴት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ሃፍረተ ገላን የሚሸፍነው ይሄው ነው። ለተለያዩ አጋጣሚዎች እና ሁነቶች ማለትም ለሰርግ ፣ ለድግስ እና መሰል ነገሮች የምንገለገልበት ማጌጫ እና መዋቢያ የሚመጣው ከዚሁ ነው።

ከሴቶች አልባሳት ጋር በተያያዘ ሸሪአዊ ውሳኔዎች ትልቅ ግቦችን ያሳካሉ። በሴቶች በኩል የግል ጉዳዮቻቸው እንዲጠበቁ ፣ ከወንድ ልጅ እይታ እንዲከለሉ እና ከባለጌዎች ለከፋ እና ድርጊት እንዲድኑ ያደርጋቸዋል። ሸሪአውን የተከተሉ አልባሳት ለሴት ልጅ ሰላም ፣ መረጋጋት እና ክብር ያገናፅፋል። ከሁሉም በላይ በሸሪአው የተፈቀዱ አልባሳትን የሚለብሱና አሏህ ያዘዛቸውን የሚታዘዙ የከለከላቸውም የሚከለከሉ ሴቶች ለሃያሉ አሏህ ያላቸውን መተናነስ እና ባርነት ይገልፃሉ።

ከማህበረሰቡ አንፃር ሲታይ ደግሞ የሴቶች ሸሪአዊ አልባሳት ወይም ሂጃብ ለማህበረሰቡ ከፈተና መጠበቂያ እና ለሁሉም አባላቶቹ መረጋጋት እና ደህንነታቸው የሚጠበቅበት ነው። መጥፎ ነገር ከተከሰተ ሁሉንም የምህበረሰብ ክፍል ወንዱንም ሴቱንም ያጠፋል። የቤተሰብ አወቃቀር ፣ መረጋጋት እና ደህንነቱ ያናውጣል፤ ይበታትናል። ይህ በብዙ ሐገራት የሚታይ ክስተት ነው።

የሙስሊም ሴት ሂጃብ ቅድመ ሁኔታዎች

١
1 አንዳንድ የፊቅህ ሊቃውንት እንደሚሉት ሙሉ አካልን የሚሸፍን ወይም እንደ ሌሎቹ ንግግር ደግሞ ከእጅ እና ከፊት በቀር ሙሉ ሰውነትን የሚሸፍን መሆን አለበት
٢
2 በራሱ ጌጥ ያልሆነ መሆን አለበት
٣
3 ወፍራን እና ከስር ያለውን ነገር የማያሳይ መሆን አለበት
٤
4 ሰፋ ያለ እና የሰውነትን ቅርፅ የማያሳይ መሆን አለበት
٥
5 ሽቶ ያልተነሰነሰበት ወይም ያልታነጣ መሆን አለበት
٦
6 ከወንዶች አልባሳት ጋር የማይመሳሰል መሆን አለበት
٧
7 ከከሃዲያን ሴቶች አልባሳት ጋር የማይመሳሰል
٨
8 ስምና ዝና መገለጫ ያልሆነ መሆን አለበት

1 አካልን የሚሸፍን

አሏህ እንዲህ አለ፡ "ነብዩ ሆይ! ለሚስቶችህ ፣ ለሴት ልጆችህ ፣ ለምዕመናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው። አሏህ መሃሪ አዛኝ ነው።" (አህዛብ 59) ፊትን እና እጅን መሸፈን በተመለከተ ኡለማኦች (ሊቃውንት) በዚህ ሃሳብ ተለያይተዋል። አንዳንዶቹ ግዴታ ነው ይላሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ጠቅላላ መሸፈኑ ግዴታ እንደሆነ ቢስማሙም እጅና ፊቱን የተወደደ ነው ይላሉ።

2 በራሱ ጌጥ ያልሆነ መሆን አለበት

ይህ በተከታዩ የአሏህ ንግግር ተገልፃል፡ "ጌጣቸውንም አይግለጡ።" (ሱረቱ ኑር 31)

3 እና 4 ወፍራም እና ሰፋ ብሎ የሰውነት ቅርፅን የማያሳይ መሆን አለበት

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ያላየኋቸው ሁለት አይነት የጀሃነም ሰዎች አሉ። የበሬ ጅራት የመሰለ ሰዎችን የሚገርፉበት መግረፊያ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና የለበሱ የሚመስሉ ነገርግን የተራቆቱ (የተገላለጡ) የሆኑ ሴቶች ናቸው። እነዚህ መጥፎ ነገር ያደርጋሉ፤ ባሎቻቸውን ወደ መጥፎ ነገር እነደዲያጋድሉ የሚያደርጉ ናቸው። ራሳቸው ወደ አንድ ጎን እንዳጋደለ የቡኸት ግመል የሚመስል ነው። ጀነት አይገቡም፤ ማአዛዋን (ጠረኗንም) አያሸቱም። እንዲህ እንዲህ ካለው ርቀት ቦታ ላይ ሆኖ የሚያውድ ቢሆንም እንኳ አሉ።›› (ሙስሊም 2128) ኡሳማ ቢን ዘይድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወፍራም ካባ አለበሱኝ። ከዲህያ አል-ኸልቢ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ነው። እኔም ለሚስቴ ሰጠኋት። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቁኝ። እኔም ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ለሚስቴ ሰጥቻታለሁ አልኳቸው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉኝ፡ ‹‹ከስር ቀሚስ እንድታደርግ ንገራት። የአጥንቷ ፍላጫ (የሰውነቷ ቅርፅ) እንዳይገለጥ እፈራለሁና አሉ።›› (አህመድ 21786)

5 ሽቶ የተነሰነሰበት ወይም የታነጣ መሆን የለበትም

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሰዎች ጠረኗን ያሸቱ ዘንድ ሽቶ ነስንሳ በሰዎች በኩል የምታልፍ ሴት አመንዝራ (ዝሙተኛ) ናት አሉ።›› (አነሳኢ 5126)

6 የወንዶችን አልባሳት መምሰል የለበትም

ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሴቶችን የሚመሳሰሉ ወንዶችን እና ወንዶችን የሚመሳሰሉ ሴቶችን ረግመዋል።›› (ቡኻሪ 5885)

7 የከሃዲያን ሴቶች አልባሳት ጋር መመሳሰል የለበትም

በሸሪአ ውስጥ እንደተገለፀው ሙስሊሞች ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በአምልኮቶቻቸው ፣ በበአላታቸው ፣ በልብሶቻቸው ከከሃዲያን ጋር መመሳሰል አይፈቀድላቸውም። ምክኒያቱም የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋልና፡ ‹‹ከሰዎቹ የተመሳሰለ እሱ እራሱ ከእነሱ አንዱ ነው።›› (አቡዳውድ 4031)

8 የኩራትና ዝና መገለጫ መሆን የለበትም

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹በዚህ አለም ውስጥ (የኩራት እና የእብሪት ልብስን የተከናነበ ሰው በትንሳኤው ቀን አሏህ የውርደት ልብስን ያከናንበዋል። ከዚያም በእሳት ያያይዘዋል።›› (ኢብን ማጃ 3607) ይህ የዝና ልብስ ከሰዎች መካከል ዝነኛ ተብለው እንድታወቁ የምያደርግ ልብስ ነው።

ከላይ የተገለፁት ቅድመ ሁኔታዎች አንዲት ሙስሊም ሴት ከቤት ስትወጣ ወይም ከመህረሞቿ ውጭ ሌሎች ወንዶች ባሉበት ወቅት ልትከተለው የሚገባ የአለባበስ ስርአትን ይመለከታል። በመህረሞቿ ፊት ወይም ከሌሎች ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ተግባራዊ ማድረግ ግዴታ የለባትም። በዚህ ጊዜ ሽቶ መነስነስ እና የተወሰኑ ጌጣጌጦችን ማድረግ እና ማሳየት ይፈቀድላታል።

መገለጥ

መገለጥ ማለት አንዲት ሴት መህረሟ ካልሆኑ ሰዎች ፊት ጌጧን እና ውበቷን ማሳየት ማለት ነው።

የሙስሊም ሴት አለባበስ ከፊቷ ያሉትን ሰዎች ከግምት ውስጥ ያስገባ ስሆን እንደምከተለው መሆን አለበት

١
1 ከእንግዶች ፊት ስትሆን የሚኖራት አለባበስ (መህረም ያልሆኑ)
٢
2 ከወንድ ዘመዶቿ ፊት ስትሆን የምትለብሰው አለባበስ
٣
3 ከሌሎች ሙስሊም ሴቶች ጋር ስትሆን የሚኖራት አለባበስ
٤
4 ከአህለል ኪታብ (ከመጽሐፉ ሰዎች) ሴቶች ጋር ስትሆን የሚኖራት አለባበስ

ከእንግዶች ፊት ስትሆን የሚኖራት አለባበስ

መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ያዘዙት እና ቅድመ ሁኔታዎቹ ቀደም ብሎ የተገለፁት ሸሪአዊ የሂጃብ የአለባበስ ስርአት ነው።

አንዲት ሙስሊም ሴት ከወንድ ዘመዶቿ ፊት ስትሆን ሊኖራት የሚገባ አለባበስ

ከወንድ ዘመዶቿ ፊት በምትሆን ጊዜ ባብዛሃኛው ግልፅ ከሚሆነው ለምሳሌ አንገቷ ፣ ፀጉሯ እና እግሮቿ እንዲሁም ፊቷ እና እጆቿ በቀር ሙሉ አካሏን መሸፈን አለባት። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ለምዕመናን ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ። (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንድ ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች…አይግለጡ።" (ሱረቱ ኑር 31)

አንዲት ሙስሊም ሴት ከሌሎች ሙስሊም ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ የሚኖራት አለባበስ

መህረም ወንዶች በሚኖሩበት ጊዜ እንደምታደርገው ሁሉ መላ አካላቷን ትሸፍናለች። ያ ብዙ ጊዜ የሚገለጠው ወይም የሚታየው አንገቷ ፣ ፀጉሯ ፣ እግሮቿ እና እንዲሁም ፊቷ እና እጆቿ ሲቀሩ። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ለምዕመናን ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ። (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንድ ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው እንጅ አይግለጡ።" (ሱረቱ ኑር 31)

አንዲት ሙስሊም ሴት ከመጽሐፉ ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ የሚኖራት የአለባበስ ስርአት

ከሙስሊም ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ እንደሚኖራት የአለባበስ ስርአት መላ አካላቷን ትሸፋፍናለች። ያ ግልፅ የሆነው ሲቀር። ለምሳሌ አንገቷ ፣ ፀጉሯ ፣ እግሮቿ ፊቷ እና እጆቿ ናቸው። ይህ ምክኒያቱነም የመጽሐፉ ሰዎች ሴቶች ከምዕመናን እናቶች ቤት ይገቡ የነበረ መሆኑ እና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከእነሱ እንዲሸፋፈኑ ስላላዘዙ ነው።

የተፈቀዱ እና የተከለከሉ የሴቶች አልባሳት እና ጌጣጌጦች

١
የተፈቀዱ አልባሳት እና ጌጣጌጦች
٢
የተወደዱ አልባሳት እና ጌጣጌጦች
٣
የተከለከሉ አልባሳት እና ጌጣጌጦች

የተፈቀዱ የሴቶች አልባሳት እና ጌጣጌጦች

አልባሳት እና ጌጣጌጦች በመሰረቱ የተፈቀዱ ናቸው። ሸሪአ ከከለከለው በስተቀር የተለየ ነገር የለም። አንዲት ሴት ማንኛውንም አይነት አልባሳት ፣ ሁሉንም የቀለም እና የጨርቅ አይነቶች መልበስ ይፈቀድላታል። እንዲሁም በተፈቀዱ የጌጣጌጥ አይነቶች እራሷን ማስዋብ ትችላለች። ለምሳሌ ጌጣጌጥ ፣ ሽቶ እና ኮስሞቲክሶች ወ.ዘ.ተ ናቸው። ያ ግን እራሷን የማይጎዳት እስከሆነ ድረስ እና ከከሃዲያን ጋር የማይመሳሰሉ እና የተሰሩባቸው ቁሳቁሶች የተከለከለ ለምሳሌ የአሳማ ስብ እስካልሆነ ድረስ ነው።

የተወደዱ አልባሳት እና ጌጣጌጦች

በዚህ ማለት የተፈለገው ሸሪአው የተወደደ ነው ብሎ የጠቀሰውን ማንኛውንም ነገር እና አንዲት ሴት ባሏን ለማስደሰት እና ለማማለል የምትለብሰው እና የምትዋብበትን ያልተከለከለ ማንኛውም ነገር ነው።

የተከለከሉ አልባሳት እና ጌጣጌጦች

ይህ ማለት ሸሪአው የከለከለው እና በእሱ ላይ ያስጠነቀቀው ማንኛውም አይነት አልባሳት እና ጌጣጌጥ ነው። አሏህ ያዘዘውን መታዘዝ ፣ የከለከለውን መከልከል አለባት። ይህ ደግሞ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ከሚያደርጉት የተለየ ነገር ማድረግ እና ከወንዶች ጋር አለመመሳሰል ወ.ዘ.ተ ነው።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር