የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ውርስ በኢስላም
ውርስ የሰው ልጆች በጥንት ጊዜም ሆነ በአሁኑ ጊዜ የተቀበሉት አለማቀፋዊ ስርአት ነው። ምክኒያቱም የገንዘብ ባለቤት ለመሆን ለሚወደው እና እሱን ለማግኘት ለሚመኘው የሰው ልጅ ተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ እና የሟቹን ሰው ውርስ የመከፋፈል ችግር የሚቀርፍ ነው።
ከውርስ ጋር ተያያዥ የሆኑ የእስልምና ህግጋት የሚታወቁት የአውራሹ እና የወራሾቹ ሁኔታ እንዲሁም ድርሻቸውንከመመርመር ጋር የተያያዘ መሆኑ ነው። የእስልምና የውርስ ስርአት የተሟላ እና የሚደንቅ ስርአት ነው። የእስልምና የውርስ ስርአት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል አንዱ በወራሾች መካከል ጠብ እና ጥላቻን የሚያስቀር መሆኑ ነው። ምክኒያቱም ወራሾቹ ውርሱ በአሏህ ትዕዛዝ መሰረት እንደተከፋፈሉ ሲያውቁ ነፍሶቻቸው ይረጋጋሉ፤ በክፍልፋዩም ይረካሉና ነው። እንዲሁም የእስልምና የውርስ ስርአት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል የሁሉንም ወራሾች መብት የሚያስጠብቅ መሆኑ ነው። ከውርሱ አንድም ክፍልፋይ አይቀርባቸውም።
የውርስ ምሰሶዎች
አውራሽ ሟች ሰው ነው። ወይም ደግሞ ውርስ ትቶ የሞተ ሰው ነው።
ከውርስ ምክኒያቶች በአንዱ ከአውራሹ ሰው መውረስ የሚገባው በህይወት ያለ ወይም በህይወት እንዳለ የታመነበት ሰው ነው።
ይህ አውራሹ ሰው በውርስ መልኩ እንዲተላለፍ ትቶት የሄደው ገንዘብ ወይም ንብረት ነው።
የውርስ ቅድመ ሁኔታዎች
ውርሱ የሚከፈልበት ቅደም ተከተል
በእስልምና ህግ ውስጥ ከውርስ ጋር ተያያዥ የሆኑ አህካሞች (ብያኔዎች)
ወንድ ወራሾች
ሊቃውንት የተስማሙባቸው ወንድ ወራሾች በቁጥር አስር ናቸው። እነሱም፡- ልጅ ፣ የልጅ ልጅ ፣ አባት ፣ የወንድ አያት እና ቅድመ አያት ፣ ወንድም ፣ የወንድም ልጅ ፣ የአባት አጎት ፣ የአባት አጎት ወንድ ልጅ ፣ ባል እና በሟቹ ነፃ የተደረገ አገልጋይ ወይም ባሪያ ናቸው።
ሴት ወራሾች
ከሴቶች መካከል ሊቃውንት የተስማሙባቸው ሰባት ሴት ወራሶች አሉ። እነሱም ሴት ልጅ ፣ የወንድ ልጅ ሴት ልጅ፣ እናት ፣ ፣ የሴት አያት ፣ እህት ፣ ሚስትእና በሟች ነፃ የተባለች ሴት ባሪያ ወይም አገልጋይ ናቸው።