የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በሠላት ውስጥ መመሰጥ
አለትምህርቱ ማብራሪያ
ዓላማዎች
43,531 ሌላ ተማሪ ይህን ትምህርት አጠናቀቀ
በሠላት ውስጥ መመሰጥ የሠላት እውነተኛ መገለጫና አንኳሩ ነው፡፡ መመሰጥ ማለት፡ አንድ ሰጋጅ፣ በሠላት ውስጥ የተናነሰና እራሱን ዝቅ ያደረገ ሆኖ፣ የሚያነበውን የቁርኣን አንቀጽ፣ ጸሎቱንና ውዳሴን በሕሊናው እያስተነተነ አላህ(ሱ.ወ) ፊት መቆሙ ነው፡፡
መመሰጥ፣ ከአምልኮዎች ሁሉ በላጩና የላቀ የታዛዥነት መገለጫ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ በመፅሐፉ ውስጥ መመሰጥ የምእመናን ባህሪ መሆኑን ትኩረት ሰጥቶ የተናገረው ለዚህ ነው ፡፡አላህ (ሱ.ወ)፡- #ምእመናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ) እነዚያ እነሱ በስግደታቸው ውስጥ አላህን ፈሪዎች (የሆኑት); ይላል፡፡ (አል ሙእሚኑን 1-2)
በሠላት ውስጥ መመሰጥ የቻለ ሰው፣ የኢማንና የአምልኮን ጣዕም ማጣጣም ይችላል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹የዓይን መርጊያዬ በሠላት ውስጥ ተደርጋልኛለች›› ያሉት ለዚህ ነው፡፡ (አል ነሳኢ 3940) የዐይን መርጊያ ማለት፣ ከዳር የደረሰ ደስታ፣ ስኬትና እርካታን ማግኘት ነው፡፡
በሠላት ውስጥ ለመመሰጥ የሚረዱ መንገዶች
ዝግጅት ማለት፡ ወንዶች፣ የሚያምር ልብስ በመልበስና ወደ ሠላት በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ በመራመድ አስቀድሞ ወደ መስጂድ በመምጣት፣ ከሠላት በፊት የሚከናወኑ ነብያዊ ፈለጎችን በማከናወን የሚረጋገጥ ነው፡፡
አንድ ሰው፣ ከፊት ለፊቱ ሐሳቡን የሚሰርቁ ምስሎች፣ ልብ የሚያንጠለጥሉ ጨዋታዎችና ሐሳቡን የሚሰርቁ ድምፆች ባሉበት መስገድ የለበትም፡፡ እንዲሁም፣ ሽንት ቤት መግባት እያስፈለገው፣ ተርቦ ወይም ተጠምቶ፣ ምግብና መጠጥ በቀረበበት ቅጽበት ሠላት መጀመር የለበትም፡፡ ይህ ሁሉ ያስፈለገው ሰጋጁ አዕምሮው ነፃ እንዲሆንና ከባድ ጉዳይን በማስተናገድ እንዲጠመድ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ከፊት ለፊቱ የሚያገኘው ሠላቱን ይሆናል፡፡ ሠላት ደግሞ ከጌታው ጋር የሚነጋገርበት ወሳኝ ነገር ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሠላትን ሲሰግዱ፣ በሩኩዓቸውም በሱጁዳቸውም ውስጥ፣ እያንዳንዱ መገጣጠሚያቸው ወደ ቦታው እስኪመለስ ድረስ በመረጋጋት ነበር፡፡ ሠላቱን ማሳማር ያልቻለውን ሰውዬ፣ በሠላቱ ውስጥ በሚፈፅማቸው ተግባሮችን በሙሉ በእርጋታና በዝግታ እንዲፈፅም አዘውታል፡፡ መቻኮልን ከልክለዋል፤ችኮላን ከቁራ ውሃ አጠጣጥ ጋር አመሳስለውታል፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- #በስርቆት አደገኛው ሰው ማለት ከሠላቱ ላይ የሚሰርቅ ነው፡፡; ሲሉ፣ ሠሓቦች፡ «ከሰላቱ ላይ የሚሰርቀው እንዴት ነው?» በማለት ጠየቁ፡፡ እሳቸውም፡ #ሩኩዓንም ሱጁዷንም በማጓደል ነው; በማለት መለሱላቸው (አህመድ 22642)
በሠላት ውስጥ ሆኖ የፈጣሪን ኃያልነትና ልቅና፣ የነፍሱን ደካማነትና ወራዳነት፣እንዲሁም ጌታው ፊት በመቆም እየተማፀነውና እያናገረው እንደሆነ ያስብ፣ ለርሱ በመዋደቅና በመዋረድ ፈጣሪውን ይለምን፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ አላህ (ሱ.ወ) በወዲያኛው ዓለም ለምእመናን ያዘጋጀውንና የደገሰውን፣ እንዲሁም አጋሪያን የሚጠብቃቸውን ቅጣትና ውርደት ያስተንትን፡፡ በወዲያኛው ዓለም ጌታው ፊት የሚቆምበትን ጊዜ ያስታውስ፡፡
አንድ ሰጋጅ በሠላቱ ውስጥ መመሰጥን የሚያገኘው፣ አላህ (ሱ.ወ) እንደሚሰማው፣ የጠየቀውን እንደሚሰጠውና ለልመናው ምላሽ እንደማይነፍገው በሕሊናው መሳል በሚችለው ደረጃ ልክ ነው፡፡
ቁርኣን የተወረደው ሊያስተነትኑት ዘንድ ነው፡፡ "ይህ ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሀፍ ነው አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአዕምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ አወረድነው፡፡;" ሶድ 29