የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ዘካት ትርጉሙና ዓላማዎች
ዘካ የእስልምና ሶስተኛው ምሰሶ ሲሆን ለድሆች፣ ለተቸገሩ እና ለሚገባቸው ሰዎች ከገንዘባቸው የተወሰነ ክፍል በመስጠት ስቃያቸውን ለማቃለል ከአላህ የተጣለበት የገንዘብ ግዴታ ነው።
1 ገንዘብን መውደድ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ሲሆን፣ ይህ ባህሪው ገንዘቡን በመያዝና በመጠበቅ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት እንዲኖረው ያደርገዋል፡፡ ኢስላማዊው ሕግ ነፍስ ከዘቀጡ የስስታምነትና ልክ የለሽ የገንዘብ ጥማት ባህሪዎች እንድትጸዳና እንዲሁም ከቁሳቁስ ፍቅርና እንድትላቀቅ ምጽዋትን በግዴታነት ደነገገ፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከገንዘቦቻቸው ስትኾን፣ በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የኾነች ምጽዋትን ያዝ፡፡›› (አልተውባ 103)
ምዕዋት መስጠት በማኅበረሰቡ መካከል የመደጋገፍና የመዋደድ መሰረትን ይጥላል፡፡ የሰው ልጅ ነፍስ ውለታ የዋለላትን አካል በመውደድ ላይ የተገራች ናት፡፡ በምጽዋት አማካይነት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ልክ እንደ አንድ ግንብ ከፊሉ ከፊሉን የሚደግፍና እርስ በርሳቸው የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ሆነው ይኖራሉ፡፡ በመሐከላቸው ስርቆት፣ ዘረፋና ማጭበርበር በብዛት የማይታየውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
3 በምጽዋት፣ ለዓለማት ጌታ ሙሉ ለሙሉ መማረክና ፍጹም ታዛዥ መሆን ይረጋገጣል፡፡ አንድ ባለ ሃብት፣ ከንብረቱ ላይ ምጽዋትን በሚያወጣ ጊዜ የአላህን ሕግጋት በመተግበርና ትዕዛዙን በመፈፀም ላይ ሲሆን በተሰጠው ጸጋ ላይ የጸጋውን ባለቤት እያመሰገነም ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹ብታመሰግኑም እጨምርላችኋለሁ፡፡›› ይለናን፡፡ (ኢብራሂም 7)
ምጽዋትን በመተግበር ማኅበራዊ ዋስትና ይረጋገጣል፣ እንዲሁም በተለያዩ የማኅበረሰቡ ክፍሎች መካከል አንጻራዊ የሆነ የኢኮኖሚ መመጣጠን ይከሰታል፡፡ በተጨማሪም ምጽዋትን ለሚገባቸው የማኅበረሰቡ ክፍሎች መስጠት፣ ሀብት በተወሰኑ የማኅበረሰቡ ክፍሎች ውስጥ የተገደበና የተከማቸ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፡- ‹‹ከናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይሆን፡፡›› ይላል፡፡
ኢስላም ዘካ የሚሰጣቸውን ክፍሎች ገድቦ አስቀምጧል፡፡ አንድ ሙስሊም ከነኚህ ክፍሎች መካከል ለአንዱ ብቻ ወይም ከአንድ በላይ ለሆኑ አካሎች ዘካውን መስጠት ይችላል፡፡ ለሚገባቸው ክፍሎች ሊያከፋፍሉለት ለሚችሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበሮች መስጠትም ይችላል፡፡ ዘካን በሀገር ውስጥ ማከፋፈሉ በላጭ ነው፡፡