መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የክረምት ትምህርት፡ ሶላት እና ፆም

በክረምት ወቅት ወደ ሃያሉ አሏህ የምንቀርብበት ትልልቅ እድሎች አሉ። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለነዚህ እድሎች እና በክረምት ውስጥ ከሶላት ጋር ተየያዥ የሆኑ ስንቆችን ትማራላችሁ።

1 በክረምት ወቅት የሶላት ስንቆችን ትማራላችሁ2 በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ወደ አሏህ የምትቀርቡበትን እድሎች ትለያላችሁ

የሶላት ጥሪ በብርዳማው ክረምት

ብርዱ በክረምት ውስጥ ካየለ (ከበረታ) ሁኔታው መታየት አለበት። ብርዱ ከቤታቸው ወጥተው ወደ ሶላት ከመሄድ ካገዳቸው የሶላት ጥሪው እንደተለመደው ይሆናል።

ብርዱ በጣም ጠንቶ፤ ሰውም ከቤቱ ወጥቶ ለመሄድ አስቸጋሪ በሆነ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) በሶላት ጥሪው ውስጥ እንዲህ ይላል፡ ‹‹አዋጅ! ባላችሁበት (በምቾታችሁ) ስገዱ›› ወይም ‹‹በቤታችሁ ውስጥ ስገዱ›› ‹‹በቤታችሁ ውስጥ ስገዱ›› ይላል። በዚህም ምክኒያት ወደ መስጅድ ሄደው ከመስገድ ቤታቸው ውስጥ ሆነው እንዲሰግዱ ይፈቀድላቸዋል።

ናፊዕ እንዲህ አለ፡ ኢብን ኡመር በአንድ ብርዳማ ሌሊት ደጅናን (በመካ አቅራቢያ የሚገኝ ተራራ) ላይ የሶላት ጥሪ አደረገ። ከዛም አለ፡ ‹‹በምቾታችሁ (ባላችሁበት) ስገዱ አሏህ ሰላት እና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና የአሏህ መልዕክተኛ አዛን እንድናደርግ እና ከዛም ‹‹አዋጅ! በቤታችሁ ውስጥ ስገዱ›› በብርዳማ ሌሊት ወይም ደግሞ መንገደኛ ሁናችሁ ዝናብ በሚጥል ጊዜ ብለው አሳውቀውናል ሲል ነገረን። (ቡኻሪ 632 ፣ ሙስሊም 697)

እሳት ወይም የእሳት ምድጃ ባለበት ቦታ መስገድ

ሰዎች በክረምት ወቅት ቤታቸውን ለማሞቅ ሲሉ እሳት ያቀጣጥላሉ። ያ ደግሞ ሶላት በሚሰግዱበት አቅጣጫ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጅ እሳት አምላኪ ማጁሳዎች ጋር ከመመሳሰል እንዲርቅ እና እሳቱም የሰጋጁን ልቦና ስለሚሰርቅ ስግደቱ ወደ እሳቱ አቅጣጫ ባይሆን ይመረጣል።የእሳት ምድጃን ከፈለጓትና ቦታ መቀየር ከከበዳቸው ወደ እሱ ዞሮ መስገድ ችግር የለውም።

የእሳት ምድጃን በተመለከተ የእሳት ነበልባል እስከሌለው ድረስ ወደ እሱ ዞሮ መስገድ ችግር የለውም የቂብላ አቅጣጫ እስከሆነ ድረስ ማለት ነው።

ሁለት ሶላቶችን ማጣመር (ማቀኛጀት)

ሁለት ሶላቶችን ማጣመር የዝሁር እና የአስር ሶላትን ማጣመር እና መስገድ ነው። ወይም ደግሞ የመግሪብ ሶላት መስገድ እና ከኢሻ ሶላት ጋር ማጣመር ነው። ያ ማለት ደግሞ ሁለት ስግደቶችን በአንደኛው የሶላት ወቅት ይሰገዳሉ ማለት ነው። (የማፍጠንም ይሁን የማዘግየት) ማጣመሩ የሚፈቀደው ለማጣመር በቂ ምክኒያት ካለው ብቻ ነው።

ሁለት ሶላቶችን ማጣመር ከሚፈቀድበት በቂ ምክኒያቶች ውስጥ በክረምት ወቅት በብዛት ይገኛል። ለምሳሌ ዝናብ። አንዳንድ ሊቃውንት (ኡለማ) ደግሞ ከባድ ብርዳማ ንፋስ ፣ ከባድ ቅዝቃዜ ፣ መንገዶች የሚዘጋጉበት የበረዶ ግግር ፣ መንገዶችን ያጥለቀለቀ አሮንቃ (ጭቃ) ይጠቅሳሉ።

ሶላት ለማጣመር የሚፈቀድበት በቂ ምክኒያት ምን ማለት ነው? ሰዎች በጀመአ (በህብረት) ለመስገድ ከቤት ወጥተው ወደ መስጅድ ለመሄድ ከባድ በሚሆንባቸው ሁኔታዎች ውስጥ መስጅድ መቅረት የሚፈቀድበት አግባብ ሲሆን ልክ እንደ ቀላል ዝናብ ያለ ግን ሰዎችን ከቤት ወጥተው ጉዳያቸውን መፈፀም አይከለክላቸውም።

ዋና መርሁ ሙስሊሞች ሶላታቸውን በሰአቱ መስገድ አለባቸው የሚለው ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በረጋችሁም ጊዜ ሶላትን (አሟልታችሁ) ስገዱ። ሶላት በምዕመናን ላይ በጊዜያት የተገደበች ናትና።" (ሱረቱ ኒሳዕ 103) ለዚህም ነው ማጣመሩ በቂ ምክኒያት ወይም ሰበብ ካልኖረው በቀር ተቀባይነት የሌለው። በኡመር ኢብን ኸጧብ እና በኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንደተወራው፡ "ያለ በቂ ምክኒያት ሁለት ሶላቶችን ማጣመር ከትልልቅ ሃጢያት (ወንጀሎች) ነው።"

በጀመአ (በህብረት) የማይሰግዱ ሰዎች ለምሳሌ ሴቶች ፣ የታመመ ሰው ፣ ጀመአ ዝንጉ የሆነ ሰው ሶላትን አያምሩም። ምክኒያቱም አጣምረው መስገድ አያስፈልጋቸውምና። ከእነሱ የሚጠበቀው ሶላትን በወቅቱ መስገድ ነው። ልክ እንደዚሁ ሁለተኛውን ሶላት ከመስገዱ በፊት ሰበቡ (የማጣመሩ ምክኒያት) ካበቃ ሶላቱን አያጣምርም።

ሶላትን ማጣመር በተመለከተ ለሙስሊም ሰው አንድ አዛን ማድረግ ፣ ለእንዳንዱ ሶላት ኢቃም ማድረግ ፣ ከእነሱ በኋላ አሏህን ማውሳት በቂ ነው።

በማጣመሩ ምክኒያት ሰበቦች መኖራቸውን በተመለከተ በአንዳንድ መስጅዶች ልዩነት ይኖራል። ዋናው መሰረታዊ መርህ ግን ኢማሙ ሃላፊነት አለበት የሚለው ነው። እውቀት ካለው ያቅሙን ይጥራል፤ እውቀት ያላቸውንም ያማክራል። የተፈቀደ መሆኑን ካላሰበ አይሰበስብም። የመስጅዱ ጀመአ (ህብረት) መበጣበጥ የለበትም።

ክረምት፡ ቂያም እና ፆም

በአንዳንድ ዘገባዎች እንደመጣው፡ "ክረምት የሙዕሚን (የአማኝ) ሰው ፀደይ ነው። ቀኑ አጭር ነው፤ ይፆማል። ሌሊቱ ረዥም ነው፤ ቆሞ ይሰግዳል።" አልበይሃቂ ‹‹ሱና አል-ኩብራ›› 8456 ላይ አካተውታል። ፀደይ ተብሎ የተጠራበት ምክኒያት በአምልኮ አፀድ (የአትክልት ቦታ) ስለሚመላለስ ፣ በክረምቱ ውስጥ በቀኑ ማጠር ቀኑን ያለ ረሃብ እና ጥማት መፆም እና በሌሊቱ መርዘም የሌሊት ስግደቱን መፈፀም ስለሚችል ነው። ምክኒያቱም ሶላት እና እንቅልፍ አዋዶ መሄድ ይችላልና ነው።

በአንዳንድ ዘገባዎች ደግሞ፡ "በክረምት ወቅት መፆም የብርድ ምርኮ ነው" ተብሏል። (አህመድ እነደዘገበው 18959) ምርኮውን ተጠቀሙበት) ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ "ክረምት የአሏህ ተገዦች (የአቢዶች) ምርኮ ነው።" በአቡ ነኢም ((አል-ሂለያ) ላይ ተዘግቧል። (1/51)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር