የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት በጉዞ ወቅት የተትረፈረፉ ስንቆች
በክረምት የሽርሽር ጉዞ ወደ መኝታ ከመሄድ በፊት የተለኮሰ እሳት መጥፋት አለበት። በተለይ ደግሞ በድንኳን እና መሰል ነገሮች ውስጥ የተለኮሰ ከሆነ።
አቡ ሙሰል አሽአሪ ባስተላለፈው ሐዲስ እንዲህ አለ፡ "መዲና ውስጥ አንድ ቤት ሌሊት በሰዎቹ ላይ ተቃጠለ። እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ እነሱ አወሩና ‹‹ይህ እሳት ለእናንተ ጠላት ነው፤ በተኛችሁ ጊዜ አጥፉት አሉ።››" (ቡኻሪ 6293 ፣ ሙስሊም 2015)..............
መርሁ አደን የተፈቀደ ነው የሚል ሲሆን ነገርግን ልብ ከአደኑ ጋር የተንጠለጠለ ፣ ከሃይማኖት ጉዳይ እና ከቤተሰብ የሚያርቅ ፣ የብክነት እና የጉራ ምክኒያት መሆን የለበትም። በሐዲስ ውስጥ እንደተገለፀው፡ ‹‹በበረሃ ውስጥ የሚኖር ሰው ደረቅ ነው። አደንን የሚከተል ሰው ደግሞ ሰነፍ ደካማ ነው›› ተብሏል። (አቡዳውድ 2859)
መከልከሉ ማስረጃ የቀረበበት ካልሆነ በቀር እንስሳትን ማደን እና መብላት የተፈቀደ ነው። ለምሳሌ ልክ እንደ ተኩላ ፣ ቀበሮ ፣ እንደ ጥንባንሳ ያሉ ጥፍር ያላቸው የወፍ ዝርያዎች እና እንደ እባብ እና መሰል ያሉ መርዛማ እንስሳት መብላት አይፈቀድም።
አመቱን ሙሉ የየብስ እና የባህር እንስሳትን ማደን የተፈቀደ ነው። በጁምአም ሆነ በረመዷን ወር ወይም በተከበሩ ወራት ማደን ከሌላው ጊዜ ጋር ምንም ልዩነት የለውም። ነገርግን በመካና በመዲና ውስጥ ማደን የተከለከለ ነው። ባለቤትነታቸው የሌሎች ሰዎች የሆኑ እንስሳትን ማደን የተከለከለ ነው። ለሙህሪም ሰው የሜዳ እንስሳትን ማደን የተከለከለ ነው።
አዳኙ ሰው ሙስሊም መሆን አለበት። ለአደን በተዘጋጁ ወፎች ወይም ውሾች ወይም ደግሞ ሳያውቅ መሳሪያው አባርቆበት አደኑን ቢመታ የአደኑን እንስሳ መብላት አይፈቀድም። ከመሞቱ በፊት ይዞ ሃላል ካላደረገው በቀር ማለት ነው።
የአደን እንስሳ ሞቱ በመመታቱ ካልሆነ በቀር አንገቱን በማነቅ ፣ ውሃ ውስጥ በመዝፈቅ ፣ ክብደት ባለው ነገር በመምታት ወይም ከፍ ካለ ቦታ ወርውሮ በመጣል መግደል አይፈቀድም። ይልቁንም የአደኑን እንስሳ ህይወቱ እያለ ከያዘው የአሏህን ስም በመጥቀስ ማረድ አለበት።
አድኖ ላይበላ ያለ አግባብ በቂልነት የአደን እንስሳዎችን መግደል እና ለአደን መለማመጃ ብሎ ወፎችን አስሮ ማስቀመጥ ሃጢያት (ወንጀል) ነው።
‹‹ከኢብን ኡመር ጋር ሁኜ እያለ አንዲት ወፍ አስረው እሷን ኢላማ አድርገው በሚወረውሩ ወጣት ወንዶች በኩል አለፍን። ኢብን ኡመርን ባዩ ጊዜ እሷን ትተው በመሄድ ተበታተኑ። ኢብን ኡመር እንዲህ አለ፡ ‹‹ይህን ያደረገው ማን ነው? ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን ያደረገ ሰው ረግመዋል።›› (ቡኻሪ 5515 ፣ ሙስሊም 1958)
ለጨዋታ ለቀልድ ተብሎ እንኳ ቢሆን ሰው ላይ መሳሪያ መደቀን የተከለከለ ነው። በሐዲስ ውስጥ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው፡ ‹‹አንዳችሁም ወደ ሙስሊም ወንድሙ መሳሪያን አይደግን፤ እንዲመታው ሸይጧን ሊፈትነው እንደሚችል አያውቅምና። እናም ወደ እሳት ጉድጓድ ይወረወራል።›› ቡኻሪ 7072 ፣ ሙስሊም 2617) በሌላ ሐዲስ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ወደ ወንድሙ መሳሪያ የደገነ ሰው፤ ትክክለኛ የስጋ ወንድሙ እንኳ ቢሆን ይህን ማድረጉን እስካልተወ ድረስ መልአክት በእሱ ላይ እርግማንን ይለምናሉ።›› (ሙስሊም 2616)
አዳኝ ሰው እራሱን እና ሌሎችን ለመጠበቅ የአደን ህገ ደንቦች እና የደህንነት ጥንቃቄዎችን ማወቅ አለበት። አዳኝ ውሾች ፣ የአደን እንስሳ ሞት እና የአስተራረድ ዘዴ ጋር በተያያዘ ልዩ ሸሪአዊ ብያኔ አለ።
መከልከሉን የሚጠቁም ማስረጃ ካልኖረ በቀር ምግብን መቋጠር እና መሰነቅ የተፈቀደ ነው።
እርም የተደረጉ (በጥብቅ የተከለከሉ) ምግብ እና መጠጦች
በሜዳ (በማሳ) ወይም በገበያ ቦታ ውስጥ የሚገኙ አትክልት እና ፍራፍሬዎች ሁሉ ለመብልነት የተፈቀዱ ናቸው። ነገርግን አንድ ሙስሊም ሰው ሊጎዳው የሚችል እና ስለ ደህንነቱ የማያውቀውን ነገር መመገብ የለበትም።