መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት መሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን መመስከር

"ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው” የሚለው ምስክርነት የሁለቱ ምስክሮች ሁለተኛ ክፍል ነው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ትርጉሙን እና መልእክቱን ይማራሉ.

  • "መሐመድ የአላህ መልእክተኛ ነው" የሚለውን ምስክርነት ትርጉም ማወቅ ።

«ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው» የሚለው ቃል ትርጉም

እንዲህ ብሎ መመስከር፥ የተናገሩትን አምኖ መቀበል፣ ትዕዛዛቸውን መፈፀምና ክልከላቸውን መታቀብ ማለት ነው፡፡ አላህንም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) በደነገጉትና ባስተማሩን መሠረት ብቻ ማምለክና መግገዛት ማለት ነው፡፡ ይሄ የሚከተሉትን ያጠቃልላል።

1 ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ሁሉንም ነገር አስመልክቶ የተናገሩትን እውነት ብሎ መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም፡-

١
ከህዋስ ስለራቁ ምስጢራዊ ነገሮች፣ ስለመጨረሻው ቀን፣ ስለጀነት ፀጋዎችና ስለ እሳት ቅጣት፣
٢
በእለተ ቂያማ ሰለሚከሰቱ ነገሮችና ምልክቶቻቸው እንዲሁም በመጨረሻው ዘመን ስለሚሆኑ ነገሮች፡-
٣
• ስላለፉና ስለቀደሙ ህዝቦች፣ በነቢያትና ጥሪ ባደረጉላቸው ህዝቦች መካከል ስለተፈጠሩት ነገሮች

2 ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ያዘዟቸውን ነገሮች መተግበርና ከከለከሉት ተግባራት መታቀብም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህም፡-

١
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) የሚያዝዙን ትዕዛዛት ከራሳቸው አፍልቀው ሳይሆን ከአላህ በሚገለፅላቸው ራዕይ አማካኝነት መሆኑን በእርግጥኝነት ማመን ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው፥ በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡” (አል-ኒሳእ፡80)
٢
እርሳቸው ከከለከሏቸው ሐራም ነገሮች፣ መጥፎና ጎጂ የሆኑ ሥነ-ምግባራትና ግብረ ገቦች መታቀብም ይኖርብናል፡፡ እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የከለከሉንም እውነታው ከእኛ ቢሰወርና ባናውቀውም ለአንዳች ጥበብ አላህ ፈልጎ ያደረገው መሆኑንና ለራሳችን ጥቅም መሆኑን ማመን ይኖርብናል፡፡
٣
ያዘዙንን መተግበራችን፣ ከከለከሉን መታቀባችን ዞሮ ዞሮ ለእኛ መልካም እንደሆነና በዚህም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ደስታን እንደሚያጎናፅፈን በእርግጠኝነት ማመን ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል …”ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልእክተኛውን ታዘዙ፡፡” (አሊ-ዒምራን፡132)
٤
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ትዕዛዝ ሆን ብሎ መጣስ ለቅጣት የሚዳርግ ተግባር መሆኑ ተገቢ ነገር መሆኑንም ማመን ይኖርብናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “…እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሉ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” (አል-ኑር፡63)

3 አላህን ማምለክ የሚኖርብን ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) በደነገጉት መልኩ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ዕውነታ ብዙ ነገሮችን የሚያካትት በመሆኑ ይህን ማረጋገጥ ተገቢነው፡፡ ይኽውም፡-

• አርዓያነታቸውን መከተል፡-

የአላህ መልእክተኛን (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና (የየእለት ተግባር) ፣ መመሪያና ህይወት በአጠቃላይ ንግግራቸውን፣ተግባራቸውንና አፅድቆታቸውን ጨምሮ በሁሉም የህይወት እርከናችን በአርዓያነት ልንከተለው ይገባል፡፡አንድ የአላህ ባሪያ የአላህ መልእክተኛን ሱንና ይበልጥ በአርዓያነት በተከተለ ቁጥር፥ ይበልጥ ወደ አላህ የተጠጋና ደረጃውም ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ አላህእንዲህ ይላል… “በላቸው አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋል፤ ኃጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነው፡፡”(አሊ-ዒምራን፡31)

• የተሟላ ህግ፡-

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ይዘው የመጡት ሃይማኖትና ህግጋት በሁሉም ረገድ ምሉዕና ጉድለት የሌለው ነው፡፡ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ.) ያልደነገጉትን የአመልኮ ተግባር በአዲስ መልክ መፍጠር ለማንም ሰው ቢሆን የተፈቀደ አይደለም፡፡

• አላህ የደነገገው ህግ በሁሉም ጊዜና ቦታ ተስማሚ ነው፡-

በአላህ መፅሐፍና በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና ውስጥ የተደነገገው ህግና ሥርዓት በሙሉ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ሁሉ ተስማሚ ነው፡፡ ሰዎችን ከምንም ካስገኛቸውና ከፈጠራቸው ጌታ በላይ ሰዎችን የሚጠቅም ነገር የሚያውቅም ማንም የለም፡፡

• ከሱንና ጋር ስምሙ መሆን፡-

አንድ የአምልኮ ተግባር አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከተፈለገ የአላህን ውዴታ ብቻ አስቦ (ነይቶ) መስራትና ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሱንና ጋር የተጣጣመ መሆኑ ግድ ይላል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል… “የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤መልካም ስራን ይስራ በጌታውም መግገዛት አንድንም አያጋራ በላቸው፡፡” (አል-ከህፍ፡110) በዚህ አንቀፅ ውስጥ «መልካም ሥራ» በሚል የተወሳው ከአላህ መልእክተኛ ሱንና ጋር ተጣጥሞ የተገኘ ስራ ማለት ነው፡፡

• ሃይማኖታዊ ተግባር መፍጠር ሃራም ነው፡-

አላህን ለማምለክ በሚል፥ የአላህ መልእከተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ያልደነገጉትንና ሸሪዓዊ ባልሆነ መንገድ አዲስ የአምልኮ ተግባር የፈጠረ ሰው፥ የነቢዩን መንገድ ተፃሮ የተገኘ በመሆኑ ወንጀለኛ ይሆናል፡፡ ስራውም ተመላሽና ተቀባይነት የሌለው ይደረጋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “… እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡” (አል-ኑር፡63) ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል“በዚህ ጉዳያችን ውስጥ ከርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ፤ ሥራው ተመላ ሽነው፡፡” (አል-ቡኻሪ፡2550 ሙስሊም 1718)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር