መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ኑዛዜ እና ውርስ

የእስልምና ህግ አንድ ሙስሊም ሰው ከሞተ በኋላ የሚፈፀም ኑዛዜ እንዲናዘዝ እስልምና ይፈቅድለታል፡፡ በእስልምና ህግ ውስጥ በጥበብ የተሞላ የውርስ ክፍፍል ስርአት አለ፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ኑዛዜ እና ከውርስ ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ፡፡

የትምህርቱ አላማ1 ስለ ኑዛዜ ምንነት ትማራላችሁ፡፡2 ስለ ኑዛዜ ክፍሎች እና አህካሞች ትማላችሁ፡፡3 ስለ ውርስ ትርጉም ትማራላችሁ፡፡

የኑዛዜ ትርጉም

ኑዛዜ፡ አንድ ሰው ከሞተ ወይም ከሞተች በኋላ የሆነ ነገር እንዲፈፀምለት ሃላፊነት የመስጠትት ጥያቄ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በገንዘቡ መስጅድ እንዲሰሩለት ኑዛዜ መስጠት ነው፡፡

ኑዛዜ

......የሆነ ነገር ያገኘ ሙስሊም ሰው ያገኘውን ነገር በተመለከተ ኑዛዜው ሳይፃፍ ሁለት ሌሊቶችን ማሳለፍ ተገቢ አይደለም፡፡ አብዱሏህ ቢን ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ኑዛዜየ ሳይፃፍ አንዲትን ሌሊት አሳልፌ አላውቅም፡፡›› (ቡኻሪ 2738 ፣ ሙስሊም 1627)

አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው ኑዛዜው የሚፈፈፀመው እና እዳው ሊከፈል የሚገባው ወራሾቹ ድርሻቸውን ከመከፋፈላቸው በፊት ነው፡፡ አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹በእሷ ከተናዘዘባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡›› (ሱረቱ ኒሳዕ 11)

የኑዛዜ ሁኔታዎች

ኑዛዜ የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉት፡፡

አስገዳጅ ኑዛዜ

አንድ ሙስሊም ሰው እገዳ ካለበት ወይም የገንዘብ መብት ካለው እና ይህን የሚያሳይ ማስረጃም ሆነ መረጃ ዶክመንት ከሌለው እነዚህን መብቶችን ለማስጠበቅ ኑዛዜ የግድ መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ምክኒያቱም አዳን መመለስ ግዴታ ነውና፡፡ ግዴታው ያለዚህ የማይፈፀም ከሆነም ይህ በራሱ ግዴታ ይሆናል፡፡

የተወደደ ኑዛዜ

ይህ የኑዛዜ አይነት አንድ ሙስሊም ሰው ከሞተ በኋላ ከገንዘቡ ከፊሉን ለበጎ አድራጎት ስራ እንዲውል የሚያደርግበት ነው፡፡ ለምሳሌ ለድሃ ዘመዶች ምፅዋት መስጠትን የመሰለ ነው፡፡ ይህም የተወሰኑ ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡

ሀ) ኑዛዜው ከወራሾቹ መካከል ለአንዱ መሆን የለበትም፡፡ አሏህ ቀድሞ የየድርሻቸውን አከፋፍሏቸዋልና፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ለአንድ ወራሽ ኑዛዜ የለውም፡፡›› (አቡዳውድ 3565 ፣ ትርሚዚ 2120፣ ኢብን ማጃ 2713)

ለ) ኑዛዜው የገንዘቡ ከአንድ ሶስተኛ ያነሰ መሆን ይገባዋል፡፡ የገንዘቡ አንድ ሶስተኛ መሆኑ የተፈቀደ ሲሆን ከዛ በላይ ከሆነ ግን የተከለከለ ነው፡፡ ከሶሃቦች መካከል አንዱ አንድ ሶስተኛውን ለመናዘዝ በፈሎገ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከለከሉና እንዲህ አሉ፡ ‹‹አንድ ሶስተኛ፤ አንድ ሶስተኛ በጣም ብዙ ነው፡፡›› (ቡኻሪ 2744 ፣ ሙስሊም 1628)

ሐ) ኑዛዜ የሚያደርገው ባለጠጋ እና ለወራሾቹ የሚተወው ገንዘብ በቂ መሆን አለበት፡፡ ሰኢድ ቢን አቢወቃስ (ረ.ዐ) ኑዛዜ ማድረግ በፈለገ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉት፡ ‹‹ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋቸው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው፡፡›› (ቡኻሪ 1295 ፣ ሙስሊም 1628)

3 የተጠላ ኑዛዜ

ኑዛዜ የሚያደርገው ሰው ትንሽየ ገንዘብ ኖሮት ወራሾቹ በጣም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ነው፡፡ ምክኒያቱም ወራሾቹን ገድቧቸዋልና ነው፡፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰአድ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ‹‹ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው፡፡›› (ቡኻሪ 1295 ፣ ሙስሊም 1628)

የተከለከለ ኑዛዜ

በእስልና ህግ የተከለከለን ነገር ኑዛዜ እንዲሆን መጠየቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ከወራሾቹ ለአንዱ በእድሜ ከፍ ላለው ልጁ እና ለሚስቱ እንዲወርሱት ፣ መቃብሩ ላይ ጉልላት እንዲሰራለት መጠየቅ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡

የተፈቀዳ የኑዛዜ መጠን

ከኑዛዜው አንድ ሶስተኛውን ለበጎ አድራጎት ስራ መስጠት የተፈቀደ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ መስጠት ግን የተከለከለ ነው፡፡ እንዲያውም መቀነሱ በላጭ ነው፡፡ ሰአድ ቢን አቢወቃስ (ረ.ዐ) እንዲህ ባለ ጊዜ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ሁሉንም ገንዘቤን ለበጎ አድራጎት ስራ እንዲውል ትቻለሁ አላቸው፡፡፡ እሳቸውም፡ ‹‹አይሆንም›› እኔም አልኳቸው፡ ግማሽስ፡፡ እሳቸውም፡ አይሆንም አሉ፡፡ እኔም አንድ ሶስተኛስ አልኳቸው፡፡ እሳቸውም፡ አንድ ሶስተኛ፤ አንድ ሶስተኛ ብዙ ነው፡፡ ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋቸው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው አሉ፡፡›› (ቡኻሪ 2742)

ወራሽ ለሌለው ሰው ከአንድ ሶስተኛው ይልቅ ሁሉንም ገንዘቡን ለማውረስ መናዝ የተፈቀደ ነው፡፡

ኑዛዜው የመፈፀም ብያኔ

የሟቹን ሰው ኑዛዜ መፈፀም ግዴታ ነው፡፡ ይህ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው ቅድመ ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ ኑዛዜውን የማይፈፅም ከሆነ ሃጢያት እየሰራ ነው፡፡ አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹ኑዛዜውን ከሰማ በኋላ የለወጠ ሰው፤ ሃጢያቱ በነዚያ በለወጡት ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ አሏህ ሰሚ እና አዋቂ ነውና፡፡›› (ሱረቱል በቀራ 181)

ውርስ

አንድ ሰው በህይወት እያለ የሰበሰበው ገንዘብ በሞተ ጊዜ የዛ ገንዘብ ባለቤት አይሆንም፡፡ ሆኖም የሟቹን ሰው እዳ ከከፈልን እና ኑዛዜውን ከፈፀምን በኋላ ውርሱ ለሚገባቸው ሰዎች ድርሻቸውን ምናከፋፍልበትን ህግ እስልምና ደንግጓል፡፡

ቁርአን እና የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ውርሱን በወራሾች መካከል አለመግባባት እና ቅራኔ በማይኖርበት አኳኋን የምናከፋፍልበትን ዘዴ ያብራራልናል፡፡ የእስልምና የውርስ ስርአት ከሁሉም የህግ ስርአቶች ሁሉ በላጭ እና በጥበብ የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም አንድ ሰው የአንድን ሐገር የህግ ስርአት እና የህዝቡን የአኗኗር ዘይቤ ሰበብ አድርጎ ይህን የሸሪአ የህግ ስርአት መቀየር አይፈቀድለትም፡፡ ለዚህም ነው ሃያሉ አሏህ ከውርስ አያ በኋላ እንዲህ ያለው፡ ‹‹እነዚህ የአሏህ ውሳኔዎች ናቸው፡፡ አሏህን እና መልዕክተኛውንም የሚታዘዙ ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል፡፡ ይህም ትልቅ ዕድል ነው፡፡›› (ሱረቱ ኒሳዕ 13)

በሟቹ ሰው ልጆች እና ዘመዶች በመካከላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክን እንዳይፈጠር ስለ ሸሪአ የውርስ ክፍፍል ስርአት ኡለማኦችን እና ፍቅሃዎችን መጠየቅ አለባቸው፡፡

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር