ትምህርት ስለ ቅዱስ ቁርኣን
የእነዚህ ርዕሶች ዋና አላማ ተማሪው የቅዱስ ቁርአንን እውነታዎች በአይነ ህሊናው እንዲያይ ፣ ትሩፋቶቹን ፣ ህግጋቱን እና ከእሱ ጋር ሊኖረን ስለሚገባው ምግባር እና ቃላቶቹ እንዴት እንደሚተረጎሙ ወይም እንደሚብራሩ እንዲያው እንዲረዳው የታሰበ ነው።
1 ስለ ቅዱስ ቁርአን እውነታዎች ፣ ስለ ክፍሎቹ እና ስለ ምዕራፎቹ ትማራላችሁ2 የቅዱስ ቁርአን የመሰብሰብ ሂደቶቹን ትማራላችሁ
18,727 ሌላ ተማሪ ይህን ትምህርት አጠናቀቀ
የዚህ ትምህርት ትርጉም በሚከተሉት ቋንቋዎች ይገኛል።
ቅዱስ ቁርአን
ሃያሉ አሏህ ቁርአን የገለጠው ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላጭ ለሆኑ እና ለነብያት መደምደሚያ ለሆኑት ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነው። ቁርአን ለሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እና ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገሪያ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "በእርግጥ ከአሏህ ዘንድ ብርሃን እና ገላጭ መጽሐፍ መጣላችሁ። አሏህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገድ በእሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛውም መንገድ ይመራቸዋል።" (ሱረቱል ማኢዳ 15-16)
የቅዱስ ቁርአን ፍች
ቅዱስ ቁርአን ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለጠላቸው ተአምራዊ ቃል ነው። ቁርአን በፋቲሃ ጀምሮ በሱረቱ አናስ የሚያበቃ ሲሆን ይህን በማንበብም አሏህ ይመለክበታል።
የቅዱስ ቁርአን መገለጥ
ቁርአን መጀመሪያ ለነብዩ (ሰ.ዐወ) የተገለጠው በረመዷን ውስጥ በለይለቱል ቀደር (በውሳኔዋ ሌሊት) ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "ያ በእሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩ ገላጭ (አንቀፆች) ሲሆኑ ቁርአን የወረደበት የረመዷን ወር ነው።" (ሱረቱል በቀራ 185)
የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች
የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች 114 ናቸው። ሆኖም የመጀመሪያው ምዕራፍ አል-ፋቲሃ ሲሆን የመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ አል-ናስ ነው።
የቁርአን ክፍሎች 30 ሲሆኑ ሂዝቡ ደግሞ 60 ናቸው።
የቁርአን ጽህፈት እና አሰባሰብ
የቁርአን ጽህፈት እና አሰባሰብ ሶስት ደረጃዎች አሉት።
የመጀመሪያው ደረጃ፡ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን
በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ትኩረቱ የነበረው ከመፃፍ ይልቅ ሽምደዳ ላይ ነው። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የመሸምደድ አቅማቸው እና ለመሸምደድ የነበራቸው ፍጥነት ጠንካራ በመሆኑ ፣ የጽሐፊዎች እና የመፃፊያ ዘዴ ባለመኖሩ ምክኒያት በመጽሐፍ መልክ አልተሰበሰበም ነበር። ነገርግን አንድ አንቀፅ በሰሙ ጊዜ ይሸመድዱ እና ባገኙት የዘንባባ ዛፍ ጉማጅ ፣ ብራና እና ድንጋይ ላይ ይፅፉ ነበር።
ሁለተኛው ደረጃ፡ በአቡበክር (ረ.ዐ) ጊዜ
በሂጅራ በአስራ ሁለተኛው አመት በየማማ ጦርነት ጊዜ ብዙ ቃሪኦች (አንባቢዎች) በመገደላቸው ምክኒያ እና ቁርአን እንዳይጠፋ በማሰብ ቁርአኑ እንዲሰበሰብ አቡበክር (ረ.ዐ) አዟል።
ዘይድ ኢብኑ ሳቢት(ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የየማማ ሰዎች (በሙሰይሊማ) በተገደሉ ጊዜ አቡበክር (ረ.ዐ) መልዕክት ላከብኝ። እኔም ወደ እሱ ሄድኩ። እናም ኡመር ኢንኑ ኸጧብ ከእሱ ጋር ተቀምጦ አገኘሁት። አቡበክር (ረ.ዐ) እንዲህ አለኝ፡ ‹‹በየማማ የጦር ሜዳ ቁርአን አንባቢዎች ላይ የደረሰው ሞት የከፋ እንደሆነ ኡመር (ረ.ዐ) ነግሮኛል። በሌላ የጦር ሜዳ ተጨማሪ የቁርአን አንባቢዎች እንዳይሞቱ እና ከፍተኛው የቁርአን ክፍል እንዳይጠፋ እሰጋለሁ። ሆኖም ቁርአን እንዲሰበሰብ አቡበክር ትዕዛዝ እንዲያስተላልፍ ሃሳብ አቀረበ። ለኡመርም እንዲህ አልኩት፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ያላደረጉትን አንተ ታደርጋለህን? አልኩት። ኡመርም ያ ጥሩ ነው አለ። አሏህ ለዚህ ነገር ደረቴን እስከከፈተልኝ ጊዜ ድረስ ኡመር ያቀረበውን ሃሳቡን እንድቀበል ጎተጎተኝ። ኡመር የተረዳውን ሃሳብ እኔም መረዳት ጀመርኩ። ከዚያም አቡበክር ‹‹አንተ ጠቢብ ወጣት ነህ፤ በአንተም ላይ አንዳችም ጥርጣሬ የለንም። ለአሏህ መልዕክተኛ የተገለጠላቸውን መለኮታዊ ራዕይ ትፅፋለህ። ሆኖም የተበታተኑ የቁርአን የእጅ ጽሁፎችን አፈላልገህ በአንድ መጽሐፍ አሰባስበው አለኝ። በአሏህ ይሁንብኝ! ከተራራዎቹ አንዱን እንዳንቀሳቅስ ቢያዙኝ ይህን የቁርአን እንዳሰባስብ ካዘዙኝ የበለጠ የሚከብድ አይመስለኝም። ከዚያም ለአቡበክር እንዲህ አልኩት፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያላደረጉትን ነገር እናንተ ታደርጋላችሁን›› አልኩት። አቡበክርም፡ ‹‹በአሏህ ይሁንብኝ ጥሩ ነው›› ሲል መለሰልኝ። አሏህ የአቡበክር እና የኡመርን ደረት እንደከፈተው የእኔንም ደረት እስከከፈተልኝ ድረስ አቡበክር ሃሳቡን እንድቀበል ጎተጎተኝ። ከዚያም ቁርአንን መፈለግ ጀመርኩ። የሱረቱ ተውባን የመጨረሻውን አንቀፅ ከአቢ ኸዛኢም አል-አንሷሪ እንጅ ከእሱ በቀር ከሌላ ሰው ማግኘት እስካልቻልኩበት ጊዜ ድረስ በተለያዩ ነገሮች ላይ በዘንባባ ዛፍ ጉማጆች ፣ በነጭ ድንጋይ ላይ እና በልባቸው ካስቀመጡ (ከሸመደዱ) ሰዎች አሰባሰብኩ። ከዚያም ሙሉ የቁርአን የእጅ ፅሁፍ ቅጅ አቡበክር እስኪሞት ድረስ ከእሱ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም ኡመር እስኪሞት ድረስ ከእሱ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም የኡመር ልጅ ከሆነችው ሐፍሷ ጋር ተቀመጠ።›› (ቡኻሪ 4986)
ሶስተኛው ደረጃ፡ በኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዐ) ዘመን
በኡስማን ቢን አፋን (ረ.ዐ) የአስተዳደር ዘመን የእስልምና የግዛት ወሰን ተስፋፍቷል። የሁሉም ሐገር ሰዎች ከሶሃቦች መካከል ያስተማሯቸውን የቁርአን የአነባበብ ዘይቤ ተቀበሉ። በቅዱስ ቁርአን የአነባበብ ዘይቤ ብዝሃነት ምክኒያት እና ቅዱስ ቁርአንን ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያልሰሙ ሰዎች እንዳይሳሳቱም ተፈራ። እናም ሰዎች በሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ላይ እንዳይለያዩ ፣ እንዳይጨቃጨቁ እና እንዳይበታተኑ በማሰብ ኡስማን (ረ.ዐ) ሰዎች ሰዎች በአንድ የቁርአን ቅጅ እንዲሰባሰቡ አዘዘ።
አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ሁዘይፋ ቢን አልየማን ወደ ኡስማን መጣ። በአርመን ወረራ ወቅት የሶሪያን ሰዎች ሲዋጋ ፣ አዘርባይጃን ደግሞ ከኢራቅ ሰዎች ጋር ሲዋጉ በነበራቸው የአነባበብ ልዩነት ምክኒያት ኹዘይፋ ፈራ። እናም ኹዘይፋ ለኡስማን እንዲህ አለው፡ ‹‹የሙዕሚኖች አዛዥ ሆይ! አይሁዳዎች እና ክርስቲያኖች እንደተለያዩት ሁሉ ይህ ኡማ በመጽሐፉ ከመለያየታቸው በፊት ተረዳቸው አለው። እናም ‹‹በመጽሐፍ መልክ እናበዛቸው ዘንድ ቅጅውን ላኪልን፤ ከዚያም መልሰን እንልክልሻለን›› ሲል ኡስማን ወደ ሐፍሷ መልዕክት ላከ። ሐፍሷም ወደ ኡስማን ቅጅውን ለከች። ከዛም ዘይድ ቢን ሳቢት ፣ አብዱ ረህማን ቢን አል-ሐሪስ ቢን ሂሻምን በቁርአን ማባዛት ሂደት ውስጥ እንዲካተቱ እና ቁርርአኑን እንዲያባዙ አዘዛቸው።›› (ቡኻሪ 4987)