መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የቁርአን ማብራራት እና ማስተንተን

የቅዱስ ቁርአን ትርጉም ትንተና እና ማብራራት ሁለት ትልቅ ተጋባራቶች ናቸው። ይህም ሃያሉ አሏህ አንድን ሙስሊም ሰው ከቃሉ የፈለገውን ነገር እንዲያውቅ እና በእሱም እንዲሰራበት ያስችለዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ማስተንተን ምን ማለት እንደሆነ ፣ ስለ ተፍሲር (ትንተና) ምንነት እና ጠቀሜታ ትማራላችሁ።

1 የቁርአን ትርጉም ትንተና እና በቁርአን ማስተንተን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ2 የቁርአን ማብራሪያ እና በእሱ ማስተንተን ያለው ደረጃ እና አስፈላጊነቱን ታውቃላችሁ3 የቅዱስ ቁርአን ትርጉም የሚብራሩበትን መንገዶች ታውቃላችሁ4 አስፈላጊ የሆኑ እና የታወቁ የቁርአን ትንተና መጽሐፍትን ታውቃላችሁ

የቅዱስ ቁርአን ትንተና እና በቁርአን ማስተንተን

ሁሉም ሙስሊም ሰው ቁርአንን በትክክል ማንበብ ፣ በእሱ ማስተንተን ፣ ስለ ትርጉሞቹ ፣ ስለ ትዕዛዛቱ እና ስለ ክልከላዎቹ ማሰብ ፣ ማብራሪያውን እና ህግጋቱን መማር አለባቸው። የዚችን አለም እና የመጭውን አለም ደስታ ለማግኘት በእሱ መስራት አለባቸው።

የተደቡር (የማስተንተን) ትርጉም

ማስተንተን፡ ከቁርአን አንቀፆች ጋር መቆም ፣ በእነሱ ላይ ማስተንተን እና ጥቅም ላይ ለማዋል ከእነሱ ጋር ቁርኝት መፍጠር ነው።

በቅዱስ ቁርአን አንቀፆች ላይ የሚያስተነትን ሰው ማሰላሰሉ (ማስተንተኑ) እና መረዳቱ ትክክል ይሆን ዘንድ አጠቃላይ ትርጉሙን ማወቅ አለበት።

በቁርአን ማስተንተን ያለው ደረጃ

ሁሉም ሙስሊሞች በቁርአን ማስተንተን ፣ አንቀፆቹን እና ትርጉሙን መረዳት ፣ በእነሱም መሰረት መኖር አለባቸው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ወደ አንተ ያወረድነው የተባረከ መጽሐፍ ነው፤ በአንቀፆቹ ላይ እንዲያስተነትኑ እና የአዕምሮ ባለቤቶች እንዲያስታውሱ ነው።" (ሱረቱ ሷድ 29) አሏህ እንዲህ አለ፡ "በቁርአን አያስተነትኑምን? ወይስ (እሱን ለመረዳት) ልቦቻቸው ተቆለፉ?" (ሱረቱ ሙሐመድ 24)

የተፍሲር ትርጉም

ተፍሲር የቅዱስ ቁርአን ትርጉም ማብራሪያ ነው።

የተፍሲር (የትንተና) ጠቀሜታ እና አስፈላጊነት

የተፍሲር እውቀት (ሳይንስ) በጣም ጠቃሚ ከሆኑ እውቀቶች ውስጥ አንዱ ነው። ምክኒያቱም ከሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ጋር የተያያዘ ነውና። እንዲሁም የአሏህን ቃል ለመረዳት ያስችላል። በተፍሲር እውቀት የቅዱስ ቁርአን ትርጉሞች ይታወቃሉ። ሙስሊም ሰው መልካም ስራ እንዲሰራ ይረዳዋል፤ የአሏህን ውዴታ እና ጀነት ለማግኘት ያስችለዋል። ይህም በቅዱስ ቁርአን የተጠቀሱ ትዕዛዛዘትን በመፈፀም ፣ ክልከላዎቹን በመከልከል ፣ ከታሪኮቹ ትምህርት በመውሰድ ፣ በዜናዎቹ በማመን ነው። በተፍሲር እውቀት አንድ ሰው እውነትን ከውሸት መለየት ይችላል፡፡ ከአንቀፆቹ ትርጉም እና ከሚያመለክቱት እውነተኛ ነገር ግራ እንዳይጋባም ይረዳዋል።

ሶሃቦች የቁርአን ትርጉም እና ተፍሲር ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለማወቅ የነበራቸው ትኩረት

እነዚያ ብርቅየ ሶሃቦች ከቁርአን ለመረዳት የከበዳቸው ነገር ሲኖር ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይጠይቁ ነበር። ይህ አንቀፅ "እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን በበደል ያልሸፈኑ፤" (ሱረቱል አንአም 82) የሚለው በተገለጠ ጊዜ አብዱሏህ ቢን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች ይህ ከብዷቸው ነበር። እነሱም፡ ማነው ከእኛ ውስጥ እራሱን ያልበደለ? አሉ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹እንደምታስቡት አይደለም፤ ነገርግን ሉቅማን ለልጁነ እዳለው ነው አሉ። ‹‹ልጄ ሆይ! በአሏህ ላይ አታጋራ (ባላንጣ አታብጅ)፤ በእርግጥ ሽርክ (በአሏህ ላይ ማጋራት) ትልቅ በደል ነውና።›› (ሱረቱ ሉቅማን 13) (ቡኻ 6937 ፣ ሙስሊም 124)

የቅዱስ ቁርአን ትርጉም እና ማብራሪያ ማጣቀሻ መንገዶች

١
የቁርአን ተፍሲር በቁርአን (ቁርአንን በቁርአን መተንተን)
٢
ቁርአንን በሱና መተንተን
٣
የሶሃቦች ትንተና
٤
የታቢኦች (ከሶሃች በኋላ የነበሩ ትውልዶች) ትንተና

አንደኛ፡ ቁርአንን በቁርአን መተንተን

ቁርአን ያወረደው (የገለጠው) ሃያሉ አሏህ በመሆኑ በእሱ ሊያሳውቀን የፈለገውንም አዋቂ ነው።

ነው። ለምሳሌ፡ ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "አዋጅ! የአሏህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ አያዝኑምም። እነሱም እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩት ናቸው።" (ሱረቱ ዩኑስ 62-63) በእርግጥ የአሏህ ወዳጆች የሚለው በዚህ አንቀፅ ‹‹እነዚያ ያመኑ እና ይፈሩት የነበሩት›› በሚል ተብራርቷል።

ሁለተኛ፡ የቁርአን ትንተና በነብዩ ሱና

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከአሏህ የተገለጠላቸውን ራዕይ በእሱ በኩል ለሰዎች እንዲያስተላልፉ የተመረጡ በመሆናቸው ነው። አሏህ በቃሉ ማለት ስለፈለገው ነገር ከሁሉም ሰው በላይ ያውቃሉና ነው።

ለምሳሌ፡ ቀስት ውርወራ ጥንካሬ እንደሆነ የተናገሩበት የኡቅባ ቢን አምር (ረ.ዐ) ዘገባ ያሳያል።፡ ‹‹ኡቅባ እንዲህ አለ፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሚንበር ላይ ሆነው እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ ‹‹ከሃይል በእነሱ ላይ የቻላችሁትን ሁሉ አዘጋጁ።›› (ሱረቱል አንፋል 60) ‹‹አዋጅ ጥንካሬ ቀስትትን ያካትታል፤ አዋጅ ጥንካሬ ቀስትን ያካትታል፤ አዋጅ ጥንካሬ ቀስትን ያካትታል።›› (ሙስሊም 1917)

ሶስተኛ፡ የሶሃቦች ማብራሪያ

በዚህ ጉዳይ ላይ ሶሃቦች የበለጠ እውቀት ያላቸው ነበሩ። ምክኒያቱም ለቁርአን እና ላለፉበት ሁኔታ ምስክሮች በመሆናቸው ነው። እንዲሁም የተሟላ ተረድኦ ፣ ትክክለኛ እውቀት እና የመልካም ስራ ባለቤቶች በመሆናቸው ነው።

ለዚህ ምሳሌ ተከታዩ የአሏህ ንግር ነው። "ብትታመሙ ወይም በጉዞ ላይ ብትሆኑ ወይም ከእናንተ አንዱ ለተፈጥሮ ጥሪ መልስ ሰጥቶ (ተፅዳድቶ) ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩ" (ሱረቱ ኒሳዕ 43) በጦበሪ ተፍሲር (ማብራሪያ) መሰረት ‹‹ብትነካኩ›› የሚለው የግብረ ስጋ ግኑኝነት እንደሆነ ተገልፃል። (389/8) ኢብን አባስ (ረ.ዐ) ትክክል ነው ብሏል።

አራተኛ፡ የታቢኦች ተፍሲር

ታቢኦች ከሶሃቦች በኋላ የነበሩ በላጭ ህዝቦች በመሆናቸው እና ከፍላጎቶቻቸው የተጠበቁ በመሆናቸው ምክኒያት የሶሃቦችን የቁርአን ትንተና ጠብቀው አቆይተዋል። ታቢኦች ከእነሱ በኋላ ከመጡ ህዝቦች የበለጠ ቁርአንን ለመረዳት የቀረቡ ነበሩ።

የቁርአን ማብራሪያ በተመለከተ የሙስሊም ሰው ግዴታ

ቁርአንን ለመረዳት ፣ ትጉሙን ለማወቅ የሆነ ነገር አሻሚ የሆነበት ሰው የተፍሲር ማጣቀሻ መጽሐፍትን እና የቁርአን አንቀፆችን ትርጉም በመግለፅ እና በማብራራት የታወቀ ሊቃውንትን ማብራሪያ መመልከት አለበት።

የቅዱስ ቁርአን ትንተና ለሁሉም ሙስሊም አይደለም። ይልቁንም የትንታኔው እውቀት ላላቸው ሰዎች ነው። ሆኖም እውቀቱ የሌላቸው ሙስሊሞች ያለ እውቀት ወደዚያ መሄድ የለባቸውም። ሙፈሲሩ (ተንታኙ) የሚያብራራው በሃያሉ አሏህ ስም ነው። በቃሉ ማስተላለፍ ለፈለገው ነገር ምስክር ነው። ይህን ምስክርነትም በስራው አጉልቶ ያሳያል። ስለ አሏህ ያለ እውቀት እንዳይነገር እና በከለከለው ነገር ውስጥ እንዳይወድቅ ፣ ለፍርድ በመቆሚያዋ ቀን እንዳይዋረድ በመስጋት ይጠነቀቃል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ጌታየ እርም ያደረገው መጥፎ ስራዎችን ፣ ከእሷ የተገለፀውን እና የተደበቀውን ሃጢያትንም ፣ ያለ አግባብ መበደልን ፣ በእሱ ማስረጃ ያላወረደበትን በአሏህ ማጋራታችሁን እና በአሏህ ስም መናገራችሁ ብቻ ነው በላቸው።" (ሱረቱል አዕራፍ 33)

የቁርአን ተፍሲር ጠቃሚ መጽሐፍት

የቁርአን ተፍሲር ማብራሪያ ተብለው የተለዩ ብዙ መጽሐፍት አሉ። ሁሉም በቅቡልነታቸው ተመሳሳይ ደረጃ ላይ ባለመሆናቸው የትንተና ህግጋትን አጥብቆ የተከተለን ጽሐፊ ማብራሪያ ላይ መደገፍ አለባቸው። ከነዚህ የታወቁ ስራዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

ወሳኝ የተፍሲር መጽሐፍት

١
ጃሚዕ አል-በያን የቁርአን ማብራሪያ በኢማም ቢን ጀሪር አጦበሪ
٢
የቅዱስ ቁርአን ማብራሪያ በኢማሙ ኢብን ከሲር አዲመሽቂ
٣
ተይሲር አል-ከሪም አረህማን በአልመናን በሼህ አብዱረህማን አሰአዲ
٤
ቀላል ማብራሪያ በእውቅ ሊቃውንቶች፡ አሳታሚ ንጉስ ፋህድ የቁርአን ህትመት፤ መዲና

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር