የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት
የሰው ልጆች መልዕክተኞች ያስፈልጋቸዋል
ከሃያሉ አሏህ ጥበብ ውስጥ ለሁሉም ኡማ (ህዝብ) ያወረደውን ራዕይ እና መመሪ የሚያብራሩ አስጠንቃቂ ነብያትን ማድረጉ ነው። ይህም በዚች አለም ሆነ በመጭው አለም ህይወት ያለውን ሁኔታ የሚያስተካክሉበት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲገህ አለ፡ "ማንኛውም ህዝብ በውስጡ አስፈራሪ (አስጠንቃቂ) ያላለፈበት የለም።" (ሱቱ ፋጢር 24)
በዚህ አለም ሆነ በመጭው አለም ህይወት ወደ ደስታ እና ፈላህ (ደህንነቱ የሚረጋገጥበት) መንገድ የለም በነብያቶች ቢሆን እንጅ። ልክ እንደዚሁ ጥሩ እና መጥፎውን በዝርዝር ለመለየት የሚያስችል መንገድ የለም በእነሱ በኩል ቢሆን እንጅ። የሃያሉ አሏህ ውዴታ የሚገኘውም በእነሱ እጅ ነው። መልካም ቃላት ፣ መልካም ስራዎች እና ውብ ፀጋዎች የሚገኙት ከአስተምሮታቸው እና ይዘውት ከመጡት ነገር ነው።
ነብዩ ሙሐመድ የአሏህ ነብይ አና መልዕክተኛ መሆናቸውን ማመን
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህ አገልጋይ እና መልዕክተኛ መሆናቸውን ፣ ቀደምትም ሆኖ የመጨረሻው ዘመን ትውልዶች የበላይ መሆናቸውን ፣ የነብያት መደምደሚያ (ማብቂያ) መሆናቸውን ፣ መልዕክቱን እንዳደረሱ ፣ አማናውን (አደራውን) እንደጠበቁ ፣ ኡማውን እንደመከሩ ፣ በአሏህ መንገድ እውነተኛ መታገልን እንደታገሉ እናምናለን።
ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ ነው።" (ሱረቱል ፈትህ 29)
በነገሩን ማመን ፣ ያዘዙትን መታዘዝ ፣ የከለከሉትን እና የገሰፁትን መከልከል እና መራቅ ፣ በሱናቸው መሰረት አሏህን ማምለክ እና አርአያነታቸውን መከተል አለብን።
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያቶች እና የመልዕክተኞች ሁሉ መደምደሚያ ናቸው። ከእሳቸው በኋላ ነብይ የለም። የእሳቸው መልዕክት ከሳቸው በፊት የነበሩ ሰማያዊ መልዕክቶች መደምደሚያ (ማብቂያ) ነው። እንዲሁም ሃይማኖታቸው የሃይማኖቶች ሁሉ ማብቂያ ነው።
ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንዳችሁም አባት አይደለም። ነገርግን የአሏህ መልዕክተኛ እና የነብያቶች ማብቂያ ነው።" (ሱረቱል አህዛብ 40)
አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ "የእኔ እና ከእኔ በፊት የነበሩ ነብያት ምሳሌ ልክ ቤቱን አሳምሮ እና አስውቦ እንደ ሰራ ሰው ሲሆን ጠርዝ (ዳር) ላይ ካለች የጡብ ቦታ በቀር አሉ። እናም ሰዎች ተዘዋውረው አይተው እያደነቁ ‹‹ይሄን ጡብ ለምንድን ነው ያደረከው?›› አሉ። እሳቸውም፡ እኔ ጡቡ ነኝ፤ እኔም የነብያቶች ማብቂያ ነኝ›› አሉ።" (ቡኻሪ 3535)
የመልዕክተኞች እና የነብያ ፈርጥ
ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የነብያቶች ሁሉ ምርጥ ፣ የፍጡራኑ ሁሉ ምርጥ እና ከሃያሉ አሏህ ዘንድ በደረጃ ከሁሉም የላቁ ናቸው። አሏህ ደረጃቸውን ከፍ አድርጎታል። አሏህ ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላጭ ያደረጋቸው ሲሆን ከአሏህ ዘንድ ትልቁን ክብር የያዙ ናቸው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህም በአንተ ላይ መጽሐፉን እና ጥበቡን አወረሰ። የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ። የአሏህ ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው።" (ሱረቱ ኒሳዕ 113) አሏህ እንዲህ አለ፡ "መወሳትህን ለአንተ ከፍ አደረግንልህ።›› (ሱረቱል ኢንሽራህ 4)
የአደም ልጆች ሁሉ አለቃ ፣ መቃብራቸው የሚከፈተው የመጀመሪያው ሰው ፣ ምልጃ የሚፈቀድላቸው የመጀመሪያው አማላጅ ፣ ለፍርድ በመቆሚያዋ ቀን የምስጋና ባንድራ በእጃቸው የሚኖር ፣ የሲራጥን መንገድ የሚሻገሩ የመጀመሪያው እና በመጀመሪያ የጀነት በር የሚያንኳኩ እና ወደ እሷም የሚገቡ የመጀመሪያው ሰው እሳቸው ናቸው።
ሃያሉ አሏህ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የላካቸው ለአለማት እዝነት አድርጎ ነው። መልዕክታቸው ለሁሉም የሰው ልጆች እና ለጅን ዘሮች ነው። መልዕክታቸውም ለሰው ልጅ በሙሉ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ለአለማት እዝነት አድርገን እንጅ አላክንህም።" (ሱረቱል አንቢያ 107)
ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ለሰው ልጅ በሙሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን እንጅ አላክንህም።›› (ሱረቱ ሰበዕ 28) "እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለሁላችሁም (የተላኩ) የአሏህ መልዕክተኛ ነኝ በላቸው።" (ሱረቱል አዕራፍ 158)
ሃያሉ አሏህ ለአለማት እዝነት አድርጎ የላካቸው ለሁለቱ የሰው እና የጅን ዘሮች በሙሉ ከሽርክ ፣ ከክህደት እና ከድንቁርና አውጥተው ወደ እውቀት ፣ ኢማን (እምነት) እና ንፁህ ወደ ሆነው የአሃዳዊነት ብርሃን እንዲያሻግሯቸው ነው። በዚህም የአሏህን ምህረት ፣ ውዴታ ማግኘት እና ከቅጣቱ እና ከቁጣው መዳን ይችላሉ።
በእሳቸው ማመን እና መልዕክታቸውን የመከተል ግዴታ
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክት ከእሳቸው በፊት የነበሩ መልዕክቶችን ሁሉ ሽሯል። አሏህ ሃይማኖትን ከማንም አይቀበልም ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) የተከተለ ቢሆን እንጅ። እንዲሁም የጀነት ሃሴት (ፍፁም ደስታ) አያገኝም መንገዳቸውን በመከተል ቢሆን እንጅ። ምክኒያቱም ከነብያቶች ሁሉ በጣም የተከበሩ ፣ ህዝባቸው ከህዝቦች ሁሉ በላጭ የሆኑ እና ሸሪአቸው ከሸሪአዎች (ከህጎች) ሁሉ ፍፁም እና ሙሉ የሆነ ነውና።
አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከእስልምና ውጭ ሌላን ሃይማኖት የፈለገ ሰው ተቀባይነት የለውም። በመጭው አለም ከከሳሪዎች አንዱ ይሆናል።" (ሱረቱል ኢምራን 85)
አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፡ ‹‹የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ይሁንብኝ! በዚህ ኡማ ከአይሁድ ወይም ከክርስቲያን የተላኩበትን ነገር ሰምቶ ሳያምን የሞተ ሰው የለም ከጀሐነም ጓዶች አንዱ እሱ ቢሆን እንጅ ብለዋል።›› (ሙስሊም 153)
መልዕክታኛነታቸውን ያሚያመላክቱ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተአምራቶች
የላቀው እና የተወደሰው አሏህ ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለመልዕክታቸው እና ለነብይነታቸው ምስክር እና ማስረጃ የሚሆኑ አስደናቂ ተአምራትን እና ምልክቶቸፍን ሰጥቷቸዋል። ከእነዚህ ተአምራት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
ረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ) ከተሰጡት ምልክቶች (አያት) ውስጥ ትልቁ ነፍስን እና አዕምሮን የሚያወራው ቁርአን ሲሆን እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የማይቀየር እና የማያለዋወጥ ቋሚ ምልክት (ተአምር) ነው። በቋንቋው እና በአሰራሩ ፣ በህግጋቱ ፣ በፍርዱ እና በዜናው የምንግዜም ተአምር ነው።
አሏህ እንዲህ አለ፡ "የሰው ልጆች እና ጅኖች (ጋኒኖች) የዚህን ቁርአን አምሳያ ለማምጣት ቢሰባሰቡ እና ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆኑ እንኳ አምሳያውን አያጡም በላቸው።" (ሱረቱል ኢስራዕ 88)
አሏህ እንዲህ አለ፡ "ሰአቲቱ (የትንሳኤዋ ቀን) ተቃረበች ፣ ጨረቃም ተሰነጠቀች ፣ ተአምርንም ቢያዩ ‹ከእምነት› ይዞራሉ፤ ይህማ ዘውታሪ ድግምት ነውም ይላሉ።" (ሱረቱል ቀመር 1-2) ይህ የጨረቃ መሰንጠቅ (መከፈል) የተከሰተው በእሳቸው (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ዘመን ሲሆን ቁረይሾች እና ሌሎችም ተመልክተውት ነበር።
ከእሳቸው ጋር የነበሩ ሰዎች ከምግቡ እና ከፍርፋሪው በልተዋል። ከሰሙራ ቢን ጁንዱብ የመጣው ይሁ ሲሆን እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሁነን እያለ አንድ ሳህን ገንፎ ይዘው መጡ። እንዲህ አለ፡ ‹‹እሳቸውም በሉ፤ ሰዎቹም በሉ። የቀትር ሰአት እስኪደርስ ድረስ ሰዎቹ አዘዋወሩት፤ ሁሉም ሰዎችም ይበላሉ ይነሳሉ። እናም ሰዎች ይመጣሉ፤ እረስ በእርስም ይተካካሉ።›› (ሙሰነድ አህመድ 20135)
ያልታዩ ነገሮች አስመልክቶ የተነገሯቸው ነገሮች ይከሰታሉ። ከተናገሩትም ብዙው ተከስቷል። ከተናገሩትም ነገሮች እስካሁን ድረስ ሲከሰቱ እናያለን።
አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) የበድር ሰዎችን ታሪክ አስመልክቶ እንዲህ አለ፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ከጦርነቱ በፊት) ታገይ የበድር ሰዎችን አሳዩን። የአሏህ ፈቃድ ከሆነ እገሌ እና እገሌ የሚሞቱበት ቦታ ይሆናል አሉ። ኡመር እንዲህ አሉ፡ ከእውነት ጋር በላከው (አሏህ) ይሁንብኝ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የጠቆሙላቸውን የመሞቻቸውን ቦታ አልሳቱም።›› (ሙስሊም 2873)
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በህይወታቸው ላይ ያላቸው መብት ብዙ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።
1 በነብይነታቸው ማመን
በነብይነታቸው ፣ በመልዕክተኝነታቸው እና መልእክታቸው ከእሳቸው በፊት የነበሩ መልዕክቶችን ሁሉ የሻረ መሆኑን ማመን ነው።
2 ተሰዲቁሁ (የነቢዩን ንግግር እውነቱን ነው ብሎ መቀበል)
የተናገሩትን ማመን ፣ ያዘዙትን ነገር መታዘዝ ፣ የከለኩትን መከልከል እና በእሳቸው መንገድ አሏህን መገዛት ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "መልዕክተኛው የሰጣችሁን ነገር ያዙ፤ የከለከላችሁንም ነገር ተከልከሉ።" (ሱረቱል ሐሽር 7)
3 ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያመጡትን መቀበል
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዘውት የመጡትን ነገር መቀበል ፣ ሱናቸውን መተግበር እና መመሪያቸውን የአክብሮት እና የውዳሴ ስጦታ ማድረግ በእኛ ላይ ግዴታ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "በጌታህ እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስኪያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከሚያገኙ እና ፍፁም መታዘዝን እስኪታዘዙ ድረስ አያምኑም።" (ሱረቱ ኒሳዕ 65)
4 የእሳቸውን (ሰ.ዐ.ወ) ትዕዛዝ ከመጣስ መጠንቀቅ
ትዕዛዛቸውን ከመጣስ መጠንቀቅ አለብን። ምክኒያቱም ትዕዛዛቸውን መጣስ ጥመት ፣ መሳሳት እና አሳማሚ ቅጣት የሚያስከትል ነውና። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።" (ሱረቱ ኑር 63)
5 ውዴታን ከሌላ ሰው በፊት ለእሳቸው ማደረረግ
አንድ ሰው እራሱን ፣ ልጆቹን ፣ ወላጆቹን እና ሌሎች ፍጡራንን ከሚወደው በላይ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ውዴታ ማስቀደም በእሱ ላይ ግዴታ ነው። አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹አንዳችሁም አላመናችሁም ከወላጆቹ ፣ ከልጆቹ እና ከሌሎች ሰዎች ሁሉ በላይ አብልጦ እስኪወደኝ ድረስ።›› (ቡኻሪ 15) በሌላ ዘገባ ደግሞ ኡመር ኢብን ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! አንቱ ለእኔ ከሁሉም ነገር በላይ ተደዳጅ ነሁ፤ ከነፍሴ (ከእራሴ) በቀር›› አላቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ‹‹አይደለም! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ! ከነፍስህ (ከእራስህ) በላይ ለአንተ ተወዳጅ እስክሆን ድረስ ነው›› አሉት። ኡመርም አለ፡ ‹‹በአሏህ ይሁንብኝ አሁን ከነፍሴም በላይ ለእኔ ተወዳጅ ነሁ።›› ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሁኑኑ ኡመር አሉት።›› (ቡኻሪ 6632)
6 መልዕክቱን እንዳስተላለፉ ማመን
መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) መልእክቱን ሙሉ በሙሉ አስተላልፈዋል ፣ አደራቸውን ተወጥተዋል ፣ ህዝባቸውንም መክረዋል ብሎ ማመን ያስፈልጋል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ። ፀጋየንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ። ከሃይማኖትም እስልምናን ለእናንተ ወደድኩ።" (ሱረቱል ማኢዳ 3)
ከዚህ በተጨማሪ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦች በትልቅ ስብስቦች ላይ እና ሐጀተል ወዳዕ (የስንብት ሐጅ) በሐጅ ወቅት መልዕክቱን እንዳደረሱ መስክረዋል። በጃቢር ሐዲስ ውስጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ እንዳሉ ተዘግቧል፡ ‹‹ስለ እኔ በተጠየቃችሁ ጊዜ፤ ስለ እኔ ምነድን ነው የምትሉት? አሉ። እነሱም (ሶሃቦች) መለሱ፡ ‹‹መልዕክቱን እንዳደረሱ ፣ አደራን እንደመለሱ እና መልካም ምክርን እንደለገሱ እንመሰክራለን። ከዚያም አመልካች ጣታቸውን ቀስረው ወደ ሰማዩ እና ወደ ሰዎቹ አፈራርቀው እየጠቆሙ ሶስት ጊዜ ‹‹አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን! አሏህ ሆይ! ምስክሬ ሁን!›› አሉ። (ሙስሊም 1218)