የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ቁማር
ቁማር ማለት ምንድን ነው?
ቁማር ሁለት ተጫዎቾች ወይም ተወዳዳሪዎች ወይም ተወራራጆች አንዳቸው ካተረፈ (ካሸነፈ) ከከሰረው (ከተሸነፈው) ላይ ገንዘብ እንዲወስድ ቅድመ መስፈርት በሚቀመጥለት ውድድርና ጫወታ ላይ ይከሰታል፡፡በዚህ ላይ የሚሳተፉት ሁለቱም ወገኖች ገንዘቡን ከሌላው ወገን በሚያገኙበት ወይም ለሌላው በማስረከብ በሚከስርበት መሀል የሚሽከርከሩ ናቸው፡፡
ቁማር እርም ነው፡፡ በቁርኣንና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ውስጥ እርምነቱ በግልፅ ተነግሯል፡፡
አላህ (ሱ.ወ) በቁማር ምክንያት የሚከሰት ወንጀልና ጉዳት በርሱ ከሚገኝ ጥቅም እጅግ የገዘፈ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹አዕምሮን ከሚቃወም (አስካሪ) መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፤ በሁለቱም ውስጥ ጥቅሞች አሉባቸው ግን ሃጢአታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው በላቸው፡፡›› (አል በቀራ 219)
አላህ (ሱ.ወ) በግለሰቦችና በማህበረሰብ ላይ ከሚያስከትሉት መጥፎ ጉዳቶች አንጻር ቁማርን ስውር ወይም ረቂቅ እርኩስ በሚል ፍርድ ሰጥቶበታል፡፡ ከርሱ በመራቅም አዟል፡፡ የልዩነትና የጥላቻ መንስኤ፣ ከሠላትና አላህ ከማውሳት የመዘናጊያ ምክንያት መሆኑንም ተናግሯል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጦኦታትም አዝላምም(የመጠንቆያ እንጨቶች) ከሰይጣን ስራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡(እርኩስን) ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡ ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል አላህን ከማውሳትና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው ታዲያ እናንተ (ከነዚህ) ተከልካዮች ናችሁን (ተከልከሉ)›› (አል ማኢዳ 90-91)
ቁማር በማህበረሰብና በግለሰቦች ላይ የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፡
1- ማንኛውም አሸናፊው በማሸነፉ ከተሸናፊው ገንዘብ ሊወስድ ቅድመ መስፈርት የሚቀመጥበት ጫወታ፡፡ ለምሳሌ፡ የሆኑ ሰዎች ተሰባስበው ካርታ ሲጫወቱ በቅድሚያ ሁላቸውም የሆነ ያክል ገንዘብ ያስይዛሉ ወይም ያስቀምጣሉ፡፡ ከነሱ መካከል አሸናፊው የሁሉንም ገንዘብ ይወስዳል፡፡
የሆነ ክለብ፣ ወይም ቡድን፣ ወይም ተጫዋች ያሸንፋል አያሸንፍም በሚል መወራረድ፡፡ የሚወራረዱት ሁላቸውም ቅድሚያ ገንዘብ በማስያዝ ሲሆን እያንዳንዳቸው ያሸንፋል ብለው በሚገምቱትና በሚያምኑበት ቡድን ወይም ተጫዋች ስም ገንዘብ ያስይዛሉ፡፡ ከዚያም የተወራረደበት ቡድን ካሸነፈ የተወራራጆቹን ገንዘብ ይወስዳል፡፡ የተወራረደበት ቡድን ከተሸነፈ ገንዘቡን ይከስራል፡፡
ሎተሪና ዕጣ፡ ለምሳሌ ዕጣው ሲወጣ ትልቅ ገንዘብ አሸናፊ ልሆን እችላለሁ በሚል እሳቤ በእጣው ላይ ለመሳተፍ የሆነ ካርድ በሆነ ያክል ዶላር ይገዛል፡፡
4- በስልክ ጥሪዎች ወይም በሞባይል መልእክቶች ከወትሮው ወጪ በላይ በሚያወጡ ውድድሮች ላይ መሳተፍ፣ ተንቀሳቃሽ የሆኑ በኤክትሮኒክስ መሳሪያ የሚሰሩ ወይም በኢንተርኔት ድህረ ገጾች ላይ የሚለቀቁ የቁማር ጨዋታዎች፡፡ በነዚህ ጨዋታዎች ላይ ተጫዋቹ ሁለት ግምቶች ይኖሩታል፡፡ እሱም ገንዘብ ማግኘት ወይም መክሰር ነው፡፡