መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ኪራይ

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ኪራይ ሃሳብ እና እሱን በተመለከተ በእስልና ህግ ውስጥ ያሉትን ብያኔዎች (የህግ ውሳኔዎች) ትማራላችሁ።

ስለ ኪራይ ትርጉም ፣ ብያዎቹ እና በእሱ ድንጋጌ ላይ ያሉ ጥበቦችን ትማራላችሁ።ስለ ኪራይ ውል ባህሪ እና ስለ ቅድመ ሁኔታዎቹ ትማራላችሁ፡፡(ስለ ካሳ እና ሰራተኛ) የክፍያ እና የደመወዝ አይነቶችን ታውቃላችሁ፡፡የኪራይ ውል የሚያበቃበትን አግባብ ታውቃላችሁ፡፡

የኪራይ ትርጉም

አንድ የታወቀ ንብረት ወይም እቃ ለስራ ወይም የተፈቀደ ጥቅም ስለሚገኝበት ተብሎ በተወሰነ የጊዜ ገደብ እና ክፍያ መሰረት የሚፈፀም ውል ነው።

በእስልምና ህግ የኪራይ ብያኔ (ሁክም)

ኪራይ የተፈቀደ እና ህጋዊ ነው። ይህ በቁርአን ፣ በሱና እና በኡለማኦች ስምነት ማስረጃ ይደገፋል። ሁለቱ ወገኖች ከተስማሙ በኋላ የማይሻር ውል ነው። እሱን በሚያመለክት በማንኛውም ንግግር ላይ ተፈፃሚነት ይኖረዋል። ለምሳሌ ከፍያህ ፣ እዳህ እና መሰል የተለመዱ ንግግሮች ናቸው።

የኪራይ መፈቀድ ማስረጃ

አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከሁለቱ አንደኛዋ ‹አባቴ ሆይ! ቅጠረው። ከቀጠርከው ሰው ሁሉ በላጩ ፣ ብርቱው ፣ ታማኝ ነውና› አለችው።" (ሱረቱል ቀሶስ 26)

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ እና አቡበክር ከበኒ አዲል ጎሳ የሆነን (የቁረይሽ ጣኦት አምላኪ) ሰው እንደ ባለሞያ መሪ እርገው ቀጠሩት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና አቡበክር ሁለት የሚጋለቡ ግሞሎቻቸውን ሰጡት። በሶስተኛው ቀን ጠዋት ወደ ሰውር ዋሻ ግመሎቻቸውን ይዞ እነዲመጣ ቃሉን ተቀበሉት።›› (ቡኻሪ 2264)

የኪራይ ህጋዊነት ጥበብ

ኪራይ በሰዎች መተዳደሪያ ገቢ ውስጥ ብዙ ጥቅሞችን ያስገኛል። በእርግጥ የባለሞያዎችን ስራ ይፈልጋል፡፡ ከእነዚህም ለኪራይ ከሚየሠገለግሉት ውስጥ መኖሪያ ፣ መሸጫ ሱቆች ፣ እንስሳቶች ፣ ተሸከርካሪ መጓጓዣዎች ፣ ሰዎች የሚጠቀሙባቸው ማሽነሪዎች ይገኙበታል። ብዙ ሰዎች እነዚህ ነገሮች መግዛት ላይችሉ ይችላሉ። ሆኖም እነሱ ለመከራየት መፈቀዱ ህይወታቸውን ያቀልላቸዋል፤ ሁለቱንም በሚጠቅም ዝቅ ባለ ዋጋ ፍልጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ይረዳቸዋል። አሏህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይገባው!

የኪራይ አይነቶች

١
1 በግልፅ በእይታ የሚታወቅ ንብረት፡ ለምሳሌ መኖሪያ ቤት ፣ መጋዘን ፣ ሱቅ ወይም ሌላ ነገሮች ናቸው።
٢
2 የሚታወቅ ስራ መሆን፡ ለምሳሌ ልክ እንደ ቤት መስራት (ግንባታ) ፣ መሬት ማረስ እና መሰል ነገሮች ናቸው።

የቅጥር አይነቶች

١
1 የግል ቅጥር
٢
2 የጋራ ቅጥር

የግል ቅጥር

አንድ ሰው ለተወሰነ ጊዜ ያህል እንዲሰራለት ብሎ የሚቀጥረው ነው። ሆኖም በዚህ ጊዜ ከከጣሪው ውጭ ለማንም ሰው መስራት አይፈቀድለትም። ይህ ሳይሆን ቢቀር ከቀጣሪው ውጭ ለሰራበት ክፍያው ታስቦ ይቀናነስበታል። ስራውን ስላሳየ እና መስራት ስለጀመረ መከፈል ይገባዋል። ስራውን እስኪጨርስ ድረስ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ማብቃት ሳይጠበቅ ሙሉ ክፍያውን ማግኘት ይገባዋል። ለምሳሌ ልክ እንደ ህመም ወይም የአካል ጉዳት ያለ አሳማኝ ምክኒያት አስካልኖረው በቀር ክፍያውን የሚያገኘው ለሰራበት ቀን ብቻ ነው።

የጋራ ቅጥር

ይህ አይነቱ ቅጥር አንድ ሰው ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥበት ነው። በራሱ ሃሳብ እና ከሰዎች ትዕዛዝ ተቀብሎ የሚሰራ ለምሳሌ ብረት አንጥረኛ (ብረት ቀጥቃጭ) ፣ የቧንቧ ሰራተኛ ፣ ቀለም ቀቢ ፣ ልብስ ሰፊ ያለ ነው። ይህ አይነቱ ሰራተኛ ለሌሎች ሰዎች ከመስራት አይከለከልም። ዋናው ነገር ክፍያውን የሚያገኘው ስራውን ከጨረሰ ብቻ ነው።

የኪራይ ውል ህጎች

١
1 ውል ሰጭ እና ውል ተቀባይ
٢
2 የውል ቅፅ
٣
3 አገልግሎት ሰጪነት
٤
4 ክፍያ

ውል ሰጭ እና ውል ተቀባይ

ይህ ማለት የሚዋዋሉት ወገኖች አከራዩ እና ተከራዩ ሲሆኑ ውሉን የሚያቀርብው እና የሚቀበሉት ናቸው።

የውል ሰነድ ቅፅ

ይህ ቅፅ ውሉ የሚቀርብበት እና የሚቀበልበት እንዲሁም የህግ አግባብ ተከትሎ ውሉ እንደተፈፀመ የሚያሳይ ቅፅ ነው።

አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል መሆን

ይህ የከራይ ውል የሚያዝበት ሲሆን የሰው ልጅ የሚያቀርበው አገልግሎት ወይም እንስሳ ወይም እቃ ሊሆን ይችላል።

ክፍያ

የሰው ልጅ በሰጠው አገልግሎት ወይም ባቀረበው እቃ ምትክ የሚሰጥ ዋጋ ነው። ይህም በውል ሽያጭ ውስጥ ካለው ዋጋ ጋር እኩል ነው።

የኪራዩ ህጋዊነት ቅድመ ሁኔታዎች

١
1 ሁለቱ የውል አካል የሆኑ ወገኖች ንብረቱን ማስተዳደር የሚችሉ ፣ ቂል ሳይሆኑ ነገሮችን የሚያስቡ ስተውሉ ፣ የሚረዱ መሆን አለባቸው። ሆኖም ውሉ የተፈፀመው በልጅ ወይም አዕምሮው በተረበሸ (እብድ) ከሆነ የኪራዩ ውል ተቀባይነት የለውም። የተዋዋሉት ሰዎች በውለታቸው መሰረት ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆን ይገባቸዋል።
٢
2 ጥቅም የሚሰጥ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡ ለምሳሌ አንድ ቤት ውስጥ መኖር ወይም የሰው ልጅ ካበረከተው አገልግሎት ማግኘት ወ.ዘ.ተ ናቸው።
٣
3 ክፍያው መታወቅ አለበት
٤
4 የሚገኘው አገልግሎት ወይም ጥቅም የተከለከለ ሳይሆን የተፈቀደ ነገር መሆን አለበት። ሆኖም የሆነ ሰው እንዲዘፍን መቅጠር ፣ ቤትን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ማከራየት ወይም አስካሪ መጠጥ እንዲሸጥበት ማከራየት ተቀባይነት የለውም።
٥
5 የሚከራይ እቃውን በማየት ወይም የትዕዛዝ ማብራሪያውን በመከተል መታወቅ አለበት። ከዚህ በተጨማሪ ውሉ እቃው ጋር ብቻ ሳይሆን እቃው ከሚሰጠው ጥቅም ጋር የጠያያዘ መሆን አለበት።
٦
6 ኪራዩ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት የሚፈፀም መሆን አለበት።
٧
7 በሁለቱ ወገን መካከል ውሉን መስጠት እና መቀበል
٨
8 ኪራዩ የሚቆይበትን የጊዜ ገደብ መታወቅ አለበት። ለምሳሌ ወር ፣ ስድስት ወር ፣ አመት
٩
9 የተከራዩ እቃ አገልግሎት የተሟላ እንዳይሆን የሚያደርግ እንዳይሆን ከማንኛውም አይነት እንከን የፀዳ መሆን አለበት።

ክፍያ ግዴታ የሚሆንበት ወቅት

ኪራዩ የሚገባውን የሚያገኘው ውሉ እንዳበቃ ነው። ክፍያው መፈፀምም ያለበት የኪራዩ ጊዜ ካበቃ በኋላ ነው።

የተዋዋሉት ሁለቱ ሰዎች ኪራዩን ለማፋጠን ወይም ለማራዘም ከተስማሙ የክፍያውን ጊዜ ማራዘም ወይም ከፋፍሎ መክፈል ይፈቀዳል። በሌላ በኩል ደግሞ ተቀጥሮ የሚሰራው ሰው ስራውን በአግባቡ እንደጨረሰ ክፍያው በሰአቱ ይከፈለዋል።

ኪራዩ ከንብረት ጋር የተያያዘ ከሆነ ክፍያው የሚፈፀመው ግልጋሎቱን አግኝቶ ካበቃ በኋላ ነው። አቡ ኹረይራ () እንዳስተላለፈው ነብዩ () እንዲህ አሉ፡ ‹‹በትንሳኤው ቀን በሶስት ሰዎች ላይ ጠላት እሆናለሁ። 1 በእኔ ስም ቃል ገብቶ የከዳ 2 ነፃ የሆነን ሰው እንደ ባሪያ አድርጎ የሸጠ እና ተመኗን (ዋጋውን) የበላ 3 የጉልበት ሰራተኛ ቀጥሮ ሙሉ ስራውን አጠ ቆ ሲያገኘው ክፍያውን ያልከፈለው ሰዎች ናቸው አሉ።›› (ቡኻሪ 2227)

የኪራዩ ውል ማብቂያ

١
1 የተከራየው ንብረት መበላሸት፡ ለምሳሌ ቤት ፣ መኪና ወ.ዘ.ተ
٢
2 የኪራዩ ጊዜ ማብቃት
٣
3 ውል ማፍረስ ከተዋዋሉት ሰዎች አንደኛው ሌላውን ከውል ማውጣት ጠይቆት ሲሰጠው
٤
4 የተከራየው ንብረት ላይ እንከን ወይም ጉዳት ሲታይበት፡ ለምሳሌ አንድ ቤት ሲወድቅ ፣ ማሽነሪ ሲሰበር ወ.ዘ.ተ

ኪራዩ ከተዋዋሉ ሰዎች አንዱ በመሞቱ ወይም የተከራየው ንብረት በመሸጡ አይቋረጥም። በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው ለመስራት ተቀጥሮ የሚሰራ ቢሆን እና ስራው ሳይጨርሰው ቢሞት ኪራዩ ይቋረጣል። የክራዩ ግዜ ስያልቅ ተከራዩ ስራ ያቆማል፤የተከራየውን ንብረት ተንቀሳቃች ከሆነ ለባለቤቱ ያስረክባል።

የኪራይ እና የሽያጭ ልዩነት

١
1 በኪራይ ውስጥ የተዋዋሉበት እቃ ወይም ግልጋሎት ወዲያውኑ የሚጠናቀቅ አለመሆኑ ነው። በሽያጭ ግን የተዋዋሉበት እቃ ወይም ግልጋሎት ወዲያውኑ ይወሰዳል።
٢
2 ለኪራይ ተብሎ የተፈቀደ ሁሉ ለሽያጭ የተፈቀደ አይደለም። ለምሳሌ ነጻ የሆነን ሰው ለሙያው ልሰራ መከራየት (መቅጠር) የተፈቀደ ነው። ነገር ግን እሱን መሸጥ አይፈቀድም።
٣
3 ኪራይ ከሽያጭ ጋር የተወሰነ መመሳሰል ቢኖረውም የሚለየው እቃው እንደ ሽያጭ ሳይሆን ግልጋሎቱ ሽያጭ በመሆኑ ነው።
٤
4 ኪራዩ በጊዜ ገደብ ላይ የተመሰረተ እና ከመጭው ጊዜ ማራዘም ጋር የተያያዘ ነው። ሽያጭ ደግሞ የሚኖራቸው ውጤት ወዲያውኑ የምጠናቀቅ ነው።

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር