የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት ብድር
ሃያሉ አሏህ መተዳደሪያን በፍትሁ እና በጥበቡ በሰዎች መካከል ከፋፍሎታል። ከእነሱም መካከል ሐብታም እና ድሃ ፣ አቅመ ደካሞች እና ሚስኪኖች ናቸው። ሰዎች ፍላጎታቸውን ለሟሟላት እርስ በእርሳቸው መበዳደር የተለመደ ነው። ሆኖም የሃያሉ አሏህ ህግ የተሟላ እና ሁሉን አቀፍ በመሆኑ ከብድር ጋር የተያያዙ የተወሰኑ የህግ ድንጋጌዎች አሉት። ሃያሉ አሏህ ብድርን በቁርአን ውስጥ ረዘም ባለው የሱረቱል በቀራ አንቀፅ 282 ላይ ገልፆታል። ይህ አንቀፅ አያቱ ዲን ተብሎ ይጠራል።
የብድር ትርጉም
ለበተጋገዝ ስባል ለሌላ ሰው ተጠቅሞ የሚመልሰው ገንዘብ መስጠት ነው።
የብድር የህግ ብያኔ (ሁክም)
ብድሩ ለአበዳሪው የተወደደ እና ለተበዳሪው የተፈቀደ ነው። ብድር መጠየቅ እንደልመና የተጠላ አይደለም። ምክኒያም ተበዳሪው ገንዘቡን የሚወስደው ሊጠቀምበት እና ፍላጎቱን ሊያሟላበት ነውና። ከዚያም ተመሳሳዩን ገንዘብ ይመልሳል።
ነገርግን ብድሩ ለአበዳሪው ጥቅምን ወይም ትርፍ ገንዘብ ይዞለት የሚመጣ ከሆነ የተከለከለ አራጣ ነው። ገንዘቡን ያበደረው ትርፍ ጨመር አድርጎ እንዲመልስለት ከሆነ ማለት ነው። ልክ እንደዚሁ ሌላ ውል በብድር ላይ እንደ ሽያጭ እና መሰል ነገር ከተጨመረበት የተከለከለ ነው። ምክኒያቱም ብድርን እና ሽያጭን ማቀላቀል አይፈቀድምና ነው።
እስልምና ብድርን ፈቅዷል። ምክኒያቱም ለሰዎች መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ፣ ጉዳዮቻቸውን እና ጭንቀታቸውን ያቀላል ፣ ችግረኞችን ያፅናናል። እንዶሁም አበዳሪው ወደ አሏህ የሚቃረብበት አንድ መንገድ ነው። የተበዳሪው ፍላጎት ክፍ ባለ ቁጥር የአበዳሪው ሽልማትም ክፍ ያለ ነው።
ብድሩ ትልቅም ሆነ ትንሽ በመፃፍ ወይም የአይን እማኝ በማስመስከር መዝግቦ ማስቀመጥ የተወደደ ነው። ሆኖም ብድሩ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ መጠኑን ፣ የሚመለስበትን ሁኔታ እና ቀነ ገደብ መፃፍ አለበት። አበዳሪው በተበዳሪው ሞት ወይም እሱ ራሱ በመርሳት ወይም በክህደት ምክኒያት መብቱን ላለማጣት ዋስትና ይሆነዋል። አሏህ በእዳ አንቀፅ እንዲህ አለ፡ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በዕዳ በተዋዋላችሁ ጊዜ ፃፉት። ፀሐፊም በመካከላችሁ በትክክለ ይፃፍ። ፀሐፊም አሏህ እንደ አሳወቀው መፃፍን እንቢ አይበል። ይፃፍም። ያም በእሱ ላይ እዳ ያለበት ሰው በቃሉ ያፅፍ። ጌታውን አሏህ ይፍራ። ካለበትም እዳ ምንም አያጓድል።" (ሱረቱል በቀራ 282) በዚሁ አንቀፅ አሏህ እንዲህ ይላል፡ "እዳው ትንሽ ወይም ትልቅ ቢሆንም እስከ ጊዜው ድረስ የምትፅፉት ከመሆን አትሰልቹ። እንዲህ ማድረጋችሁ አሏህ ዘንድ በጣም ትክክል ፣ ለምስክርነትም አረጋጋጭ ፣ ላለመጠራጠራችሁም በጣም ቅርብ ነው።" (ሱረቱል በቀራ 282)
የብድር ትክክለኛነት ቅድመ ሁኔታዎች
ከሆነ ሰው ገንዘብ የተበደረ ሰው መልሶ መክፈል አለበት። ለመመለስ ሃሳብ ሳይኖረው የሰዎችን ገንዘብ መውሰድ የተከለከለ ነው። ሆኖም እዳውን የመክፈያ ጊዜ ሲደርስ ለባለቤቱ መመለስ አለበት። አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ እንዲህ አሉ፡ መልሼ እከፍለዋለሁ ብሎ አስቦ የሰዎችን ገንዘብ የወሰደ ሰው አሏህ በእሱ በኩል መልሶ ይከፍለዋል። ሊገፈው አስቦ የወሰደ ሰው አሏህ እሱን ይገፈዋል።›› (ቡኻሪ 2387)
የተበዳሪው ሁኔታ ብድሩን የሚከፍልበት ጊዜ ስደርስ
ገንዘብን ባንክ ውስጥ የማስቀመጥ ሁክም (ብያኔ)
ተበዳሪው ክፍያውን ቢያዘገይ መቀጫ ገንዘብ መጠየቅ አይፈቀድም። ይህ አራጣ ነው። ልክ እንደዚሁ ባስፈለገ ጊዜ ብድር መውሰድ አይፈቀድም፤ ተበዳሪው እዳውን በጊዜ (በሰአቱ) እከፍለዋለሁ፤ ቅጣቱንም አልከፍልም ብሎ እርግጠኛ እንኳ ቢሆን ማለት ነው። ምክኒያቱም የሚፈፅመው ውለታ የአራጣ ውል ስለሆነ ነው።
እዳን ሲከፍሉ በጎ መሆን
እዳን ሲከፍሉ በጎ መሆን ሲባል ገንዘቡን ሲመልሱ በራሱ ፈቃድ ማንም ሳይጠይቀው ጨመር አድርጎ መመለስ የተወደደ ነው። ምክኒያቱም እዳን የሚከፍሉበት አንድ ጥሩ መንገድ ነውና። በሌላ በኩል ደግሞ ተገዶ ወይም ተጠይቆ ከሆነ ግን የተከለከለ አራጣ ነው።