መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት ውሰት

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ውሰት ምንነት እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ የህግ ብያኔዎችን ትማራላችሁ።

1 የውሰት ትርጉም ታውቃላችሁ።2 ከውሰት ጋር የተያያዙ የህግ ብያኔዎችን ታውቃላችሁ።3 በውሰት እና በተቀማጭ መካከል ያለውን ልዩነት ታውቃላለችሁ።

የውሰት ፅንሰ ሃሳብ

ውሰት አንድ ሰው የሆነን ነገር ዋጋ ሳይከፍል የሚጠቀምበት ሲሆን የተፈቀደ ነው። ይህን ተብሎ የተጠራውም ዋጋው የማይከፍልበት በመሆኑ ነው።

የውሰት ሁክም (ብያኔ)

ውሰት በመልካምነት እና በደግነት የመረዳዳት አንድ አካል ነው። በቁርአን ፣ በሱና ፣ በሊቃውንት ምስለት እና ስምምነት የተፈቀደ ነው። የውሰት ውል ከተፈቀዱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ፅኑ ውል ግን አይደለም፤ ከሁለቱ ወገን አንዱ በማንኛውም ጊዜ ሊያቋርጠው ይችላል። ውሰት ወደ አሏህ የሚያቃርብ የተወደደ ተግባር ነው። ምክኒያቱም ሰዎች ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉበት ፣ በሰዎች መካከል መቀራረብን እና መዋደድን የሚያስገኝ ስለሆነ ነው። የንብረቱ ባለቤት በማይፈልገው ጊዜ የሚበደረው ደግሞ በሚፈልግበት ጊዜ ሲሆን ተገቢ ነው። ተበደረ ወይም ተዋሰ በማለት ብቻ ዱቤ ተፈፃሚነት ይኖረዋል።

ውሰት የተፈቀደበት ጥበብ

አንድ ሰው አንድ ንብርት ወይም እቃ ሊጠቀምበት ፈልጎ ነገርግን የእቃው ባለቤት እሱ ሳይሆን ሲቀር እና ለእሱ የሚከፍለው ገንዘብ ሳይኖረው ሲቀር እና ሌሎች በስጦታ ወይም በምፅዋት መልክ የማይሰጡት በመሆኑ ለጊዜው በዱቤ ተጠቅሞ የሚከፍልበት ነው። ሆኖም ሁለቱም ወገኖች ፍላጎታቸውን ያሟላሉ።

ከአሏህ እዝነት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ውሰትን መፍቀዱ ነው። ተዋሹ የእቃውን ደህንነት በመጠበቁ ፍላጎቱን የሚያሟላበት ፣ አዋሹም ወንድሙ እቃውን እንዲጠቀምበት በማድረጉ የሚመነዳበት ነው።

አሏህ እንዲህ አለ፡ "በበጎ ነገር እና አሏህን በመፍራት ተረዳዱ። በሃጢያት እና ወሰን በማለፍ አትረዳዱ።" (ሱረቱል ማኢዳ 2)

አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ በአንድ ወቅት የመዲና ሰዎች ተስፈራሩ። እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አል-መንዱብ ተብሎ የሚጠራ ፈረስ ከአቡ ጦልሃ ተውሰው ጋልበውት ሄዱ። ተመልሰው በመጡ ጊዜ እንዲህ አለ፡ ‹‹ምንም የሚያስፈራ ነገር አላየንም። ነገርግን ፈረሱ በጣም ፈጣን ነበር።›› (ቡኻሪ 2627 ፣ ሙስሊም 2307)

ለውሰት ህጋዊነት ቅድመ ሁኔታ

١
1 የተጠየቀው ንብረት ከተጠቀሙበት በኋላ በነበረበት ሁኔታ መመለስ አለበት።
٢
2 የሚጠቀምበት መንገድ የተፈቀደ መሆን አለበት። ግን አስካሪ መጠጥ ለማመላለስ መኪናን ወይም ሌላ የመጓጓዣዎችን ማዋስ አይፈቀድም።
٣
3 የተጠየቀውን እቃ አዋሹ መስጠት ይገባዋል። ይህን ለማድረግ የዕቃው ባለቤት እሱ ራሱ መሆን አለበት ወይም ለሰው እንዲሰጥ ፈቃድ የተሰጠው መሆን አለበት።
٤
4 አዋሹ ንብረት የማንቀሳቀስ መብት ያለው መሆን አለበት።

የውሰት ምሰሶዎች

١
1 አዋሹ፡ የንብረቱ ባለቤት የሆነ
٢
2 ተዋሹ፡ ንብረቱን የሚዋሰው እና የሚጠቀምበት ሰው ።
٣
3 የሚዋሰው እቃ፡ ውሰት ለጠየቀው ሰው የሚሰጠው እቃ ወይም ንበረት እንስሳ ፣ ማሽን ወይም ሌላ ነገር ሊሆን ይችላል።
٤
4 የውሰት ፎርም (ቅፅ)፡ ይህም ውሰቱ የሚገለፅበት ማረጋገጫ ነው።

የተዋሰው ሰው ንብረቱን በደንብ ተንከባክቦ መያዝ እና መጠበቅ ፣ በአግባቡ መጠቀም እና ለባለቤቱ በሰአቱ በጥሩ ሁኔታ መመለስ አለበት። እቃው ከተዋሰው ሰው ጋር ሆኖ እያለ ችላ በማለቱ ምክኒያት ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ በቻለው መንገድ የጠፋውን ወይም የተበላሸውን እቃ ማካካስ አለበት። በሌላ በኩል እቃው የጠፋው ወይም የተበላሸው ባለቤቱ በፈቀደለት አግባብ እየተጠቀመበት እያለ ከሆነ ተዋሹ ማካካስ አይጠበቅበትም፤ ድንበር ያለፈበት ወይም ቸል ያለበት ነገር ኖሮ ካልሆነ በቀር።

ውሰትን የመመለስ ብያኔ (ሁክም)

የተዋሰው ሰው የተዋሰውን ነገር ተጠቅሞ ፍላጎቱን ካሟላ በኋላ እቃውን የሚመልሰው በጥሩ ሁኔታ መሆን አለበት። ያ ማለት በወሰደበት አግባብ እና ሁኔታ ነው።እስኪጠይቀው ድረስ እራሱ ጋር አድርጎ ማስቀመጥ እና ውሰቱን መካድ የለበትም። ይህ ካልሆነ ከሃዲና ሃጢያተኛ ይሆናል።

እቃውን ያዋሰ ሰው በማንኛውም ጊዜ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል። ተዋሹ ሰው የሚጎዳበት ነገር እስካልኖረ ድረስ ማለት ነው። ተዋሹ ሰው (ተበዳሪው) ሰው በተባለው ጊዜ ወይም ከዛ ቀደም ብሎ በመመለስ ጉዳት የሚደርስበት ከሆነ ጉዳቱ እስኪጠፋ ድረስ ውሰቱ ይራዘማል። ለምሳሌ የሆነ ሰው መሬት ቢዋስ እና አዝዕርት ቢዘራበት አዋሹ ሰው መሬቱ የሚመለስለት ሰብሉ ከተሰበሰበ በኋላ ነው።

ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ አሏህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል። በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል። አሏህ በእሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር! አሏህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው።" (ሱረቱ ኒሳዕ 58)

የውሰት እና የአደራ ተቀማጭ ልዩነት

١
1 ውሰትን የሚክድ ሰው ልክ እንደ ሌባ እጁ መቆረጥ አለበት። ተቀማጭ ግን ይህ አይደለም።
٢
ተበዳሪው የተበደረውን ገንዘብ የወሰደው የእራሱን ፍላጎት ሊያሟላበት ነው። ስለ ሆናም ዋስትና ያለው እሱ ላይ ነው። ተቀማጭ ገንዘብን በተመለከተ ተቀብሎ የሚያስቀምጠው ሰው ወደ አሏህ ለመቃረብ ነው። እሱ ታማኝ ይሁን ዋስትና ግ ን የለበትም። አደራ በተሰጠው ንብረት ላይ ድንበር እስካላለፈ እና ቸልተኛ እስካልሆነ በቀር።

ውሰት የሚያበቀው እንዴት ነው?

١
1 ጊዚያዊ ውሰት ሲሆን የተዋዋሉበት ጊዜ ሲያበቃ
٢
2 ያዋሰው ሰው ውሳኔው ላይ እንደገና አስቦ እንዲመለስለት ሲፈልግ
٣
3 ከሁለቱ ወገኖች አንዱ ቢያብድ
٤
4 ከሁለቱ ወገኖች አንዱ ቂልነት ሲያጠቃው ወይም ሲከስር እና እገዳ ስጣልበት
٥
5 ከተዋዋሉት ሰዎች አንዱ ቢሞት
٦
6 የተዋሰው ንብረት ወይም እቃ ሲጠፋ ወይም ሲበላሽ
٧
7 የሆነ ሰው የውሰቱን እቃ የባለቤትነት መብት ባገኘ ጊዜ

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር