የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል
ትምህርት የሐጅ ትርጉም እና ትሩፋቱ
የሐጅ ትርጉም
ሐጅ ማለት የተወሰኑ አምልኮት ተግባራትን ለመፈፀም ወደተከበረው አላህን ማምለኪያ ቤት- በይቱላሂል ሐራም(ካዕባ) በማሰብ መጓዝ ነው፡፡ ከዚያም፣ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፉ ተግባሮችና ንግግሮችን ማከናወን ነው፡፡ ኢሕራም መታጠቅ፤ በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ መዞር፤ በሠፋና በመርዋ ኮረብታዎች መሐል ሰባት ጊዜ መመላለስ፤ በዐረፋ መቆም፤ በሚና ጠጠሮችን መወርወርና ሌሎችንም ተግባራት መፈፀምን ያጠቃልላል፡፡ ሐጅ በውስጡ ለአላህ ባሮች ከበባድ ጥቅሞችን ይዟል፡፡ ከነኚህም ጥቀሞች መካከል፤ የአላህን አሃዳዊነት በይፋ ማሳየት፣ ሐጃጆች የሚጎናጸፉት ላቅ ያለ ምህረት፣ የሙስሊሞች መተዋወቅ፣ የሃይማኖት ድንጋጌዎችን በተግባር መማርና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
የሀጅ ድንጋጌ
ሐጅ የእስልምና አምስተኛው ምሰሶ ሲሆን እያንዳንዱ ሙስሊም ወንድ እና ሴት ከቻሉ በህይወት ዘመናቸው አንድ ጊዜ ግዴታ አለባቸው። ታላቁ አላህ እንዲህ ብሏል፡- “በሰዎች ላይ የአላህ ቤት ሐጅ የማድረ ግዴታ አለበት። ለቤቱም መንገድን የቻለው ሰው። የካደም ሰው አላህ ከኣለማት የተብቃቃ ነው። ኣለ ኢምራን፡ 97]
ከአቡ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “እናንተ ሰዎች ሆይ አላህ በናንተ ላይ ሐጅ ግዴታ አድርጓልና ሐጅ አድርጉ። .” ከዚያም አንድ ሰው፡-የአላህ መልእክተኛ ሆይ በየ አመቱ ነውን?" አለ፣ ነቢዩ ዝም አሉ ሶስት ጊዜ እስኪናገር ድረስ፣ ከዚያ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “አዎ ባልኩ ኖሮ ግዴታ ይሆን ነበር አናንተም አትችሉም ነበር። ” (ሙስሊም 1337)።
አንድ ሙስሊም ከቻለ ሐጅ ለማድረግ መቸኮል አለበት።
የሀጅ ግዜ
ሐጅ የተወሰነ ጊዜና ቦታ አለው።
የጊዜ መርሃግብሮች
ሐጅ የተወሰኑ ወራቶች ያሉት ሲሆን በእነዚህ ወራት ውስጥ ካልሆነ በስተቀር ለሐጅ ኢሕራም መድረግ አይፈቀድም። እነርሱም፡- ሸዋል፣ ዙልቃዳህ እና ዙልሂጃህ ናቸው።የሐጅ ተግባራት በዙልሂጃ ወር በስምንተኛው እና በአስራ ሦስተኛው ቀን መካከል የምከናወኑ ናቸው፣ይህም በእስልምና አቆጣጠር ከጨረቃ ወራቶች አስራ ሁለተኛው ነው።
እነዚህ ቦታዎች ከውጪ ለሚመጣ ሀጃጅም ሆነ ኡምራ አድራጊ ኢህራም ሳያደርግ ከእነሱ አልፈው ወደ መካ መሄድ የማይፈቀድላቸው ቦታዎች ናቸው ። የመዲና ሰዎች ሚቃት ዙ አል-ሁለይፋ ነው። የሻም ሰዎች ሚቃትት አል-ጁህፋ ነው። የነጅድ ሰዎች ሚቃት ቀርን አል-መናዝል ነው። የየመን ሰዎች ሚቃት የለምለም ነው። የኢራቅ ሰዎች ሚቃት ዛት ኢርቅ ነው።እነዚህ ሚቃቶች ለነሱ እና ከነሱ ውጪ በዚያ አቅጣጫና መንገድ ወደነሱ የሚመጡት ሀጅ ወይም ዑምራ ለማድረግ ለሚፈልጉ ነው። እነዚህ ቦታዎች ልምድ ባላቸው ሰዎች እና በዘመናዊ ካርታዎች ይታወቃሉ።
የሀጅ ግዴታነት መስፈርቶች
የመጀመሪያው ቅድመሁኔታ፡ እስልምና
ሐጅ በሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ሐጅ በካፊር ላይ ግዴታ አይደለም ካደረጋም አይጸናም፤ ምክንያቱም እስልምና ለአምልኮ ተቀባይነት ቅድመ ሁኔታ ነው።
ሁለተኛው ቅድመ ሁኔታ: አእምሮ ጤንነት
በዐሊ (ረዐ) በዘገቡት ሐዲሥ ላይ እንደተገለጸው ጤነኛ መሆን ግዴታና ትክክለኛ መሆን ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ሐጅ ለዕብድ ሰው አይገደድም አይፀናምም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ብዕሩ ከሦስት ሰዎች ላይ ተነሥቷል፡- ከእንቅልፍተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፣ ከህጻን እስከ ጉርምስና ድረስ፣ ከእብድ ሰውም እስክድን ድረስ። ” (አቡ ዳዉድ 4403)።
ሦስተኛው ቅድመ ሁኔታ: ጉርምስና
ሐጅ በህጻናት ላይ አይገደድም።በዓልይ (ረዐ) በዘገቡት ሀዲስ ላይ በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- “ብዕሩም ተነሥቷል ከሦስት ሰዎች፡- ከአንቀላፋው እስኪነቃ ድረስ፣ ከህጻን እስከ ጉርምስና ድረስ፣ ከእብድ ሰውም ወደ አእምሮው እስኪመለስ ድረስ።” (አቡ ዳዉድ 4403)።
ህጻን ልጅ ሀጅ ቢሰራ ሀጅው ትክክለኛ ነው ከእስልምና ሀጅ ግን አይበቃም። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “ህጻን ልጅ ሐጅ ቢያደርግ እስክጎረምስ ተቀባይነት አለው። ከጎረመሳ በኋላ ሌላ ሀጅ አለበት"። (ሙስተድራክ) አል-ሀኪም 1769)
አራተኛው ቅድመ ሁኔታ: ከባሪነት ነፃ መሆን
በባለቤትነት የተያዘ ባሪያ ሀጅ ማድረግ አይጠበቅበትም፣ እሱ ጌታውን በማገልገል ስለተጠመደ ይቅርታ ይደረግለታል። ባሪያው በጌታው ፍቃድ ሐጅ ከሰራ ሀጁ ትክክል ነው። ከእስልምና ሀጅ ግን አይበቃም። ከኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) በተዘገበው ጊዜ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- “ሐጅ ያደረገና ከዚያም ነፃ የወጣ ባሪያ ሌላ ሀጅ ይጠበቅበታል።” አል-ሱነን አል-ኩብራ በአል-በይሃቂ (8613)።
አምስተኛው ቅድመ ሁኔታ: ችሎታ
የአካል ብቃት ያለው፣ ለመጓዝ የሚችል፣ ስንቅ ያለው እና ሐጅ ለማድረግ የሚሄድበት ትራንስፖርት ባለው ሰው ላይ ሐጅ ግዴታ ነው። አንዲት ሴት ሐጅ የማድረግ ችሎታዋ መስፈርት በሐጅ ጉዞ ወቅት አብሮት የሚሄድ መህራም መገኘት ነው። ምክንያቱም ያለ መህራም ለሐጅም ሆነ ለሌላ ዓላማ መጓዝ አይፈቀድላትም።
ኃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡- “በሰዎችም ላይ ለአላህ ወደ ቤቱ ሐጅ ማድረግ ለእርሱ መንገድን የቻለው ሰው ግዴታ ነው።” (አለ ኢምራን 97)።
በገንዘቡ የቻለ ነገር ግን በማይድን በሽታ ወይም በእርጅና ምክንያት የአካል ጉድለት ያለበት ሰው በእሱ ምትክ ሐጅ የሚያደርግ ሰው መሾም አለበት። በአልፈድል ብን አባስ እንደተላለፈው አንድ ሰው ነብዩን (ሶ.ዐ.ወ) ጠየቀ እና፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ አባቴ እስልምናን የተቀበለው በሸመገለ ጊዜ በግመሉ ላይ ማርጋት አይችልም። እሱን ወክዬ ሐጅ ማድረግ አለብኝ? እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- ምን ይመስላችኋል እዳ ብኖርበትና ክሱ ብትከፍል አይበቃም? እሱም አዎ አለ፤ አሷቸውም፡- “እንግዲያውስ ከአባትህ ሐጅ አድርግ” (ሙስነድ አህመድ 1812)።
አንድ ሙስሊም ሐጅ ማድረግ የመቻል መገለጫዎች፡
አንዲት ሴት ሐጅ ለማድረግ መሕረም (የቅርብ ዘመዷ) አብሯት መኖሩ መስፈርት ነው፡፡
በሴት ላይ ሐጅ ግዴታ ሊሆን የሚችለው መሕረሟ (የቅርብ ተጠሪዋ) ካለ ብቻ ነው፡፡ መሕረሟ አብሯት ከሌለ በሴት ልጅ ላይ ሐጅ ግዴታ አይሆንም፡፡ ለአንዲት ሴት መሕረም የሚሆኗት ባለቤቷ ወይም እርሷን ፈፅሞ ማግባት የማይፈቀድላቸው፣ እንደ አባት፣አያት፣ልጅ፣የልጅ ልጅ፣ ወንድሞችና የወንድም ልጆች፣ አጎቶች፣ የእናት ውንድሞች ናቸው፡፡
በራሱዋ የምትተማመን ሁና ያለሙህረም ሐጅ ካደረገች ሐጁዋ ትክክል ነው፤ ምንዳም ያስገኛታል፤ ነገር ግን ጥፋተኛ ትሆናለች፡፡
የሐጅ ትሩፋቶች
ሐጅ የሚያስገኘውን ትሩፋቶችና መልካም ነገሮች በማስመልከት ብዙ ተነግሯል፡፡ ከዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
1 ሀጂ ከሥራዎች ሁሉ በላጭ ሥራ ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሥራዎች በላጩ ሥራ የትኛው ነው? ተብለው በተጠየቁ ጊዜ፡ ‹‹በአላህና በመልክተኛው ማመን ነው›› አሉ፡፡ ከዚያስ? ተባሉ ‹‹በአላህ መንገድ ላይ መታገል›› አሉ፡፡ በድጋሚ ከዚያስ? ተባሉ ‹‹ተቀባይነት ያገኘ ሐጅ›› ብለው መለሱ (አል ቡኻሪ 1447 / ሙስሊም 83)
2 ሐጅ ሰፊ ምህረት የሚገኝበት አጋጣሚ ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሐጅ ያደረገ፣ በሐጁም ውስጥ ከማላገጥና ከማፈንገጥ የራቀ ሰው፣ ልክ እናቱ እንደወለደችው ዕለት ከወንጀል የጸዳ ሆኖ ይመለሳል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1449 / ሙስሊም 1350)
3 ከእሳት ነፃ ለመውጣት ታላቅ አጋጣሚ ነው፡፡
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከዐረፋ ዕለት የበለጠ አላህ (ሱ.ወ) ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ዕለት የለም፡፡›› (ሙስሊም 1348)
4 የሐጅ ምንዳ ጀነት ነው፡፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ተቀባይነትን ያገኘ ሐጅ ከጀነት ሌላ ለርሱ ምንዳ የለውም፡፡›› (አል ቡኻሪ 1683 / ሙስሊም 1349) እነኚህና ሌሎች ትሩፋቶች የሚሰጡት ሃሳቡ(ኒያው) ላማረ፣ ከልቡ ለሚሰራ፣ ውስጡ ጽዱዕ ለሆነና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ፈለግ ላልሳተ ሰው ብቻ ነው፡፡