መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና

የእስልምና ሃይማኖት በሁለት ምንጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነሱም ቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ናቸው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እውነትነት እና በኢስላም ውስጥ ያለውን ቦታ ትማራላችሁ።

 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጥቅሞች ማወቅ ሱና በህግ ድንጋጌዎች ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ ማወቅ የሱና በህግ ድንጋጌዎች ውስጥ ያለውን ልቅና መረዳት

የነብዩ ሱና

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና አሏህ ለነብዩ ሙሐመድ ያደረገላቸው ወህይ (ራዕይ) መገለጥ ነው። ከአሏህ መጽሐፍ ጋር የእስልምና ሃይማኖት ምንጭ እና መሰረት ነው። ሁለቱ የማይነጣጠሉ የሁለቱ የእምነት ምስክርነት አካል ናቸውና። በሱና ያላመነ ሰው በቁርአን አያምንም።

የሱና ፍች

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና የእሳቸውን ንግግሮች ስራዎች ፣ ውሳኔዎች ፣ ግብረገባቸውን እና ስብዕናቸውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።

የነቢዩ ሱና ደረጃ

የነብዩ ሱና በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን የሚከተሉት ደረጃውን እና ጠቀሜታዎቹን ያሳያል።

1 ሁለተኛው የህግ ድንጋጌ ምንጭ ነው

ሱና ከቅዱስ ቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የእስልምና ሃይማኖት ምንጭ ነው። በአል-ሚቅዳድ ኢብን ማዲ ከሪብ አል-ኪንዲ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አለ፡ ‹‹መጽሐፉ እና ከእሱ ጋር አቻው ተሰጥቶኛል። አንድ ሰው መከዳ (አልጋ መሰል) ጋደም ብሎ እንዲህ ልል ይቃረባል። ‹‹ቁርአንን ያዝ። እናም እዚያ የተፈቀደ የምታገኘውን ማንኛውንም ነገር የተፈቀደ አድርገው። እዚያ የተከለከለውን ማንኛውንም ነገር የተከለከለ አድርገው›› ይላል።››(ይህ ሱናን ያገለላ ትልቅ ጥመት ነው) (ሙሰነድ አህመድ 17174)

2 ከሃያሉ አሏህ የሆነ መገለጥ ነው

የነብዩ ሱና ከአሏህ ለመልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ያደረገው የራዕይ መገለጥ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከስሜቱ (ከፍላጎቱ) አይናገርም። እሱ (ንግግሩ) የሚወርድ ራዕይ እንጅ ሌላ አይደለም። ሃይለ ብርቱ (መልአክ) አስተማረው።" (ሱረቱ ነጅም 3-4)

3 የቁርአን ማብራሪያ ነው

የነብዩ ሱና የቁርአን ማብራሪያ በውስጡ ይዟል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "ከግልፅ ማስረጃዎች ጋር በመጽሐፍት ሎክናቸው። ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልፅላቸውና ያስተነትኑ ዘንድ ቁርአንን አወረድን።" (ሱረቱ ነህል 44)

የቅዱስ ቁርአን አንቀፆች በብዙ ጉዳዮች ላይ ጠቅለል ያለ ውሳኔ ይዘው የመጡ ሲሆን የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግራቸው ወይም በቁርአን ውስጥ የተናገሩትን በተግባር ሰርተው አብራርተው አስቀምጠዋል። ለዚህ ምሳሌ ይህ የአሏህ ንግግር ነው፡ "ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ። ምፅዋትንም ስጡ። መልዕክተኛውንም ታዘዙ። ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና።" (ሱረቱ ኑር 56) ሶላትን ስገዱ እና ዘካም (ምፅዋት) ክፈሉ የሚለው ጥቅልል ብሎ የመጣ ሲሆን የዚህ ዝርዝር በሱና ውስጥ ተብራርቷል። በሱና ውስጥ የአምስቱ ሶላቶች (ስግደቶች) ወቅት ፣ የስግደቱ አፈፃፀም ሁኔታ እና ስንቆቻቸው እንደ ፆም ፣ የዘካ ስንቆች በግልፅ ተብራርተዋል።

አሏህ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጠብቆታል

የነብዩ ሱና አሏህ እንደሚጠብቀው ቃል ከገባው የአደራ ተውስታ ውስጥ አንዱ አካል ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡ "በእርግጥ ዚክሩን (አስታዋሹን) ያወረድነው እኛ ነን። በእርግጥም እኛ እንጠብቀዋለን።" (ሱረቱል ሒጅር 9) ዚክር የሚለው ቃል አሏህ ለነብዩ ከቁርአን እና ከሐዲስ የገለጠላቸውን ነገር ሁሉ የሚያጠቃልል ስም ነው።

የዚህ ጥበቃ አንዱ መገለጫ የነብዩ ሱና ሐዲስ ለመሰብሰብ ፣ ለመፃፍ ፣ ዘገባውን ትክክለኛነት የሚቆጣጠሩ ህግጋትን ያስቀመጡ ሊቃውንትን ማዘጋጀቱ ነው።እነዚህ ሊቃውንት የተጨመሩ ውሸት እና ስህተቶችን የመለየት የመቆጣጠር ስራ ሰርተዋል። የዘጋቢዎችን እና የዐስተላላፊዎችን ታማኝነት አጥንተዋልም። ይህንንም በጥሩ መንገድ ጠብቀው አቆይተዋል።

የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ለመጠበቅ በተጠቀመባቸው በእነዚያ ዘጋቢዎች እና ሊቃውንቶች አማካኝነት እንደሚጠበቅ ከአሏህ ዘንድ ዋስትና ተሰጥቶታል።

የነቢዩ ሱና ማስረጃነት

የነብዩ ሱና ከታላቁ ቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የህግ ምንጭ ሲሆን የሃያሉ አሏህ ሃይማኖት የጠሟላ አይሆንም መጽሐፉን (ቁርአን) እና ሱናን ጎንለጎን አድርጎ በመያዝ ቢሆን እንጅ።

ሱና ህጋዊ ውሳኔዎችን ለማግኘት አስፈላጊ እና ወሳኝ ምንጭ ነው። በእምነት እና በህግ ውሳኔዎች ላይ መተግበር አለበት።

ሱና የቅዱስ ቁርአን ድንጋጌዎችን ሊያብራራ ይችላል። እንዲሁም እራሱን ችሎ ፍርዶቹን ለማፅደቅ ይመጣል። ልክ እንደ ቁርአን የተፈቀደውን የሚፈቅድ ፣ የተከለከለውን የሚከለክል ነው።

የቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሐዲሶች ማስረጃ በእስልምና ህግጋት ውስጥ ያለውን ደረጃ እና ቦታ የሚያረጋግጡ ናቸው። ብዙ አያት (አንቀፆች) እና ሐዲሶች ሱናን አጥብቆ መያዝን የሚያዙ እና ሙስጦፋን መታዘዝ ግዴታ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ። አሏህ እንዲህ አለ፡ "መልዕክተኛው የሠጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙ። የከለከላችሁንም ነገር ሁሉ ተከልከሉ።" (ሱረቱል ሐሽር 7)

አል-ሙቀደም ኢብን መስኡድ የክሪብ አል-ኪንዲ እንዳስተላለፈው የዐሏ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ፡ ‹‹አንድ ሰው መከዳ (አልጋ መሰል) ላይ ጋደም ይልና እንዲህ ይላል፡ ‹‹በእኛ እና በእናንተ መካከል ያለው የአሏህ መጽሐፍ ነው። በእሱ ውስጥ ያገኘነው ፈቅደነዋል። በውስጡ ተከልክሎ ያገኘነውን ደግሞ ከልክለናል። ልክ እንደ አሏህ ክልከላ ሁሉ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ክልከላዎችን አድርገዋል።›› (ኢብን ማጃ 12)

ሱናን መከተል

አሏህ ባሮቹ መልዕክተኛውን እና ሱናቸውን ፣ ንግግራቸውን ፣ ስራቸውን የህይወት ሁኔታ እንዲከተሉ ደንግጓል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህ የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ በላቸው። አሏህም ይወዳችኋል። ወንጀላችሁን ይምርላችኋል። በእርግጥ አሏህ አዛኝ መሃሪ ነው።" (ሱረቱል ኢምራን 31) አሏህ እንዲህ አለ፡ "ትመሩ ዘንድ ቅንን መንገድ ተከተሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 158)

ኢርባድ ቢን ሰሪያህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሱናየን እና በትክክል የተመሩትን ኸሊፋዎችን ተከተሉ። ይህንንም በመንጋጋ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ (አጥብቃችሁ) ያዙት። ቢድአ (ፈጠራን በሃይማኖት) ተጠንቀቁ፤ ሁሉም ፈጠራ ቢድአ ነው፤ ሁሉም ቢድአ ደግሞ ጥመት ነው።›› (አቡዳውድ 4607)

መከተል ማለት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩትን ፣ የሰሩትን እና የኖሩበትን መንገድ መከተል ነው። ትዕዛዛቸውን መታዘዝ ፣ የከለከሉትን መከልከል ፣ የአምልኮ ተግባራትን በእሳቸው መንገድ መስራት እና መረተግበር ነው።

መከተል (መታዘዝ) ከግዴታዎች ውስጥ አንዱ ግዴታ እና ከሚወደዱት ውስጥም አንዱ የሚወደድ ተግባር ነው።

ሱናን የመከተል ትሩፋት

ሱናን መከተል ብዙ ጥቅሞች እና ፍሬዎች አሉት። እነሱም

ሱናን አጥብቆ መያዝና መመራት በእሳት ከተፈረጁ ጠማማ ቡድኖች መታደግ ነው። አብዱሏህ ቢን አምር እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ፡ ‹‹የእስራኢል ልጆች የደረሰባቸው ነገር በእኔ ኡመት ላይ ይደርስባቸዋል። ኮቴ በኮቴ (እግር በእግር) ይከታተላሉ። አንድ ሰው በግልፅ ከእናቱ ጋር ቢገናኝ ከእኔ ኡመት (ህዝቦች) ያን የሚያደርግ ይኖራል። በእርግጥ የእስራኢል ልጆች በ72 ቡድን ተከፋፈሉ። የእኔ ኡመት በ73 ቡድን ተቧድነው ይከፋፈላሉ። ሁሉም የእሳት ናቸው አንዷ ቡድን ስትቀር አሉ። ‹‹የዐሏህ መልዕክተኛ ሆይ! የትኛዋ ናት? አሉ (ሶሃቦች)። እሳቸውም፡ ‹‹እኔ እና ሶሃቦቼ ያለንባት ናት አሉ።›› (ትርሚዚ 2641)

ሱናን አጥብቆ መያዝ መመራትን የሚያስገኝ እና ከጥመት የሚታደግ ነው። አሏህ አንዲህ አለ፡ ‹‹ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።›› (ሱረቱል አዕራፍ 158) አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የዐሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ሁለት ነገሮችን ትቼላችኋለሁ፤ እነሱን ከያዛችሁ አትጠሙም። እነሱም የአሏህ መጽሐፍ እና የእኔ ሱና ናቸው።›› (የአል-ሐኪም ሙስተድረክ 319)

የአንድ ስራ ተቀባይነት የሚወሰነው ከሱና ጋር የሚስማማ ከሆነ ነው። አንድ የአሏህ ባሪያ የሚሰራው ስራ በነብዩ ሱና መሰረት መሆን አለበት። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእኛ ትዕዛዝ ውጭ የሆነን ስራ የሰራ ሰው እሱ (ስራው) ተመላሽ ነው (ተቀባይነት የለውም)።›› (ሙስሊም 1718)

ሱናን መከተል ማለት ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጠጋት ነው። ከሱና የሸሸ ሰው፤ ከነብዩ ሸሽቷል። አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ሶስት ወንዶች ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአምልኮ ሁኔታ ሊጠይቁ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ቤት መጡ። ስለዛ በተነገራቸው ጊዜ የእራሳቸው አምልኮ አንሶ ታያቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለፈው እና መጭው ወንጀላቸው ሁሉ ተምሮላቸው ሳለ (ይህን ካደረጉ) ታዲያ እኛ ከነብዩ አንፃር የትነው ያለነው? አሉ። ከእነሱም አንደኛው ‹‹የሌሊት ሶላት ዘላለም እሰግዳለሁ›› አለ። ሌላኛው ደግሞ ‹‹አመቱን ሙሉ እፆማለሁ፤ ፆሜንም አልፈታም›› አለ። ሶስተኛው ደግሞ ‹‹ከሴቶች እርቃለሁ ለዘላለምም አላገባም›› አለ። የአሏህ መልዕክተኛ ወደ እነሱ መጡና ‹‹እንትን እንትን ያሉት ሰዎች እናንተው እራሳችሁ ናችሁን? አሉ። በአሏህ ይሁንብኝ! ከእናንተ በላይ አሏህን እፈራለሁ ነገርግን እፆማለሁ፤ ፆምን እፈታለሁ ፣ እሰግዳለሁ፤ እተኛለሁ ፣ ሴቶችንም አገባለሁ አሉ። ከሱናየ የራቀ ሰው ከእኔ አይደለም አሉ።›› (ቡኻሪ 5063)

ሱናን መከተል ከፈተና እና ከሳማሚ ቅጣት ያድናል። አሏህ እንዲህ አለ፡ ‹‹እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ አይደርስባቸውም፤ አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።›› (ሱረቱ ኑር 63)

ሱናን መከተል እና መፈፀም በሁሉም ዳር (ቤት-ሐገር) ስኬት እና ደስታን ያስገኛል። አሏህ እንዲህ አለ፡ "አሏህ እና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው ፣ አሏህንም የሚፈራ እና የሚጠነቀቅ ሰው፤ እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው።" (ሱረቱ ኑር 52)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር