መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት እርዳታ

በዚህ ትምህረት ውስጥ ስለ እርዳታ ፅንሰ ሃሳብ እና ከሱ ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ።

 1 ስለ እርዳታ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጀርባ ያሉ ጥበቦችን ትማራላችሁ።2 ከእርዳታ ጋር ተያያዥ የሆኑ የህግ ውሳኔዎችን ታውቃላችሁ።3 የአሏህን ውዴታ ፈልጎ እርዳታ መስጠት የተወደደ እና የሚበረታታ ተግባር ነው።

ሃያሉ አሏህ ለጋስ ነው፤ ለጋስነትን እና ቸርነትን ይወዳል። በሌላ በኩል ደግሞ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ለጋስ ቸር ነበሩ። ስጦታን ይቀበላሉ፤ እሳቸውም ይሰጡ ነበር። ስጦታን እንድንቀበል እና እነድንሰጥ አስተምረዋል። ከዚህ በተጨማሪ መስጠት በጣም አብልጠው የሚወዱት ነገር ነበር።

የእርዳታ ትርጉም

ያለ ክፍያ የአንድ እቃ ወይም ንብረት የባለቤትንት መብት ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ማለት ነው።

‹‹የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ›› ስንል የባለቤትነት መብቱ የእርዳታው ውል አካል ነው ማለታች ነው።

‹‹እቃ ወይም ንብረት›› ስንል ደግሞ ገበያ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም አይነት እቃ ፣ ሸቀጥ ወይም ደግሞ ገንዘብ ነው።

‹‹የእቃው ወይም የንብረቱ የባለቤትነት መብት›› የሚለው አገላለፅ ሁለት ‹‹የጥቅም ስጦታዎችን›› በሁለት ምክኒያቶች አያካትም።

١
1 እንደ አንዳንድ ፍቅሃዎች (የፊቅህ ሊቃውንት) ጥቅሞች ገንዘብ ተብለው አይጠሩም።
٢
2 ‹‹የጥቅም ስጦታዎች›› የሚለው አገላለፅ ፉቅሃዎች ዘንድ የተለየ የቃል አጠቃቀም አለው። ይህም አል-አሪያ ወይም ውሰት ተብሎ ይጠራል።

‹‹የባለቤትነት መብት ማስተላለፍ›› የሚለው አገላለፅ እዳን መሰረዝ ወይም ነፃ ማድረግ አያካትም። ምንም እንኳ እርዳታ ወይም ስጦታ የሚለው ቃል ለመጠቀም ቢወሰንም ማለት ነው። ምክኒያቱም ነፃ ማድረግ ወይም መሰረዝ ማለት አንድን ነገር መተው ማለት ነውና።

እርዳታ የሚለው ቃል የሚያመላክተው ሃዲያ (ስጦታ) እና አል-አጢያት (አስተዋፅኦ ወይም ጉርሻን) ነው። እንዲሁም በጎነትን እና ደግነትን እና ውለታን ያካትታል።

የእርዳታ ሁክም

እርዳታ የተወደደ ተግባር ነው። ምክኒያቱም ልቦችን ያስተሳስራል ፣ ጥቅሞችን ፣ ሽልማትን ፣ ፍቅርን እና ውዴታን ያስገኛልና ነው። ከዚህ በተጨማሪ ቁርአን ፣ ሱና እና የኡለማኦች ስምምነት እንደሚያመላክተው እርዳታ የተወደደ ተግባር መሆኑን ነው።

ሃይማኖት መስጠትን ያበረታታል። ምክኒቱም ነፍስን ከስግብግብነት ፣ ከስስት እና ከመጨባጣነት ክፋት የሚያነፃ በመሆኑ ነው። ምክኒያቱም ልቦችን በእዝነት ያስተሳስራል ፣ በሰዎች መካከል ውዴታን ያጠናክራልና ነው። በተለይ ደግሞ ወዳጅ ፣ ጎረቤት ወይም ደግሞ ጥላቻ ያለበት ሰው ሲወስደው። በእርግጥ በሰዎች መሃል ጠብ እና ጥላቻ ይፈጠራል። የዝምድናም ገመድ ይበጠሳል። ይህኔ እርዳታ ጣልቃ ይገባና ልቦችን ወልውሎ ከክፋት ያፀዳል። በልቦቻቸው ውስጥ ያደረውን ጥላቻ እና መቃቃር ያስወግዳል። ከዚህ በተጨማሪ የአሏህን ውዴታ ፈልጎ እርዳታ የሰጠ ሰው ሽልማቱን ያገኛል።

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስጦታዎችን ይቀበላሉ፤ እሳቸው የሆነ ነገር ይሰጣሉ። (ቡኻሪ 2585)

ልክ እደዚሁ ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ከሰዎች ሁሉ የበለጠ ለጋስ ቸር ነበሩ። ጅብሪል በሚያገኛቸው የረመዷን ወር የልግስና (የቸርነት) ጫፍ ላይ ይደርሱ ነበር። ቁርአን ሊያስተምራቸው በሁሉም የረመዷን ሌሊት ያገኛቸው ነበር። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም ለጋስ (ቸር) ሰው ናቸው። ያለ ማቆም ከሚነፍስ ንፋስ ይበልጥ ነበር።›› (ቡኻሪ 6 ፣ ሙስሊም 2308)

የእርዳታ ምሰሶዎች

ኡለማኦች ስጦታ ከእርዳታ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነና ነገርግን በሌሎች ምሰሶዎች ላይ እንደሚለያዩ ይስማማሉ። ሆኖም ስጦታ የሚፈፀመው በቀላሉ አንድን ነገር በማቅረብ ነው። ስጦታ ንግግር ወይም ስራ ሊሆን ይችላል። ነገርግን ተቀባዩ ሰው የሚወስደው ገንዘብ የለም። የሚቀበለው ነገር ካልሆነ በቀር። ነገርግን የውል ስምምነት ውስጥ አይገባም።

የእርዳታ ቅድመ ሁኔታዎች

١
1 ለጋሹ ሰው ገንዘቡን ወይም ንብረቱን ማስተላለፍ መቻል አለበት።
٢
2 የሚለግሰው የንብረቱ ባለቤት ወይም ለመለገስ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው መሆን አለበት።
٣
3 ለጋሽ ሰው በራሱ ወዶና ፈቅዶ መሆን አለበት እንጅ በውሉ ተገዶ መሆን የለበትም።
٤
4 የሚሰጠው ሰው ገንዘቡን ወይም ንብረቱን የማስተዳደር አቅም ያለው መሆን አለበት። የንብረቱ ባለቤት ሊሆን ለማይገባ ሰው መስጠት ተቀባይነት የለውም። የህግ ጉዳይም ከግምት ውስጥ ይገባል። የተቀባዩ ሞግዚት በህግ ፊት ባላንጣ (ንብረት ተካፋይ) መሆን የለበትም።
٥
5 የእርዳታው ተጠቃሚ ሰው በህይወት ያለ መሆን አለበት። ምክኒያቱም እርዳታው ንብረትን ማስተላለፍ ነውና። ነገርግን የንብረቱ ባለቤት ለሌለም ሰው ቢሆን ማስተላለፍ ይችላል።
٦
6 የእርዳታው ተጠቃሚ በግልፅ ተለይቶ የሚታወቅ ከሆነና የለገሰው ሰው ቤቴን ለገሌ እና ለገሌ ወይም ለወንድሜ ሰጥቻለሁ ካለ በስጦታው ተቀባይነት ዙሪያ በፍቅሃዎች ዘንድ አለመስማማት አለ።
٧
7 ምንም እንኳ መሸጥ ባይፈቀድም እርዳታው በጥሩ ነገር ሊገለገሉበት የሚችል መሆን አለበት። ምክኒያቱም እርዳታ ከልውውጥም ይሰፋልና።
٨
8 የሚሰጠው ነገር መኖር አለበት። ምክኒያቱም የሌለ ነገር ሊሰጥ አይችልም። እስኪኖር ድረስ ስጦታው ይራዘማል። የሚታወቅ እና የሌለ ንብረት ሆኖ ነገርግን በኋላ ላይ የሚኖር መሆኑ ከታወቀ መስጠቱ ተቀባይነት አለው።

የሚሰጠው ነገር የሚታወቅ ወይም የማይታወቅ እና የሚከፈል ወይም የማይከፈል በሚለው ቅድመ ሁኔታ ላይ ኡለማኦች ተለያይተዋል።

ከስጦታን ለጥቅም መስጠትን የተመለከቱ ሁክሞች

አንድ ሰው የማይገባውን ጥቅም ለማስከበር ወይም ለማስፈፀም ሲል ለአንድ ማናጀር ፣ ሰራተኛ ወይም ሌላ የስራ ሃላፊ ስጦታ መስጠት፤ ስጦታው ለሰጭው እና ለተቀባዩ የተከለከለ ነው። ምክኒያቱም ጉቦ ነውና። ይህን የሰጠም የተቀበለም የተረገመ ነው።

አንድ ሰው ከሚበድለው ሰው እራሱን ለማዳን ወይም መብቱን ለማስጠበቅ ሲል ስጦታ ቢሰጥ፤ ስጦታው ለሚቀበለው ሰው የተከለከለ ነው። ነገርግን ስጦታውን ያቀረበው ሰው ተፈቅዶለታል። ምክኒያቱም መብቱን ለማስጠበቅ እና ስጦታውን ካበረከተለት ሰው ክፋት ይታደገዋልና ነው።

አቡ ሐሚድ አሰአዲ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከበኒ አሰአዲ ጎሳ የሆነ ኢብን አል-ኡተቢያ ተብሎ የሚጠራ ሰው ዘካ እንዲሰበስብ ሰየሙት (መረጡት)። ገንዘቡን ይዞ በተመለሰ ጊዜ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አላቸው፡ ‹‹ይህ ለአንቱ ነው። ይህ ደግሞ ለእኔ እንደ ስጦታ የተሰጠኝ ነው አለ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚንበራቸው ላይ ቆሙና አሏህን ካላቁና ካወደሱ በኋላ ‹‹ዘካ እንዲሰበስብ ከላክነው ከዚህ ሰራተኛ ጋር ያለው ችግር ምንድን ነው? ይህ ላንቱ እና ይህ ደግሞ ለእኔ ነው›› እያለ ተመለሰሳ። ከእናት እና ከአባቱ ቤት ሆኖ ቆይቶ ስጦታ ይሰጠው ወይም አይሰጠው እንደሆነ አያይም ወይ? አሉ። ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ ማንኛውም ነገር ባልተፈቀደ መንገድ የወሰደ ሰው በትንሳኤዋ ቀን አንገቱ ላይ ተሸክሟትይመጣል። ግመል ከሆነ ያጉረመርማል ፣ ላም ከሆነች ደግሞ እምቧ ትላለች ፣ በግ ከሆነ ደግሞ እምባ ይላል አሉና። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ብብታቸው እስኪታይ ድረስ ሁለቱንም እጃቸውን ከፍ አደረጉና ‹‹ጥርጥር የለውም! የአሏህ መልዕክት አላደረስኩምን? አሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ደግመው አሉ።›› (ቡኻሪ 7174 ፣ ሙስሊም 1832)

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር