መማርዎን ይቀጥሉ

ሎግ ኢን አላደረክም
መማር ለመጀመር፣ እድገትን ለመከታተል፣ ነጥቦችን ለመሰብሰብ እና ወደ ውድድር ለመግባት አሁኑኑ በታ ፕላትፎርም ይመዝገቡ፡ ከተመዘገቡ በኋላ ለሚማሯቸው ርዕሶች የኤሌክትሮኒክስ ሰርተፍኬት ይደርስዎታል።

የአሁኑ ክፍል ::ሞዴል

ትምህርት የሱና በመጽሃፍ መሰብሰብ እና አስፈላጊ መጽሃፎቿ

የእስልምናነሊቃውንት ሱና መዝግቦ እና ጠብቆ በማቆየት ፣ ትክክለኛው ከደካማው በመለየት ፣ የዠጋቢዎችን ታማኝነት በማጥናት እድሚያቸውን ለዚሁ አላማ ሰጥተው ኖረዋል። በዚህ ትምህርት ውስጥ ሱናን በፅሁፋ ላይ ማስፈር ምን እንደሆነ ፣ ደረጃዎቹን እና በጣም ወሳኝ የሚባሉ የሱና መጽሐፍትን ትማራላችሁ።

 የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና የመፃፍ ደረጃዎችን ማወቅ የታወቁ ወሳኝ የሐዲስ መጽሐፍትን ማወቅ የአንድን ሐዲስ ትክክለኛነት እና ደካማነት እንዴት ማወቅ እንደምትችሉ ማወቅ

የነብዩን ሱና በፅሁፍ ማስፈር

የእስልምና ሊቃውንቶች ሱናን በመፃፍ እና ጠብቆ በማቆየት ፣ ትክክለኛውን ከደካማው በመለየት ፣ የዘጋቢዎችን ታማኝነት በማጥናት እድሜያቸውን ለዚሁ አላመ ሰጥተው ኖረዋል።

የነብዩን ሱና በፅሁፍ የማስፈር ትርጉም

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግር ፣ በስራ እና በፅብት ያስተላለፉትን ነገር ሁሉ መፃፍ ፣ መመዝገብ እና በመጽሐፍ መልክ ማሰባሰብ ነው።

የነብዩ ሱና እና ሐዲሶች በመጽሁፍ የማስፈር ሂደት የተለያዩ ደረጃዎችን ያልፋል። እነሱም፡-

١
የመጀመሪያው ደረጃ፡ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና በሶሃቦች ጊዜ መፃፉ
٢
ሁለተኛው ደረጃ፡ የሐዲስ በፅሁፍ የማስፈር ሂደት በታቢኦች ዘመን ፣ሞጮሮሻ ላይ
٣
ሶስተኛው ደረጃ፡ ሱናን በመጽሐፍ መልክ የማሰባሰብ ሂደት
٤
አራተኛው ደረጃ፡ ከሌሎች ንግግሮች ጋር ሳይቀላቀል የነብዩን ሐዲሶች ብቻ ነጥሎ የመሰብሰብ እና የማደራጀት ሂደት

የመጀመሪያው ደረጃ

በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና በሶሃቦች ዘመን ሐዲስን በጽሁፍየመሰነድ ስራ የጀመረው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ዓ.ሂ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሳቸው ከቁርአን ጋር እንዳይቀላቀል በመፍራት እንዳይፃፍ ከልክለው ነበር።

አቡ ሰኢድ አልሁድሪ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእኔ ምንም ነገር አትፃፍ። ከቁርአን በቀር ከእኔ ማንኛውንም ነገር የፃፈ ሰው፤ ያጥፋው። በቃሉም ይተርክ። በእሱ ላይ ጥፋት የለበትምና። ውሸትን ወደ እኔ ያስጠጋ ሰው (ሆንብሎም ብለዋል) በእርግጥ መኖሪያውን የጀሐነም እሳት ውስጥ ይፈልግ ብለዋል።›› (ሙስሊም 3004)

ሆኖም የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ተጠብቀው የቆዩት እና የተላለፉት በቃል ትረካ ነው። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተወሰኑ ሶሃቦች እንዲፅፉ ፈቀዱላቸው።

አብዱሏህ ቢን አምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰማሁትን ሁሉንም እፅፍ ነበር፤ ከእሱ ለመሸምደድ አስቤ። ቁረይሾች ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ አንዳንዴ በቁጣ አንዳንዴ በደስታ የሚናገር የሰው ልጅ ሆኖ ሳለ ከእሱ የሰማሃውን ሁሉ ትፅፋለህን? ሲሉ ከለከሉኝ።ከዚያም መፃፌን አቆምኩና ለአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ነገሩ ገለፅኩላቸው። እሳቸውም በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ ‹‹ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ! ከእሱ የሚወጣው እውነት ብቻ ነው›› አሉ።›› (አቡዳውድ 3646)

በአል-ወሊድ ቢን ሙስሊም ሐዲስ ውስጥ አል-አውዘይ እንዳስተላለፈውአቡኹረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ አሏህን ካላቁ በኋላ ‹‹አሏህ መካ ውስጥ መፋለምን ከልክሏል። ለመልዕክተኛው እና ለምዕመናን በእሷላይ ስልጣንን ሰጥቷል። ከእኔ በፊት ለማንኛውም ሰው መፋለም አልተፈቀደም፤ ከቀኑ በተወሰነው ክፍል ብቻ ለእኔ ተፈቀደልኝ። ከእኔም በኋላ ለማንም አይፈቀድም። ያደን እንስሳት ሊሳደዱ አይገባም። እሾሃማ ቁጥቋጦዎቿ መነቀል የለባቸውም። በውስጧ ወደቀን ነገር ማንሳት አይፈቀድም፤ ለእሱ (ለሚያነሳው ነገር) ለሰዎች ያሳወቀ ቢሆን እንጅ። ዘመዶቹ የተገደሉበት ሰው ካሳን የመቀበል ወይም አፀፋውን የመመለስ (የመበቀል) ምርጫ አለው። አል-አባስ አለ ‹‹አል-ኢዝሂር በቀር፤ ምክኒያቱም ይህን የምንጠቀመው በመቃብሮቻችን እና በቤቶቻችን ውስጥ ነውና›› አለ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹አቡሻህ ፃፈው›› አሉ። (ንዑስ ተራኪው አል-አውዘኢን ጠየቀው) የአሏህ መልዕክተኛ ፃፈው? ያሉት ያሉት ምን ለማለት ነው አለ።እሱም ሲመልስ ‹‹ከአሏህ መልዕክተኛ የሰማውን ንግግር ነው›› አለ። (ቡኻሪ 2434 ፣ ሙስሊም 1355)

ሁለተኛው ደረጃ

ሐዲስን በፅሁፍ ላይ የማስፈር (የመሰነድ) ስራ የተከናወነው በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አመተ ሂጅራ በታቢኦች ዘመን ማብቂያ ነው። ይህ ጽህፈት የሚታወቀው የነብዩ ሱና ጥቅል ጽህፈት በመሆኑ ነው። ነገርግን የተለየ አቀማመጥ አልነበረውም። ያ ያሳሰበው የመጀመሪያው ሰው የሙዕሚኖች (የአማኞች) መሪ (አሚር) የሆነው ኡመር አብዱል አዚዝ (ረሂመሁሏህ) ነው። ሆኖም ሁለቱን ኢማሞች ሺሃብ አዙሁሪ እና አቡበክር ቢን ሃዝም ሱናውን እንዲሰበስቡ አዘዛቸው። ከዚያም የሚከተለውን ለተለያዩ ሐገራት ፃፈ፡ ‹‹በኡለሞች ሞት የሐዲስ እውቀት እንዳይጠፋ ስለፈረሁ የአሏህ መልዕክተኛን ሐዲስ ሰብስቡ መዝግቡ ሸምድዱ።››

ስለዚህ ሐዲሱን በትዕዛዙ መሰረት የፃፈው የመጀመሪያው ኢማሙ አዝሁሪ (ረሂመሁሏህ) ነው። ይህ ደግሞ የሱና እና የሐዲሶች አጠቃላይ መጽሐፍ ጅምር ነው።

ሶስተኛው ደረጃ፡

ደረጃ፡ የሱና ጥንቅር በኢማን ፣ አውቀት ፣ ንፅህና ፣ ሶላት ወዘተ በሚሉ ርዕሶች ተከፋፍሎ እና በደንብ ተደራጅቶ በመጽሐፍ መልክ የተሰነደበት ነው።ወይም በሰንሰለት አኳኋን የአቡበክርን ሰንሰለት፣ ከዚያም የዑመርን ወዘተ ይጠቅሳሉ።

በዚህ ደረጃ፡ ኢማሙ ማሊክ ቢን አነስ (ረሂመሁሏህ) ሙወጧዕን ያዘጋጁበት ነው። ይህ ደረጃ የሚታወቀው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግሮች ከሰሃቦች እና ከታቢኦች ንግግር እና ፈትዋ ጋር የተደባቁበት በመሆኑ ነው።

አራተኛው ደረጃ

ይህ ደረጃ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች በመከፋፈል ፣ በመሰብሰብ እና ከሶሃቦች እና ከታቢኦች ንግግር ጋር ሳይቀላቀል (ከሚያስፈልገው ከተወሰነው በቀር) የተደራጀበት እና የተሰነደበት ጊዜ ነው።ይህ ደረጃ የጀመረው በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ሂጅራ መጀመሪያ ላይ ሲሆን በውስጡም በጣም ዝነኛ ከሆኑት መጽሃፎች መካከል ሙስነድ አል-ኢማም አህመድ፣ ሙስነድ አል-ሁሜይዲ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ሐዲሱን በፅሁፍ ላይ የማስፈር ስራ ግቡን የመታው በሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ነው። ኢማሙ አል-ቡኻሪ ሰሂህ ቡኻሪን ፣ ኢማሙ ሙስሊም ሰሂህ ሙስሊም እና ከሱነን መጽሐፍት ደግሞ ሱነን አቡዳውድ ፣ ትርሚዚ ፣ ነሳኢ ፣ ኢብን ማጃ ፣ ሱነን ዳርሚ እና ሌሎች ታዋቂ የሐዲስ መጽሐፍት የተዘጋጁበት ወቅት ነው።

ወሳኝ የሱና መጽሐፍት (ኪታብ)

ከብዙ የነብዩ ሱና ኪታቦች መካከል ስድስቱ ታዋቂዎች ናቸው። እነሱም ሰሂህ ቡኻሪ ፣ ሰሂህ ሙስሊም ፣ ሱነን አቡዳውድ ፣ ኢብን ማጃ ፣ ፣ ነሳኢ እና ትርሚዚ ናቸው።

ከሱነን የሱና መጽሐፍት ታዋቂ የሆኑት ደግሞ አል-ዳሪሚ ፣ ሙሰነድ ኢማሙ አህመድ እና ሙወጧ ኢማሙ ማሊክ ናቸው።

ስድስቱ መጽሐፍት ማስተዋወቅ

ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙት የሡና ኪታቦች መካከል ስድስቱ መጽሐፍት ይጠቀሳሉ። እነሱም፡-

1 ሰሂህ አል-ቡኻሪ (የሞተው 256ዓ.ሂ)

ፀሐፊው ከአሏህ መልዕክተኛ የደረሰውን ኢማን ፣ የአምልኮ ተግባራት ፣ ግብይት ፣ ጦርነት ፣ ትርጉም እና ትሩፋቶች ወ.ዘ.ተ በሚሉ ይዘቶች መልክ የተደራጀ ሰፊ እና ሁሉን አቀፍ ከሆኑ የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው።

2 ሰሂህ ሙስሊም (የሞተው 261ዓ.ሂ)

በይዘታቸው ሰፊ እና ሁሉን አቀፍ ከሆኑ የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፀሐፊው የሐዲሶችን ትክክለኛነት ላይ ትኩረት አድርጎ ሰርቷል። ነገርግን እሱን ለማስተካከል ከተጠቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች አንፃር ሲታይ ከቡኻሪ ቀለል ይላል። በዚህም ምክኒያት ከቡኻሪ ቀጥሎ ሁለተኛው መጽሐፍ ነው።

3 ሱነን አቡዳውድ (የሞተው 275ዓ.ሂ)

‹‹ሱነን›› ተብለው ከሚጠሩ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው። ምክኒያቱም ጽሐፊዎቻቸው ያዘጋጇቸው ከፊቅህ ጋር በተያያዘ ነውና። ፀሃፊው በመጽሐፍ ውስጥ ሰሂህ እና ሐሰን እና ጥቂት ደካማ ሐዲሶች አካቷል።

4 ሱነን ትርሚዚ (የሞተው 279ዓ.ሂ)

ሰፊ የሐዲስ ስብስብ ከያዙ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ መጽሐፍ ጸሐፊው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶችን እምነት ፣ የአምልኮ ተግባራት ፣ ግብይቶች ፣ ጦርነቶች ፣ የትርጉም ማብራሪያ ፣ ትሩፋቶች በሚሉ ርዕሶች አደራጅቶ ሰንዷል። ነገርግን ሰሂህ (ትክክለኛ) ሐሰን (ጥሩ) ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶች ቢኖሩም ፀሐፊው ሰሂህ ሐዲሶች ላይ ትኩረት አላደረገም።

5 ሱነን ነሳኢ (የሞተው 303ዓ.ሂ)

ይህ የሐዲስ ስብስብ መጽሐፍ ከፊቅህ ጋር በተያያዘ በምዕራፎች ተከፋፍሎ እና ተደራጅቶ የጠዘጋጀ ነው። በውስጡም ሰሂህ (ትክክለኛ) ፣ ሐሰን (ጥሩ) እና ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶችን ይዟል።

6 ሱነን ኢብን ማጃ (የሞተው 273ዓ.ሂ)

ይህ የሐዲስ ስብስብ መጽሐፍ ከፊቅህ ጋር በተያያዘ በምዕራፎች ተከፋፍሎ እና ተደራጅቶ የተዘጋጀ ነው። መጽሐፌ ሰሂህ ፣ ሐሰን እና ዶኢፍ ሐዲሶችን አካቶ ይዟል። ነገርግን ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶቹ ይበዛሉ።

ኢማሙ ሐፊዝ አቡ አል-ሐጃጅ አል-ማዚ (የሞተው 742ዓ.ሂ) እንዲህ ብሏል፡-

ሱናን በተመለከተ አሏህ አዋቂ ሸምዳጆችን (ሃፊዞችን) ፣ እውቅ ሊቃውንትን ፣የሆኑን ሰጥቶታል። በዚህም በአጭበርባሪዎች እንዳይበረዙ ፣ እንዳይቀየሩ ፣ ካላዋቂዎች ትርጉም እና ስህተት እንዲፀዳ በማድረግ አሏህ ጠብቆ አቆይቶታል። እንዳይጠፋ እና ጠብቆ ለማቆየት በማሰብ በብዙ መንገዶች ከፋፍለው እና አደራጅተው በፅሁፍ መልክ ሰንደው አስቀምጠዋል። በአከፋፈሉነ እፁብ ድንቅ ፣ በአዘገጃጀቱ ረቂቅ ፣ በጣም ትክክል ፣ በጣም ጠቀሚ እና በበረካው ከሁሉም በላይ የላቀ በግኝቱ በጣም ቀላል ፣ የተስማሙበትም ሆኑ ያልተስማሙበት ሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የላቀ ደረጃ ያለው ነው። እነዚህ ትክክለኛ የሰነድ ስብስቦች አብዱሏህ ኢብን ኢስማኢል አል-ቡኻሪ ፣ የዐቡ አል-ሁሴን ሙስሊም ኢብን አል-ሃጃጅ አል-ኒሰፑሪ ትክክለኛ ስብስቦች እና ከዚያም ‹‹የአል-ሱነን›› መጽሐፍት በአቡዳውድ ሱለይማን ኢብን አል-ሻአስ አል-ሰጂስታኒ እና ከዚያም ደግሞ ‹‹የአል-ጃሚዕ›› መጽሐፍ በአቡ አብዱረህማን አህመድ ኢብን ሹአይብ አል-ነሳኢ እና ኢብን ማጃ ተብሎ የሚታወቀው አቡ አብዱሏህ ሙሐመድ ኢብን የዚድ መጽሐፍ ‹‹አልሱነን›› ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው። ምንም እንኳ ኢብን ማጃ ከሌሎቹ አንፃር ደከም ያለ ቢሆንም ማለት ነው።

እያንዳንዳቸው እነዚህ ስድስት መጽሐፎች በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤው ያላቸው ሰዎች ዘንድ በጣም የጣወቁ ሲሆን በእስልም ሐገሮች ተሰራጭተዋል ትልቅ ጥቅም ሰጥዋል።›› (ተህዚቡ አልከማል ጥራዝ 1 ገፅ 147)

ትክክለኛ እና ደካማ ሐዲስን መለየት

አንድ ሙስሊም ሰው የሐዲስን ደረጃ ትክክለኛ ተቀባይነት ያለው ወይም ደካማ ወይም ደግሞ ተቀባይነት የሌለው ነው የሚለው በሐዲስ ጥናት ላይ የጠሰማሩ ሊቃውንትስራ በመመልከት ማወቅ ይቻላል። በእርግጥ እነዚህ ሊቃውንት ሐዲስን ከአነጋገር ፣ ከዘገባው ሰንሰለት ፣ ተቀባይነት ያለው እና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ያጠኑታል።

በዚህ መንገድ የተፃፉ እና የጠደራጁ ብዙ መጽሐፍት አሉ። እንዲሁም ደካማ ሐዲሶችን ከትክክለኛው ለማወቅ እና ለመረዳት የሚያስችሉ ብዙ አስተማማኝ አፕልኬሽኖች እና የመማሪያ መድረኮች አሉ።

የሐዲሶችን ደረጃ ለማወቅ ከሚረዱ አፕልኬሽኖች እና የመማማሪያ መድረኮች መካከል

በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሐዲሶችን ያካተተው የሐዲስ አውደ-ጥበብ ዱራር አለ-ሱኒ ድህረገፅ ላይ ይገኛል። ከዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡ https://dorar.net/hadith

ትምህርቱን አጠናቅቀሃል


ፈተና ጀምር